ከፍሬያማ ሥራዎች
ባለ እዳ የሆኑ ችግርተኞችን ይቅር በማለት እዳቸውን ስለማለፍ
ባለእዳዎች ሲገጥሙንና ችግር ጭንቀታቸውን ለመገላገል ማድረግ የሚገባንን በተመለከተ አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ
(وَإِنْ كَانَ ذُو عُسْرَةٍ فَنَظِرَةٌ إِلَىٰ مَيْسَرَةٍ ۚ وَأَنْ تَصَدَّقُوا خَيْرٌ لَكُمْ ۖ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ). [سورة البقرة : ٢٨٠].
"የድኽነት ባለቤት የሆነ ሰው (ባለዕዳም) የሆነ እንደሆን እስኪያገኝ ድረስ (ክፈለኝ እያሉ ባለማጨናነቅ) ማቆየት ነው፡፡ የምታውቁ ከሆናችሁ (ይቅር በማለትም) ለነሱ መመጽወታችሁ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡» ይላል።
አል-በቀራህ: 280
በሀዲስም እንደተነገረን፤
عن أبي مسعود البدري رضي الله عنه قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:حُوسب رجل ممن كان قبلكم، فلم يوجد له من الخير شيءٌ، إلا أنه كان يخالط الناس، وكان موسرًا، وكان يأمر غلمانه أن يتجاوزوا عن المعسر، قال الله تعالى:نحن أحق بذلك تجاوزوا عنه“رواه مسلم
አቢ መስዑድ አል-በድሪይ አላህ ስራውን ይውደድለትና: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም «ከናንተ በስተፊት ከነበሩት ሰዎች መካከል ኣንዱ ግለሰብ ተገመገመና ምንም መልካም ስራ አልነበረውም። ነገር ግን ሰውየው ከሰዎች ጋር ይቀላቀላል (ተቀላቅሎ የሚኖር ሰው ነው)። ሀብታምም ነበርና ለሰራተኞቹ የተቸገረን ሰው ሲያገኙ (እዳውን) እንዲያልፉት ያዝዛቸው ነበር። በዚህም ምክንያት አላህ እኔ ይቅርታ ለማድረግ ተገቢ ነኝና (ይህ ሰው መልካም ስራ ባይኖረው እንኳ) እለፉት አለ።» ሙስሊም ዘግበውታል
ይህም የሚያሳየው የተቸገረን ባለእዳ በችግሩም በእዳውም ከገባበት ሃሳብ መገላገል ለወንጀላችን መማር ሰበብ መሆኑን ያስተምረናል።
ከዚህም በባሰ መልኩ ይህ ባለእዳን የማስደሰት ተግባር ለታላቅ እድል እንደሚያበቃ የሚያመላክቱ ሀዲሶች አሉ
"من أنظر معسرًا أو وضع له، أظله الله في ظله" رواه مسلم
«ብድሩን መክፈል ላዳገተው ችግረኛ ጊዜ የሰጠ ወይም እዳውን ያነሳለትን ሰው አላህ ‘በዓርሹ’ ጥላ ስር ያደርገዋል» ሙስሊም ዘግበውታል
አቢሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሰማሁ ብሎ ባስተላለፈልን ሀዲስ
وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: "من أنظر معسرًا أو وضع له، أظله الله يوم القيامة تحت ظل عرشه، يوم لا ظل إلا ظله". رواه الترمذي وقال حديث حسن صحيح، وصححه الألباني.
«ብድሩን መክፈል አቅቶት የተቸገረን ሰው የእዳውን መክፈያ ያቆየለት ወይም እዳውን ያነሳለት ሰውን በትንሳኤው እለት የሱ (የአላህ) ጥላ እንጂ ጥላ በሌለበት ቀን በዓርሹ ጥላ ስር ያደርገዋል።»
📝 ቲርሚዚ ዘግበውታል… አልባኒ ዘገባውን ትክክል ብለዉታል።
قال الامام القرطبي رحمه الله في تفسير الآية السابقة :
وقال جماعة من أهل العلم : قوله تعالى : فنظرة إلى ميسرة عامة في جميع الناس ، فكل من أعسر أنظر ، وهذا قول أبي هريرة والحسن وعامة الفقهاء.
📝 تفسير القرطبي [٣ /٣٧١]
👉🏾 ኢማም አልቁርጡቢ –አላህ ይዘንላቸውና– ከላይ የተጠቀሰቸውን አንቀጽ ሲያብራሩ:–
"ብዙዎቹ ሊቆች የአላህን ቃል ( ባለዕዳ የሆነን ሰው እስኪገራለት ጠብቁ…) የሚለው አንቀፅ ማንኛውም የተቸገረን ሰው ጉዳዩ እስኪገራለት ድረስ መጠበቅ እንዳለበት ያመላክታል። ይህም የአቡሁረይራ፣ የሀሰን እና የብዙ ሊቆች አቋም ነው።» ብለዋል።
【ተፍሲር አልቁርጡቢ: 3/371】
👉🏾 ኢማም አን-ነወዊ አላህ ይዘንላቸውና ከነዚህ ሀዲሶች የምንረዳውን ሲያብራሩልን ደግሞ
وقال النَّووي رحمه الله :
وفي هذه الأحاديث فضل إنظار المعْسِر والوضع عنه، إمَّا كلَّ الدَّين، وإمَّا بعضه مِن كثيرٍ أو قليلٍ، وفضل المسَامَحة في الاقتضاء وفي الاستيفاء، سواء استوفى مِن مُوسِر أو مُعْسِر، وفضل الوضع مِن الدَّين، وأنَّه لا يحتقر شيء مِن أفعال الخير، فلعلَّه سبب السَّعادة والرَّحمة .
📝 شرح صحيح مسلم ( ١٠/٢٢٤ ).
🔹እዳ መክፈል አቅቶት ያልቻለን ሰው መክፈያውን ማቆየት ወይም ሙሉውን መተው፣ ካልሆነም አብዛኛውን ወይም ጥቂትም ቢሆን ይቅር ማለት
🔹እዳን ሲከፍሉም ሆነ ሲያስከፍሉ ( ያለውን ሰው እና የሌለውን) በይቅርታ ማለፍ እና
🔹እዳን ይቅር ማለት ያለው ደረጃ የላቀ መሆኑ
እንዲሁም ማንኛውም መልካም ስራ ትንሽም ቢሆን የደስታና የእዝነት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል መናቅ እንደሌለበት ያመላክታል።» ብለዋል።
📝 ሸርሕ ሰሒሕ ሙስሊም (10/224)
አላህ ከእዳ ያላቅቀን። ባለ እዳዎችንም ይቅር ከሚሉ ምርጥ የአላህ ባሮች ያድርገን። የሰዉን ችግር የምንረዳ፣ የዱንያን ጉዞ የምንገነዘብ፣ ለኣኺራችን የምንስገበገብ ደጎችም ያድርገን።
--------------
©ተንቢሀት
0 Comments