Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከምግብ በኋላ ጥርስ ላይ የሚቀር ጥቃቅን የምግብ ቅሪት ውዱእ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ


🍁 ከምግብ በኋላ ጥርስ ላይ የሚቀር ጥቃቅን የምግብ ቅሪት ውዱእ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ 

📝 ተከታታይ መልእክቶቸ ከ "ፈታዋ ለሙስሊም ሴቶች" መፅሀፍ

ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል ዑሰይሚን

ጥያቄ ፦
====
አንዲት እህት እንዲህ በማለት ጠይቃለች፤ " ምግብ " ከተመገብኩ በኋላ አንዳንድ ጊዜ በጥርሴ ውስጥ ተስግስገው የማገኛቸው ቁርጥራጮች አሉ ውዱእ ከማድረጌ በፊት እነዚህን የምግብ ሽርፍራፊዎች የማስወገድ ግዴታ አለብኝ ?"

መልስ ፦
====
ለእኔ ግልጽ እንደሆነልኝ ከውዱእ በፊት እነዚህን የምግብ ሽርፍራፊዎች የማስወገድ ግዴታ የለብሽም። ይሁን እንጂ ጥርስን
ሁልጊዜም በንጽህና መያዝ ያለምንም ጥርጥር በላጩ ነገር ከመሆኑም በላይ በበሽታ እንዳይጠቃም ይከላከላል ።

እነዚህ የምግብ ቅሪቶች በየጊዜም
በንጹህና የማይወገዱ ከሆነ ጥርስንና ድድን በማበስበስ ለከፍ ጉዳት ይዳርጉታል። ስለሆነም አንድ ሰው ምግብ ተመግቦ እንደጠናቀቀ ማድረግ ያለበት ጥርሱ ላይ የተጣበቁ ጥቃቅን ቅሪቶችን በተቻለው አቅም ማስወገድ ና ማጽዳት ነው። ምግብ የአፍን ጠረን ስለሚቀይር ሚስዋክ በመጠቀም በየጊዜው ጥርስን መፍቅ ያስፈልጋል። የአላህ መልዕክተኛ ሲዋክን (መፍቂያን) አስመልከተዉ

የሚከተለውን ብለዋል ፦
"ሚስዎክ የጥርስ ንጽህናን ይጠብቃል እንዲሁም አላህን ደስ ያስኛል"

[ አህመድ ና ኢብን ሒባን ዘግበውታል ]

ስለሆነም ጥርሳችንን ማጽዳት ካለብን በሚስዋክ (መፋቂያ) ብናደርገው ተመራጭ ነው። አላህ የበለጠ ያውቃል።

[ሽይኽ ሙሐመድ ኢብን ኡሰይሚን]
–––––//–––––

© ተንቢሀት... ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት

Post a Comment

0 Comments