Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ሰርግ ሳይጠራኝ፣ ለቅሶዬን በላኝ›› ‹‹ፊቴን ላስመታ››



‹‹ሰርግ ሳይጠራኝ፣ ለቅሶዬን በላኝ››
‹‹ፊቴን ላስመታ››

የዛሬው አርስት የሚያጠነጥነው በመልካም አብሮ ስለመኗኗር ይሆናል፡፡ ምህበረሰባችን ላይ በብዛት ቅይይም ከሚፈጥሩ ነገሮች ውስጥ ሰርግና፣ ሀዘን ይገኙበታል፡፡

ሰርግ
እንደሚታወቀው አብዛኛው ወጣት ወደ ትዳር እንዳይገባ የትዳር ጣጣውን፣ ድግሱን፣ ጥሎሹን እና የመሳሰለውን አልችልም ብሎ ነው ወደ ኋላ የሚያፈገፍገው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ አረ በዛም ያሉ ጓደኞቹ ተጣጥሮ የመሰረተው ትዳር ላይ ‹‹እኔን ሳይጠራን››፣ ‹‹እነንትናን ጠርቶ እኔን ዘለለኝ››፣ ‹‹ምግብ አላጣሁ ይሄን ያህል….››፣ ‹‹ከአንድ እንጀራ በላይ አልበላ እንዲሁ ደስታው ልካፈልለት ብዬ እንጂ፣ እንዴት ሰርጉን ሳይጠራኝ….›› እና የመሳሰለውን ሲሉ ይሰማሉ፡፡

ዋናው ነገር እስቲ ጓደኛህን ታዝቤዋለሁ፣ ተቀይሜዋለሁ እያልክ ነገር የምትሰብኩ ወንድምና እህቶች ሆይ! እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት፡፡ ይህ ያገባ ጓደኛህ ቤተሰብ አለው፣ የቅርብ ዘመዶች አሉት፣ ጎረቤቶችና አብሮ አደጎች አሉት፣ ከዚህም አልፎ አብሮ አደጎቹ ልክ እንዳንተ አይነቶች ደግሞ ብዙ ጓደኞች አሉት፡፡ ታድያ መጀመርያውንም ይህን ሁሉ ሰው ደግሶ ማብላት ቢችል ኖሮ ደግሶ በጠራህ ነበር፡፡ እውነታው ግን ተጨናንቆ እገሌን እገሌን የልጅቷ ቤት ይዤ ብሄድ፣ እነ እገሌን እኔ ጋር ብጠራ ብሎ አቅሜን ልወቅ ሲል ምናለ አንተ እንዲህ አይነት ‹‹እንዴት ሰርግ አይጠራኝም ነገር›› እያነሳህ ባትወጋው፡፡

ይልቁንስ አንተ እና ሌሎች ጓደኞቹ አዋጥታችሁ ለዚህ ላገባ ወንድማችሁ ለቤቱ ሊሟላለት ከሚገቡ ንብረቶች ውስጥ ለምን አትገዙለትም?
ይህ ነበር ከጓደኛ የሚጠበቀው፡፡ ይሀው ምክር ለሴቶችም ጭምር ነው፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሰው አታጨናንቁ፡፡

ለቅሶ
‹‹ለቅሶዬን በላው›› እየተባለም ይጠቀሳል፡፡ መቼም አንድ የአኸይራ ወንድም ወይንም እህት ሌላኛው ወንድምና እህት የሞት ሀዘን እንዳጋጠማቸው ሲሰሙ ወድያው መድረስ ባይችሉ እንኳን መጀመርያ የሚያደርጉት ለሟቹና ለቤተሰቦቹ ‹‹አላህ ይዘንለት፣ አላህ ይማረው፣ አላህ ቀብሩን ያስፋለት….. ለሟች ቤተሰቦች አላህ ፅናቱን ይስጣቸው…›› ታድያ ይሄን ሁሉ ታላቅ ነገር አድርገው፣ ከዛም አልፎ ደውለው በአካል ተመችቷቸው እስኪመጡ ድረስ ‹‹አብሽር/ሪ ሟችን አላህ ይዘንላቸው›› ብለው ዱዓ ካደረጉልህና ካፅናኑህ ለምን ሌላ ነገር እየፈለግክ ትተነኩሳለህ?

ዛሬ እንደሚታየው ብዙው ሰው ሰፈሩ ሩቅ፣ ትራንስፖርት አስቸጋሪ በሆነበት ሁኔታ ሰውን እንዲህ ማጨናነቁ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የሚያስገርመው አንዳንድ ለቅሶ ደራሾች በጣም ከመጨነቃቸው የተነሳ ሀዘን የደረሰባቸው ቤተሰቦችን ሊጠይቁ ሲሄዱ ‹‹ተኝቷል›› ቢባሉም አያ እስኪነሳ እጠብቃለሁ ‹‹ፊቴን አስመትቼ እሄዳለሁ›› ወይንም ‹‹እንትና መጥቶ/ታ ነበር›› የሚል የፅሁፍ ወይንም የድምፅ መልክት ያስቀምጣሉ፡፡ እንግዲህ ይህ አካሄድ ወይ የሰውየው ምላስ ተፈርቶ ወይ እንደው ለአላህ ተብሎ መሰራቱም ጥርጥር ውስጥ ሊከት በሚችል መንገዱ ውስጥ እስኪገባ እያደረገው ነው፡፡

አንዳንዶች ደግሞ ሀዘን የደረሰባቸው ሰዎች በስራ ሊታገዙ ሲገባቸው ሀዘንተኞቹ ቤት ሄደው ‹‹ጫት እየቃሙ›› ሀዘንተኞቹን ሻይና ቡና አፍሉልን እያሉ ያስቸግራሉ፡፡ ሀዘን የደረሰባቸው ቤተሰቦች ምግብ ተይዞላቸው ይኬዳል፡፡
ሰዎችን ከማጨናነቅ አላህን እንፍራ እላለሁ፡፡

Post a Comment

0 Comments