Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከፊል አካልን ፀሀይ ላይ ከፊሉን ደግሞ ጥላ ላይ ማድረግ ክልክል ነው!!

ከፊል አካልን ፀሀይ ላይ ከፊሉን ደግሞ ጥላ ላይ ማድረግ ክልክል ነው!!

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡ አንድ ሰው በፀሀይ ብርሃንና በጥላ ላይ መቀመጡን ከልክለዋል፡፡ “የሸይጧን አቀማመጥ ነው!” ሲሉም ገልፀውታል፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 3081]
ታላቁ ዓሊም አሽሸይኽ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡-
“ይህም ማለት አንድ ሰው እንዲህ አይነቱን አቀማመጥ ከጅምሩም ይሁን አጋጥሞት ሊቀመጥ አይገባም፣ አይበጅምም፡፡ ከጅምሩም ስንል ሆን ብሎ በፀሀይና ጥላ ላይ መቀመጡን ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሊሆን የሚገባው ወይ ሙሉ ለሙሉ ፀሀይ ላይ ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ጥላ ላይ መሆን ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውነት በአንድ ሁኔታ ላይ ማለትም ወይ ሙቀት ላይ ወይ ደግሞ ቅዝቃዜ ላይ ሲሆን ሚዛኑን የጠበቀ ይሆናል፡፡ ከፊሉ ጥላ ላይ ከፊሉ ፀሐይ ላይ ሲሆን ግን ከፊሉ ተፅእኖ ያርፍበትና ብርድ ያገኘዋል፡፡ ከፊሉ ደግሞ ሙቀት ያገኘዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ጎጂ ነው፡፡ …” 

[ሸርሑ ሱነን አቢ ዳውድ፡ 27/478]

Post a Comment

0 Comments