Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ምላሳችንን አ ደ ራ ከሸይኽ ሡለይማን ሰሊመላህ አር-ሩሀይሊ የተሰጠ ድንቅ ምክር [ሀፊዘሁላህ]

ምላሳችንን አ ደ ራ
ከሸይኽ ሡለይማን ሰሊመላህ አር-ሩሀይሊ የተሰጠ ድንቅ ምክር [ሀፊዘሁላህ]
ሸይኹ አላህ ይጠብቃቸውና በድምፅ መልእክታቸው ቀጣዩን ብለውናል ☞
«🎐ይህንን ምክር በመተመለከተ ሁላችንም እንፈልገዋለን። የልቦች ሰላማዊነት የቸገረን ጉዳይ ነውና።
ይህም የሸሪዓዊ ሰላማዊነት ሲሆን፣ ተወቃሽ ያልሆነ መነሳሳት፣ መነቃቃትና ውጉዝ ያልሆነው መብረድ፣ መቀዛቀዝ ወይም ዝምታ ነው።
🎐 አንድን ነገር ያለ ቦታው የሚያስደርግ የሆነ የቀዘቀዘ ወርዕ ተፈላጊም የሚያስመሰግንም አይደለም።
🎐ልክ እንደዚያው አንድን ነገር ያለቦታው የሚያስደርግ የበዛ የሆነ መነሳሳትም የተመሰገነ ወይም የተወደሰ አይደለምና።
🎐የሰው ልጅ ለልቦናው ሰላማዊ መሆን ሊጓጓ ሊተጋ ይገባዋል። ትክክለኛ የሆነ ሸሪዓዊ መቆርቆር እርሱ ዘንድ መኖርም አለበት።
🎐ሲናገር በሸሪዓ ከሱ በሚፈለገው መልኩ መናገር አለበት። ዝም ሲልም ከሸሪዐ አንፃር ዝምታው የሚመሰገን ሊሆን ይገባል። በምላሱ ጉዳይ አላህን መፍራት አለበት። እርግጥ ንግግር ቀላል ነው፤ ነገር ግን መጨረሻው ከባድ ነውና።
🎐ከሸሪዓ አንፃር ስለሱ [ማለትም ስለ አንድ ግለሰብ] መናገሬ ይፈቀዳል የሚለውን ካላወቅክ በስተቀር ሰዎች ስለሆነ ሰው ተናግረውበታል፣ ስለሱ አውርተዋል ብለህ ብቻ አንተም ስለ አንድ ግለሰብ ከመናገር ተጠንቀቅ። ስለ ግለሰቡ ስታወራ መረጃ ይሆነሃልና።
🎐ባንተ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ስለ እገሌ እንከኑን [መጥፎ ነገሩን] ተናግረዋል በሚል አንተም ተከትለህ ማውራትህ በአላህ እምላለሁኝ በቀብርህ ውስጥ የሚጠቅምህም አይደለም።
🎐ይልቅ የሚጠቅምህ መናገርህን ሸሪዓው ካንተ የሚጠብቀው ስለሆነ የተናገርክ መሆንህን አላህ በልብህ ውስጥ ያለውን እንደሚያውቅብህ ማወቅህ ነው። ዙሪያውን ላካበበው ነገር ሲል የሆነ ነገር መናገሩ በሰውየው ላይ አደጋ ነውና።
🎐ይሁንና ስለዚያ ጉዳይ መናገርህን ሸሪዓው ካንተ የሚፈልገው ወይም የተፈቀደልህ ከሆነ ይኸ በአላህ መንገድ ላይ ከመታገል የሚቆጠር ነውና ትናገራለህ ወደ ኋላም አትበል። ነገር ግን የሰዎችን ክብር አታጣጥም። በሸሪዓው ድንበር ላይ ቆም በል።
🎐ለአላህ ስትል ስለምትጠላው ስለ አንድ ሰው ትናገራለህ፤ ሊጠላ በሚገባው የቢድዐ ተግባሩ ነው። ለዚያ ሲባል ይጠላልና።
🎐(በቢድዓው ሸሪዓን በመጣሱ) ክብሩ ተነክቶ ስለሱ ሊወራ ይችላል። በዚህም ግዜ ክብሩን ትነካለህ። (ይገባዋልና።)
🎐በሌላ በኩል ሸሪዓን የጣሱ ሴቶችን በተመለከተ ስለነሱ እንድናወራ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን ስለ ተጣሰው ሸሪዓ እንናገራለን።
🎐በዚህም ግዜ እንታገሳለን፣ ከአላህ እንተሳሰባለን፣ እንገፋበታለን፣ እንታገላለን። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ ልብ ልንለው የሚገባን) የእንስቶች ምላስ ከወንዶቹ በባሰ ሁኔታ ገዳይ [አጥፊ] መሆኑን ነው።
🎐ስለሆነም ሴቷ በእርቅና በማስተካከሉ ላይ ልትበረታ ይገባታል። ምክንያቱም እንስቷ ከተስተካከለች ህብረተሰቡም ይስተካከላል። ከተበለሻሸች ደግሞ ለብዙሃን መበላሸት ሰበብ ትሆናለች።
🎐ለዚህም ነው ነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] “ ከሴቶች የባሰ ለወንዶች ጎጂ የሆነ ነገር ከኔ በኋላ አልተውኩም።” ብለው ያሉን። ምክንያቱም ሴቷ በአካሏ ፈታኝ ትሆናለች፤ በአንደበቷ ፈታኝ ትሆናለች፤ እንዲሁም በተሳሳተ ዲናዊ አካሄዷም ፈታኝ ትሆናለችና።
💥ሴት ልጅ ወደ ጎጠኛ ቡድኖች [ማለትም ወደ ሂዝቢዮች] ስትሳብ… ይህም ከባድ የሆነ ቢድዓ ነውና ለብዙሃኑ ቤተሰቦቿ ወደ ጎጠኞች መሳብ መንገድ ትሆናለች። ስለሆነም በእንስቷ መስተካከል በርካታ መልካም ነገር ይገኝበታል።
🎐ሴቷን የምመክረው… አላህ ሀራም ያደረገውን ሁሉ በመራቁ ላይ እንድትታገልና በተለይ ከቀጣዮቹ ሶስቱ ነገሮች በመራቁ ላይ እንድትጥር ነው። እነሱም
~ የባሏን ውለታ ከመካድ
~ ወቀሳ ከማብዛትና
~ እርግማን ከማብዛት ሲሆን እነዚህም የሴቶች መጥፊያ ሰበቦች ናቸውና።
🎐ነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ባንድ ወቅት በዒድ ቀን ወንዶችን ከመከሩ በኋላ ሴቶች ላይ ሲደርሱ
" … تصدقن ، … فإني رأيتكن أكثر أهل النار ،
او قال: فإن أكثركن حطب جهانم"
“ እናንተ እንስቶች ሰደቃ መስጠትን አብዙ፣ ከእሳት ሰዎች አብዛኞቹ እናንተ ሆናችሁ አየኋችሁ።” ብለዋል።
በሌላም አገላለፅ “አብዛኞቻችሁ የጀሃነም ማገዶ ናችሁ።” ብለዋል። ከዚያም
قلن فبما يا رسول الله؟ … قال : تكثرن الشكاية ، وتكفرن العشير.
የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በምን ሰበብ ነው ስንላቸው … እናንተ ወቀሳ ታበዛላችሁ፤ የባሎቻችሁንም ውለታ ትክዳላችሁና ነው።” ብለዋል።
በሌላም ዘገባ
لإن كن تكثرن اللعن ، وتكفرن العشير.
“ እናንተ ዕርግማንን ታበዛላችሁ፣ የባሎቻችሁን ውለታም ትክዳላችሁ።” ብለዋል።
🎐በዚህ ሀዲስ እንግዲህ ሴቶች ሰደቃ ማብዛት እንዳለባቸው የሚያነሳሳ አስረጅ አለበት። እንዲሁም የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] በአንደበታቸው ለየት አድርገው በመከሯት ጉዳይ ላይ ትኩረት መቸር አለባት።
🎐ይህም “ እንስቷ አምስት ወቅቷን ከሰገደች፣ የረመዷን ወሯንም ከፆመች፣ ብልቷንም ከጠበቀች በፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።” ብለዋል።
🎐በዚህም መሰረት በመልካም ተግባራት ላይ በመጓጓት በነዚህ አራት ጉዳዮች ላይ መትጋት አለባት።
🎐በመሆኑም በግዴታ ሰላቶች ላይ መበርታት ይኖርባታል። ይህም አላህ አዝዘ ወጀል'ለ ለወንዱም ለሴቷም ባሮቹ ከሚለግሰው ተውፊቅ ምልክት ነውና።
🎐በግዳጁ ፆም ላይም መትጋት አለባት። እንዲሁም ሒጃብና በመሳሰሉት መቅድሞች ክብሯን በመጠበቅ ላይ የምትነሳሳ መሆን ሲኖርባት፣ ባሏን ከመታዘዟ ጎን ለጎን ሰደቃም በመስጠት ላይ መበርታት ይገባታል።
🎐በተጨማሪም ይህች እንስት የዲኗን እውቀት ተማሪና እውቀቱንም የምታሰራጭ ሆና ከላይ የጠቀስነውን ዝንባሌ ልኩን ሳታልፍ የምትወጣው ከሆነች ምንኛ ያማረባት እንስት ነች።
🎐ምክንያቱም እሷ ሱን'ናን አዋቂ በመሆኗ አላህን አዝ'ዘ ወጀል'ለ የምትጠነቀቅ፣ ጌታዋን የምትፈራና ምላሷን የምትጠብቅ እንዲሁም አላህ እንደሚቆጣጠራት የምታምን ናትና አንደበቷ ወደ አጥፊ ነገር እንዳይዶላት ትሰጋለች።
🎐አላህ አዝ'ዘ ወጀል'ለ ሴቶቻችንንና የሌሎች ሙስሊሞች እንስቶችንም የእሱን ፍራቻ በማላበስ ያክብርልን። ኸይርና በረከቱንም ያስፍንባቸው።
🎐ለቤተሰቦቻቸውና በዙሪያቸው ላሉትም ቅናቻ ሰበብ ያድርጋቸው።
🎐ከነፍሶቻቸውና ከአንደበቶቻቸው እንዲሁም ከሰውና ከጂን ሰይጣናትም ክፋት ያብቃቃቸው።
🎐እኛንም እነሱንም ከቢድዓዊው ቡድንተኝነትና ወደ ጎጠኞች ከሚቧደኑትም ጀማዓዎች ያርቀን።
🎐ሁሉ ነገሯ ራህመት የሆነችውን፣ ሁሉ ነገሯ ኸይር የሆነችውን፣ ሁሉ ነገሯ ሪፍቅ ልስላሴ የሆነችውን፣ ሁሉ ነገሯ ፍትህ ከሆነችውና ሁሉ ነገሯ ዕርቅና ማስተካከል የሆነችው … የመንሀጅ ሰለፉነ ሷሊሂን [ሪድዋኑላሂ አጅመዒን] ተከታይ ያድርገን።
🎐ይህች መንሀጅ ለሰውየው ለራሱ ራህመት ናት፤ በዙርያው ላሉትም እዝነት ናት፤ ለአስተዳዳሪዎችም ሆነ ለተዳዳሪዎቹም ደህንነት ናትና።
🎐አላህ አዝ'ዘ ወጀል'ለ ለዚህች መንሀጅ አብቅቶን ችሮታውን እንዲውልልን በዚያም ላይ እንዲያፀናን እለምነዋለሁ። በሆነ ነገሯ እንኳ ብንሳሳት ከሚመለሱትና ከሚታረሙት ያደርገን።
🎐 በዚህች ክቡር መንሀጅ ላይ እንፀና ዘንድም በሚመክሩን፣ በሚያስታግሱንና በሚረዱን ወንድሞች ቸርነቱን እንዲውልልን እለምነዋለሁ። አላህ ልዕለ ሃያልና የበላይ ነውና።»
ሲሉ ምክራቸውን ደምድመዋል።
___________
ከሸይኹ መልእክት የተገነዘብነው ባጭሩ
①ኛ ለዲናችን መነሳሳታችን፣ ሞቅ ሞቅ ማለታችን ከልኩ ማለፍ እንደሌለበት ሁሉ መቀዛቀዛችን፣ መቆጠባችንም የወረደ ሆኖ ሙት መሆን እንደማይገባን ተምረንበታል።
②ኛ እገሌ ወይም እነ እገሌ ስለ እገሌ እንከን ወይም ጉድለት ተናግሯል በሚል ብቻ እውነታውን ሳናውቅ ማሟሟቅ እንደማይገባን ሲያስረዱን በተለይ ጀርህ ወት-ታዕዲልን በተመለከተ ያሻው ሰው ሁሉ የሚዋኘው ኣለመሆኑን ጠቁመውናል ።
③ኛ ለየት ባለ ሁኔታም ሴቶቻችን አንደበቶቻቸውን ከማረም ጎን ለጎን በማክረርም ይሁን በማላላት ከተፈተኑት ቢድዓዊ ቡድኖች ማለትም ከሂዝቢዮች መጠንቀቅ እንዳለባቸው አመላክተውናል።
④ኛ ውለታን መካድና በሆነ ባልሆነው ወቀሳም ሆነ እርግማንን ማብዛት አደገኛ ጎጂ ባህሪ እንደሆነና መጠንቀቅ እንደሚገባ አስረድተውናል።
አላህ ሀቅን ከሚሰሙትና በሰሙትም ከሚጠቀሙበት ያድርገን።
ከ... ⇡AbuFewzan
---------------
ዚል-ሂጅ'ጃ 24/1436
October 08/2015

https://www.youtube.com/watch?v=BkKf5vDufrY&feature=youtu.be

Post a Comment

0 Comments