Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሶሃቦች ማኅደር ጓደኝነትን እንማር

ተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ

🌺 ከሶሃቦች ማኅደር
ጓደኝነትን እንማር

ሁሉም ነገር ቦታ አለው። ቀልድ፣ ቁምነገር፣ ቁጣ፣ ፈገግታ፣ ምክክር፣ ኩርፊያ፣ ረገብ ማለት፣ ጠንከር ማለት፣ ማዘን፣ መጨከን፣ መለገስ፣ መከልከል … የመሳሰሉትን ባህርያት እንደአስፈላጊነቱ በየሁኔታው ማንፀባረቅ የሰሃበተል ኪራም (ሪድዋኑላሂ አጅመዒን) ድንቅ ባህሪ ነው።

የጓደኛን ስሜት ተረድቶ በጥሩው ላይ ማበሰር፣ ሃሳብ ሲገባው ደግሞ ማፅናናት፣ ማስረሳትና ጥሩ ስሜት እንዲሰማው መጣር የመልካም ጓደኝነት ሚስጥር ነው።

ዑመር ኢብነልኸጣብ (ረዲየላሁዐንሁ) እንዳሉት☞
« የሆነ ነገር እናገርና ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይስቁ ነበር። »

ይህንን የአሚረል ሙእሚኒን ንግግር በመንተራስ ሃፊዝ ኢብኑ ሐጀር (ረሂመሁላህ) ቀጣዩን ብለዋል።

« አንድ ሰው ጓደኛው በሃሳብ ተዘፍቆ ሲያየው የሚያሳስበውን ነገር የሚያስወግድለትና ነፍሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ለሱ ማውራቱ ይወደድለታል። »
【ፈትሁል-ባሪ- 9/363】

قال عمر - رضي الله عنه -
” لأقولنّ شيئاً يُضحك النبي ﷺ “

قال الحافظ ابن حجر رحمه الله : المرء إذا رأى صاحبَه مهموما،ً استُحب له أن يحدثه بما يزيل همه ويطيب نفسه٠
[فتح الباري ٣٦٣/٩]

በመሆኑም ማንኛውም ሙስሊም ከጌታው ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳመር ዲኑን መማር፣ መገንዘብ፣ እምነቱን ማስተካከል፣ ዒባዳዎቹን በስርኣቱ መወጣት፣ ክልከላዎቹን መጠንቀቅና መራቅ እንዳለበት ሁሉ ከሰዎችም ጋር በመልካም ባህሪ መኗኗር ግድ ይለዋል።

ስለዚህም በዙርያው ላሉት ሰዎች ለሚያስተዳድራቸው ወይም አብሯቸው ለሚኖረው ቤተሰቦቹ፣ ለጎረቤቶቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለዘመዶቹና ለመሳሰሉት ጥሩ አሳቢ፣ መካሪ፣ የመጣባቸውን አደጋ ተከላካይ፣ በደስታቸው ተካፋይ ብሎም ሲያዝኑ ሲያስቡ የሚያፅናናቸውና በሀላሉ የሚያስደስታቸው ሊሆን ይገባል።

ለአላህ ብሎ ሙስሊም ወንድሙን በማስደሰቱ ነቢዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት ከአላህ ምንዳን ያስገኝለታልና።

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
( أَحَبُّ الأَعْمَالِ إِلَى اللَّهِ تَعَالَى سُرُورٌ تُدْخِلُهُ عَلَى مُسْلِمٍ ) رواه الطبراني (12/453) ، وصححه الألباني في "صحيح الترغيب" (955) .

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
«ልዕለ-ሃያሉ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ስራ በሙስሊም ልቦና የምታስገባው ደስታ ነው።» ብለዋል

ስለሆነም ተግባቢና አስተዋይ፣ አፅናኝና ተባባሪም እንሁን
--------------------
Muharram13/01/1437
October 27/10/2015
🌾www.fb.com/tenbihat

Post a Comment

0 Comments