Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መንገድን አትልቀቅ Gtm

መንገድን አትልቀቅ የሡሀቦች ፋና
የዳዕዋ አደራረግ የሒክማ ጎዳና
በዕዝነት በትግስት በኢልም የታገዘ
ኢህላሱን ጠብቆ ብዙ የተጓዘ
ኢስላምን ሚጋብዝ በአውንታዊው ተስፋ
ምንም ሣይበግረው የሙሽሪክ ዘለፋ
ሽርክና ቢድአን ሚያወግዝ በኢፋ
ቢድአና ሽርክን አንገት የሚያስደፋ
መስጂድ እንዲሞላ በአቢድ ወረፋ
እውነተኛ መንገድ ጀህልን የሚያጠፋ

ባለ ግዜ ሆኑ ዘመን ተለወጠ
ጃሂሉ ቆመና አሊም ተቀመጠ
ይዩልኝ ሆነና የኢኽላስ ማጣት
በስሜት ጎዳና በጀህል መነዳት
አብሮህ ሚሠግደውን ከመስጂድ ማስወጣት
ሱናን ስለ ያዘ አድርገህ ጠላት
የሡና ወንድምህን በአደባባይ መጉዳት
የውስጡን ማስወጣት የውጪን መጣራት
ቆም ብለህ አስብ ወጣ ከስሜት
ቀርበህ ጠይቀሀል ምንድን ነው ጥፋቱ?
እድሉ ስላለህ ባንተ መገፋቱ
ሡናን ልወቅ ባለ ከመስጂድ መውጣቱ
አላህን ፍራ!!!