Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሠለፎች ዙ ህ ድ የሀሰን ቢን አቢ ሀሰን አል-በስሪይ ዙህድ [ረሂመሁላህ]




🎐ከሠለፎች ዙ ህ ድ

የሀሰን ቢን አቢ ሀሰን አል-በስሪይ
ዙህድ [ረሂመሁላህ]
زهد الحسن بن أبي الحسن البصري رحمه الله

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህችን ዓለም የፈጠራት ለግዜያዊ መኖሪያነት፣ መጠቃቀሚያነትና መሸጋገርያነት ነው። ይህንን ሁኔታ አስተውሎ፣ ጥቅምና ጉዳቱን ለይቶ እንዲገለገልበት አእምሮ የተሰጠው ደግሞ የሰው ልጅ ነው።

ያለማስተዋልና ያለ ስሌት እየተጠቀሙባት የሚኖሩባት ህይወት ያላቸው ፍጡራን በርካታ ናቸው። እነርሱም እንሰሳ ይባላሉ። ከሰው ልጆች ጋር የሚጋሩት በርካታ ባህሪ ቢኖራቸውም እንኳ ልዩነታቸው ግን የማይደረስበት ሰፊ የሆነ ነው። እሱም የሰው ልጅ ማሰቢያ አእምሮ የተለገሰው መሆኑ ነው።

ታዲያ ከሰው ልጆች መሃል ደግሞ ለጋሹን ጌታውን የከዳና ያስተባበለው እንዳለ ሁሉ ያመነበትና ያመሰገነውም ሞልቷል።

እነዚያ የከዱት ባለውለታቸው የሆነውን ፈጣሪ ጌታቸውን ሲከዱት ማስተዋያቸውን ባለመጠቀማቸው ለሆዳቸው ብቻ ኣድረው እንደ እንሰሳ ያለ አምላካዊው ህግና ስርኣት እንዳሻቸው ውለው የሚያድሩ ናቸው።

እነዚያ ምእመናን ደግሞ ይህች አለም ለመሸጋገሪያ መጠቃቀሚያነት እንደተፈጠረችላቸው እንደሚያውቁት ሁሉ እነሱም ያን ፈጣሪያቸውን ብቻ ለማምለክ እንደተፈጠሩ በማመን በአግባቡ ያመሰግኑታል ያመልኩታል።

ህርም ያደረገባቸውን ይርቃሉ የፈቀደላቸውን ይጠቃቀማሉ። ከዚህም ኣልፈው ለጌታቸው ካላቸው እፍረትና መተናነስ የተነሳ ከተፈቀደላቸውም ነገር ላይ ራሳቸውን ያዝ ያደርጋሉ። ላለመስገብገብም ይህችን አለም ችላ ይሏታል። ትኩረታቸውን ለመጨረሻዋ አለም በማድረግ ይናፍቋታል፣ ያለቅሱላታል፣ ምቾታቸውን ይቀንሱላታል፣ በትንሹ ለመብቃቃትም ያገኟትን ከነሱ ላነሰውም ለበለጠውም ያካፍላሉ።

የዚህ አይነቱ ለዚህች አለም ብዙም ቦታ ያለመስጠት ህይወት #_"ዙህድ" ይባላል።

ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑ በርካታ የሠለፍ ሷሊሆች ታሪክን መጥቀስ ይቻላል። ለዛሬም ሀሰን አል-በስሪይ [ረሂመሁላህ ] ለዚህች አለም ያላቸውን ምልከታና ለኣኪራቸው ያላቸውን ጥንቃቄ [ዙህዳቸውን] በጥቂቱ ላስተዋውቃችሁ ☞

ዐልቀማህ ቢን ሙርሰድ ስለ ሀሰን አል-በስሪይ (ረሂመሁሙሏህ) ዙህድ እንደሚከተለው አስፍረዋል።

[[“ ከሀሰን አል-በስሪይ በበለጠ በጣም የሚያዝን ሰው አልገጠመኝም። ለአደጋ እንግዳ የሆነ ይመስለንም ነበረ። እንዲህም ይሉ ነበር ” ☞

«እንስቃለን! ግን አላህ የሆነ ስራችንን መርምሮብን ይሆናልና። " የኣደም ልጅ ሆይ…ወየውልህ፤ ምንም ነገር አልቀበልህም" ቢልህ
… ከአላህ ጋር ጦርነት ለመፋለም አቅም ኣለህ ?
አላህን ያመፀ እኮ ከሱ ጋር እየተዋጋ ነው ያለው።

ወላሂ! የበድር ዘመቻ ላይ ከተሳተፉት ሶሃቦች ሰባ ሰዎችን አግቻለሁኝ። ልብሳቸውም (ከበግ ቆዳ የሚሰራ) ሱፍ ነው። ብታይዋቸው ኖሮ ዕብዶች ናቸው ትሉ ነበር።

እነሱም ከናንተ መካከል ምርጥ የሚባለውን ቢያዩ ኖሮ ' እነዚህስ ከመጨረሻዋ እለት ምንም ድርሻ የላቸውም ' ይሏችሁ ነበር። ከናንተ መሃል መጥፏችሁን ቢያዩ ደግሞ 'እነዚህስ በመጨረሻዋ እለት አያምኑም' ባሏችሁ ነበር።

ከሰዎች መካከልም እነሱ ዘንድ ይህች አለም ከእግራቸው ስር ካለች አፈር ባነሰ የቀለለች የሆነች (ቦታ የማሰጧት) ሰዎችንም አይቻለሁ።

እንዲሁም ለእራቱ ከአንድ ጉርሻ ያለፈ መብል ሳይኖረው የሚያመሽ ሰውም ገጥሞኛል።» ይሉ ነበር።

አቡ ሀሰን ሀሰን አልበስሪይ በተግባርም ሊመገቡ ሲቀርቡ …
“ ከፊሉን ለአላህ አደርጋለሁ እንጂ ይህንን ሁሉንማ ከሆዴ አልከትተውም ”። ይሉ ነበር

ሀሰን አል-በስሪይ [ረሂመሁላህ] ሰደቃ ከሚሰጡት ሰው ይልቅ እሳቸው ችግርተኛ ሆነው ሳለ እንኳ ከምግቡ ከፊሉን ሰደቃ ያደርጉ ነበር።»]]
ረሂመሁሙላሁ ራህመተን ዋሲዓ
----------------
ምንጮች☞ ⇣⇣
①ዐልቀማህ ቢን መርሰድ ቢን አቢ-ሃቲም ባዘጋጁት "የስምንቱ ታቢዒን ዙህድ" በተሰኘው ድርሳን ገፅ 61
②አቡ-ነዒም "ሂልያ" በተሰኘው ድርሳን [2/114] እንዳጠናቀሩት
እንዲሁም
③ ሂልያ [2/149]

በዚህም መሰረት እንግዲህ የሠለፎቻችንን ማንነት ማወቅና ያቅማችንን ያህል ራሳችንን ማረም ይገባናል።

~ለዱንያዊ ጥቅማ ጥቅም ስንል ስንቶቹን ሆን ብለን በድለናል
~የስንቶቹን ክብርና መብት ነክተናል
~ለስንቶቹ መክሰር ሆነ ለችግር መዳረግ ሰበብ ሆነናል
~የስንቶቹንስ ዝና፣ ስምና ስብዕና ለማጉደፍ ተሯሩጠናል
~በዚህ ክፉ በሽታችን ሰበብ ስንት መልካም ጓደኛ አጥተናል
~ከስንቱ ዘመድ ተራርቀናል
~ከስንቱ ጎረቤት ተኮራርፈናል
~የስንቶቹስ ትዳር ተናግቷል ተበትኗል
~ስንቶቹ ለወላጆቻቸው ጠላት ሆነዋል
~ስንቶችስ ከልጆቻቸው እሳትና ጭድ ሆነዋል
~በስንቱ ቀዳዳ ጉቦ አቀብለናል ወይም ተቀብለናል
~በስንቱ ሙስሊምሰ ላይ ክስ መስርተናል
~ለስንቱ የሀሰት መስካሪ ሆነናል
~እውነትን ላለመመስከርስ ስንቱን እውነታ ደብቀናል
~ስንቶችስ ከትዳራቸው፣ ከቤተሰባቸው፣ ከወዳጆቻቸውና ከቀዬኣቸው ተፈናቅለዋል
~በዚህ ምግባራችን ሰበብ ምን ያህልስ ዲናችንን አስሰድበናል
???????? ?????????

እርግጥ ነው “ ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ፈተናዎች ናቸው።” ተብለናል። ይሁንና ፈተና እስካለ ድረስ ተፈትነው የሚወድቁ እንዳሉ ሁሉ በፈተናው የሚያልፉ ኣሉና ባገኘናት ለመብቃቃትና ከኛ በላይ ላገኙት እንዲባረክላቸው በመመኘት ከኛ በታች ላሉትም እንዲከፈትላቸው በመለመን ላለንበትም ህይወት አላህን እናመስግነው።

ለዚህም ይረዳን ዘንድ ሰለፎችን እንወቃቸው

ሠለፎች
የየመስኩ ጎበዞች
ብልጫ ያላቸው ህዝቦች
*--------------------*
🎐27 ዙልሂጅጃ 1436
11 Oct 201

Post a Comment

0 Comments