Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሳምንቱ አጀንዳ የጁምዓ ቀን ከሌላው ቀን የተሻለ ልዩ የሆነ በርካታ ብልጫ ኣለው።


የሳምንቱ  አጀንዳ
የጁምዓ ቀን ከሌላው ቀን የተሻለ ልዩ የሆነ በርካታ ብልጫ ኣለው። ይህ ቀን ከሳምንቱ ቀናት ብልጫ እንዳለው በማስመልከትም በርካታ ሀዲሶች ተነግረዋል።

በተለይም ጁምዓ ቀን ቢተገበር መልካም ትሩፋት እንዳላቸውም የተነገሩ በርካታ ኢባዳዎች ኣሉልን። ከነሱም መካከል:

1- صلاة الجمعة
አንደኛው የጁምዓ ሰላት ሲሆን ይህንንም በማስመልከት ሃያሉ አምላካችን አላህ በቃሉ
( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِي لِلصَّلاةِ مِنْ يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَى ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ )
الجمعة: 9 .
«እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ! በጁምዓ ቀን ለሰላት ጥሪ ሲደረግ አላህን ወደ ማውሳት ሂዱ። መሸጥንም (ንግድን) ተዉት። የምታውቁ ከሆነ ይኸ ለናንተ በጣም የተሻለው ነው።»

በማለት ከዱንያ ጥቅማጥቅም ተላቅቀን የሳምንቱን መልእክት የምንሰማበትን፣ ጌታችን አላህ በስፋት የሚወሳበትንና የሚወደስበትን፣ የሚሰገድለትንና ምህረቱን የምንጠይቅበት የአምልኮ ተግባር ላይ ለመሳተፍ ወደ ጁምዓ ሰላት ፈጥነን እንድንጓዝ ይመክረናል።

ኢብነልቀይዪም አልጀውዚይ ረሂመሁላህ በዛደል ሙዓድ ቅፅ 1 ገፅ 376 ላይ ባሰፈሩት መሰረት
قال ابن القيم رحمه الله:
” صلاة الجمعة هي من آكد فروض الإسلام ، ومن أعظم مجامع المسلمين ، وهي أعظم من كل مجمع يجتمعون فيه ، وأفْرَضُه سوى مجمع عرفة ، ومن تركها تهاونا بها طبع الله على قلبه اهـ“
زاد المعاد (1/376)

«የጁምዓ ሰላት ከኢስላም ግዴታዎች መካከል በዋነኛነት የፀደቀና የተረጋገጠው ሲሆን ሙስሊሞች ከሚሰባሰቡበት ስርዓትም ዋነኛው ነው። ሙስሊሞች ተሰባስበው ከሚሳተፉበትም ታላቁ ነው። ስብስቡም የዓረፋ እለት ስብስብ አይነት ነው። በስንፍና ጁምዓ ላይ መገኘትን የተወን ሰው አላህ ልቡ ላይ ያትምበታል።» ብለዋል።

በተጨማሪም በአቡዳዉድ ዘገባ አቢጀዕድ አድዲምሪ ረዲየላሁ አንሁ ከነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰምቶ እንዳስተላለፈልን

عن أبي الجعد الضمري –وكانت له صحبة- عن النبي صلى الله عليه وسلم قال :
( من ترك ثلاث جمع تهاونا بها طبع الله على قلبه ) .
رواه أبو داود (1052) وصححه الألباني في صحيح أبي داود (928) .

«በዝንጉነት ሶስት ጁምዓዎችን የተወ ሰው ልቡ ላይ አላህ ያትምበታል።» ብለዋል። አልባኒም ሰሂህ ብለውታል።

በኢማሙ ሙስሊም ዘገባም
وعن عبد الله بن عمر وأبي هريرة : أنهما سمعا رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول على أعواد منبره : ( لَيَنْتَهِيَنَّ أَقْوَامٌ عَنْ وَدْعِهِمْ [أي تركهم] الْجُمُعَاتِ أَوْ لَيَخْتِمَنَّ اللَّهُ عَلَى قُلُوبِهِمْ ثُمَّ لَيَكُونُنَّ مِنْ الْغَافِلِينَ ) . رواه مسلم (865).

ከአብደላህ ኢብኑ ዑመርና ከአቡሁረይራ በተላለፈልን መሰረት ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
«እኒያ ሰዎች ጁምዓዎችን ከመተው ቢቆጠቡ ይሻላቸዋል። ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያትምባቸውና ከዚያም ከዝንጉዎች ሆነው ያርፏታል።» ብለዋል።

ያትምበታል ሲባል ሀቅን ለይቶ እንዳይቀበል፣ ሸርን አውቆት እንዳይርቅ ልቡን ያሽገዋል። ድርቅናን ያላብሰዋል። ሀራም ከሀላል የማይለይ ለስሜቱ አዳሪ ያደርገዋል። በደመነፍሱ የሚንቀሳቀስ፣ ስለዲኑ የማያሳስበው፣ ቸልተኛ ሰነፍ ይሆናል… እንደ ማለት ነው።

2🌠- الإكثار من الدعاء ዱዓእ ማብዛት

በዚህ በጁምዓ እለት በአላህ ፈቃድ ዱዓእ ተቀባይነት የምታገኝበት ልዩ ወቅት ኣለችና የምንፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ አላህን ልንለምነው ይገባል።

ይህንንም በተመለከተ ከአቢሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ በተነገረው መሰረት
عن أبي هريرة رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ذَكَرَ يَوْمَ الْجُمُعَةِ فَقَالَ : ( فِيهِ سَاعَةٌ لا يُوَافِقُهَا عَبْدٌ مُسْلِمٌ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي يَسْأَلُ اللَّهَ تَعَالَى شَيْئًا إِلا أَعْطَاهُ إِيَّاهُ وَأَشَارَ بِيَدِهِ يُقَلِّلُهَا ) . رواه البخاري (893) ومسلم (852) .

የአላህ መልእክተኛ ለላሁ አለይሂ ወሰለም የጁምዓን ቀን ኣወሱና ከዚያም
«በዚህች እለት ማንኛውም ሙስሊም የሆነ የአላህ ባርያ ያቺን ወቅት ገጥሞ ቆሞ አየሰገደ ሃያሉ አላህን ምንም ነገር ቢለምነው ሳይሰጠው የማይቀርበት የሆነች ሰዓት ኣለች» ኣሉና የነገሩን ቀላልነት ለመግለፅ በጣታቸው አመላከቱ ይለናል።

3🌠- قراءة سورة الكهف ሱረቱል ካህፍን ማንበብ

ከአቢሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ አንሁ በተነገረው መሰረት
عن أبي سعيد الخدري : أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "من قرأ سورة الكهف في يوم الجمعة أضاء له من النور ما بين الجمعتين" . رواه الحاكم . وصححه الألباني في صحيح الترغيب (836) .

ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
«በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ከኑር ያበራለታል።» ብለዋል።

4🌠- الإكثار من الصلاة على الرسول صلى الله عليه وسلم
በአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት ማብዛት

ከአውስ ቢን አውስ ረዲየላሁ አንሁ በተወራው መሰረት
عن أوس بن أوس : عن النبي صلى الله عليه وسلم قال :
( إِنَّ مِنْ أَفْضَلِ أَيَّامِكُمْ يَوْمَ الْجُمُعَةِ ، فِيهِ خُلِقَ آدَمُ عَلَيْهِ السَّلام ، وَفِيهِ قُبِضَ ، وَفِيهِ النَّفْخَةُ ، وَفِيهِ الصَّعْقَةُ ، فَأَكْثِرُوا عَلَيَّ مِنْ الصَّلاةِ فَإِنَّ صَلاتَكُمْ مَعْرُوضَةٌ عَلَيَّ، قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَكَيْفَ تُعْرَضُ صَلاتُنَا عَلَيْكَ وَقَدْ أَرَمْتَ -أَيْ يَقُولُونَ قَدْ بَلِيتَ- قَالَ : إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ حَرَّمَ عَلَى الأَرْضِ أَنْ تَأْكُلَ أَجْسَادَ الأَنْبِيَاءِ عَلَيْهِمْ السَّلام ) . رواه أبو داود (1047) وصححه ابن القيم في تعليقه على سنن أبي داود (4/273) . وصححه الألباني في صحيح أبي داود (925)

ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
«"ከቀናቶቻችሁ መካከል በላጩ ጁምዓ ነው። በእለቱ ኣደም አለይሂ ሰላም ተፈጠረ። በእለቱም ሞተ። የቅስቀሳዋ ጥሩንባም በእለቱ ነው የምትነፋው። መጥፊያም በእለቷ ነው። በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። ሰላታችሁ እኔ ዘንድ ትቀርባለችና።" ሲሉ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንዴት ነው ሰላታችን የሚቀርብልዎት? እርስዎ እንደሆን ሞተው አፈር ሆነዋልና" ሲላቸው "ሃያሉና አሸናፊው አላህ የነቢያትን አለይሂ ሰላም አካል እንዳትበላ መሬት ላይ እርም አድርጎባታል።» በማለት መለሱለት።

♻ ከዚህ ሁሉ ብልጫዋም ጋር የጁምዓን ቀን ሆነ ምሽቷን በሸሪዓ ያልተደነገገ አምልኮትን እንዳንፈፅምባት ከልክለውናል።

አቡሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ እንዳሉት
فعن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : ( لا تَخْتَصُّوا لَيْلَةَ الْجُمُعَةِ بِقِيَامٍ مِنْ بَيْنِ اللَّيَالِي ، وَلا تَخُصُّوا يَوْمَ الْجُمُعَةِ بِصِيَامٍ مِنْ بَيْنِ الأَيَّامِ ، إِلا أَنْ يَكُونَ فِي صَوْمٍ يَصُومُهُ أَحَدُكُمْ ) .
رواه مسلم (1144) .

ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
«የጁምዓን ሌሊት ከሌሎች ሌሊቶች ለይታችሁ በሌሊት ሰላት አትዩዋት። አንዳችሁ ቀደሞም ትፆሟት የነበረች ፆም ካልሆነ በስተቀር የጁምዓን ቀንም ከሌሎች በተለየ ሁኔታ በፆም አትለይዋት።» ብለዋል።

ስለዚህም ሀዲስ ኢማሙ ሰንዓኒ በሱቡለ ሰላም ላይ እንደሰፈሩት
« የጁምዓን ምሽት በኢባዳ ለየት ማድረግ ሀራም ለመሆኑ ይህ ሀዲስ ማስረጃ ነው። ሱረቱል ካህፍን የመሰለ መረጃ የመጣለትን ከመቅራት ባለፈም ሌላ ያልተለመደ የሆነ ቂራኣትም ክልክል ነው።» ብለዋል።
【ሱቡለ-ስሰላም】

ኢማሙ ነወዊም እንዳሉት
«ይህ ሀዲስ የጁምዓን ሌሊት ከሌሎች ሌሊቶች በሰላት ለየት ማድረግ ክልክል ለመሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው። ቀኑንም በፆም ለየት ማድረግም እንደዚያው። ይህም ተግባር የተጠላ ለመሆኑ ስምምነት ያለበት ጉዳይ ነው።» ብለዋል።
【ሸርህ ሰሂህ ሙስሊም】

ኢማሙ ነወዊ ጨምረው ሲያብራሩ
«ምሁራን እንዳሉት የጁምዓን ቀን በፆም መለየት የተከለከለበት ጥበቡ: - የጁምዓ ቀን የዱዓእ፣ የዚክር እንዲሁም ትጥበት፣ ቀደም ብሎ መስጂድ የመሄድና ሰላትን የመጠባበቅ፣ ኹጥባን የማድመጥ፣ ከዚያም በኋላ አላህ
فَإِذَا قُضِيَتْ الصَّلاةُ فَانْتَشَرُوا فِي الأَرْضِ وَابْتَغُوا مِنْ فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا

"ሰላት እንዳበቃች በምድር ላይ ተበተኑና (ተዘዋወሩና) የአላህን ፀጋ ፈልጉ፣ አላህንም በብዛት አውሱ" ባለው መሰረት ዚክር የሚያበዙባት የኢባዳ ቀን ናት።

ከዚህም ውጭ ላሉት አምልኮዎች ሲባል በእለቱ ኣለመፆም የተወደደ ሆኗል። እነዚህን ስራዎቿን በንቃት፣ በደስታ፣ እየጣመው ሳይሰላችና ሳይሳነፍ እንዲወጣውም አጋዥ እንዲሆንለት ነው። እንዲሁም በሀጅ ወቅት የአረፋ እለት በአረፋ ምድር ካለው ሁኔታ ጋርም ይመሳሰላል። ሱናውም ለዚህ ጥበብ ሲባል ማፍጠር ነው። ጁምዓ ቀንን ነጥሎ መፆም ለተከለከለበት ጥበቡም የምንጠቅሰው ምክንያት ይኸ ነው። … »
【ሸርሁ ሰሂህ ሙስሊም】
_____________
23 Muharram 1437
06 November 2015


Post a Comment

0 Comments