Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጠላቶች ኢስላምን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። አደገኛውም አካሄዳቸው ...

ጠላቶች ኢስላምን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።
አደገኛውም አካሄዳቸው ሙስሊም መስሎ መንቀሳቀስ ነው።
ይህ አካሄድ ከሄዱት ጀማሪዎች ውስጥ የመጀመርያው አብደላህ ኢብን ሰባ (የሁዲ) ይገኝበታል። ሰዎች ከሸሪአዊ እውቀት ሲያፈገፍጉ እሱ ለነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች ልዩ ውዴታ ያስፈልገናል በማለት አዛኝ መስሎ መሪ ሊሆን የሚገባው ኡስማን ሳይሆን አልይ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ ነው በማለት ሞኝ ተከታዮቹን አፍርቶ 3ኛውን ኸሊፋ ኡስማንን አስገድሎ ከሙስሊሞች ከተገነጠሉት የመጀመርያዎቹ ቡድኖች ውስጥ ሺአዎችን መሰረተ።
እንዲህ አይነት ሰርጎ ገብ የኢስላምን ሽፋን ተጠቅመው ኡማውን ለሚያጠሙ ለሚሞክሩ እርኩሶች መፍትሄዎቹ በጥቂቱ
1) ሸሪአዊ እውቀትን ማካበትና በተግባር ላይ ማዋል። ይህንንም ለማህበረሰቡ ማዳረስ።
2) እውነተኛ ከሽርክ፣ ከቢድአ፣ ከቡድንተኝነት፣ ከፍልስፍና የፀዳ አንድነትና ወንድማማችነት ማዳበር ግድ ይላል።
3) እርጋታና፣ ሶብር፣ የሱና ኡለማዎችና በሱና ላይ ከሸበቱ ታላላቆች ጋር መማከር ያስፈልጋል።
4) የሆነ ነገር ሲከሰት ከመቻኮል ይልቅ ረጋ ብሎ ያን ነገር ከስር ከመሰረቱ አጥንቶ የማያዳግም መልስ መስጠት። የኢስላም ጠላቶች አንድ ነገር ሲለቁ ለመላው ማህበረሰብ ሼር እያደረጉ ብዥታቸው እንዲሰራጭላቸው ከማድረግና ማህበረሰቡን ግራ ከማጋባት፣ ለሚመለከታቸው መልስ ሊሰጡ ይችላሉ ለሚባሉት ኡለማዎች፣ ኡስታዞችና ዱአቶች ብቻ ሼር ማድረግ።
አላህ ግን ድል ለማን እንደሆነ ሲናገር
وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ
አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛው፣ ለምእመናንም ነው። ግን መናፍቃን አያውቁም።

ሙስሊሞች ሆይ! የተፈጠርንለትን አላማ ጠንቅቀን ልናውቅና ልንተገብር፣ ላንዘነጋውም ግድ ይለናል።
ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ በዱንያ ተውጧል፣ የተፈጠረለትን አላማ ዘንግቷል፣ መብላት መጠጣት ብቻ ሀሳቡ የሆነ ስንት አለ። አላህ ያስተካክለን።
መፍትሄው ነብዩ ሰለላሁ አለይ ወሰለም እንዳሉት ወደ ዲን መመለስ ነው።
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ጠላቶች ለሊትና ቀን የሚያቅዱትን ተንኮል ያክሽባቸው።

Post a Comment

0 Comments