Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እየሳቁ ይማሩ!! ለሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡- ...


እየሳቁ ይማሩ!!
ለሸይኽ ኢብኑልዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡-
ጠያቂ፡- አንድ ሰው ሌላ ሰው ተከትሎ ይሰግዳል፡፡ (ሁለት ብቻ ሆነው ማለት ነው፡፡) ሶስተኛ ሰው ገባና ኢማሙን ወደ ኋላ ጎተቶ አብሮት ቆመ፡፡ ተከታይ (መእሙም) የነበረውን ወደፊት ገፍቶ አስቀደመው፡፡ የነዚህ ሰዎች ተግባር ልክ ነውን?
ሸይኽ፡- እንዴት ይሆናል? ምናልባት በተቃራኒ እንዳይሆን፡፡ ጥቄውን በድጋሜ አንብበው፡፡
ጠያቂ፡- አንድ ሰው ሌላ ሰው ተከትሎ ይሰግዳል፡፡ ሶስተኛ ሰው ገባና ኢማሙን ወደ ኋላ ጎተቶ አብሮት ቆመ፡፡ ተከታይ (መእሙም) የነበረውን ወደፊት ገፍቶ አስቀደመው፡፡ የነዚህ ሰዎች ተግባር ልክ ነውን?
ሸይኽ፡- (እየሳቁ) እንዴ ሰዎች ይሄኮ ተቃራኒ ስራ ነው!!
ጠያቂ፡- ግን ይሄ በተጨባጭ ተከስቷል፣ አላህ መልካሙን ይዋልልህና፡፡
ሸይኽ፡- ጥሩ፡፡ ኢማሙን ጎትቶ ተከታዩን ሲያስቀድመው ተከታዩ አሁን ምን ሆነ?
ጠያቂ፡- ኢማም ሆነ!!
ሸይኽ፡- አዎ ኢማም ሆነ!! ለምንድን ነው ይሄ አዲስ ገቢው ኢማሙን የሚጎትተው? እንዴት ኢማምነቱን አፍርሶ ሌላ ይተካበታል?
ጠያቂ፡- ምናልባት ባለማወቅ ይሆናል፡፡ አላህ መልካም ይዋልልህና፡፡
ሸይኽ፡- ደግሞ ተከታዩም (ኢማም ነህ ሲባል) ምንም ሳያስተባብል ቀጥታ ኢማም ሆነ?!! (ታዳሚው ይስቃል፡፡)
ምንም ይሁን ምን ኢን ሻአላህ ሶላቱ ልክ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢማም ተከታይ ሊሆን ይቻላልና፡፡ ልክ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳደረጉት ማለት ነው፡፡ አቡበክር ሰዎችን እያሰገደ ሳለ ወጡና ተቀድመው ከአቡበክር በግራ በኩል ተቀመጡ፡፡ ይህኔ አቡበክር ኢማም ከሆነ በኋላ እንደገና መእሙም (ተከታይ) ሆነ፡፡ ስለዚህ ችግር የለውም፡፡
ነገር ግን ይቺ ርእስ ዱንያ ላይ ካሉ እንግዳ (አስደናቂ) ነገሮች አንዷ ናት፡፡ ምንም ይሁን ምን ሶላታቸው ትክክለኛ ነው፡፡
[ሊቃኣቱ ባቢልመፍቱሕ ካሴት ቁ. 188፣ ገፅ ለ]

Post a Comment

0 Comments