Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የምላስ እና እጅ መለያየት!!!


አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱሁ

የአላህ ሠላት እና ሠላም በመልዕክተኛው በቤተሠቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን
የምላስ እና እጅ መለያየት!!!

ሠዎችን በመልካም ማዘዝ እና እራስ አለመተግበር!! ወይም ከመጥፎ መከልከል እና እራስ አለመከልከል

☞ ከላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ለማንሳት የወደድኩት በርካቶቻችን በተለያዩ አጋጣሚዎች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሠዎችን የተለያዩ ሽልማቶችን የያዙ የቁርአን አንቀፆች እና በነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አንደበት የተነገሩ ሀዲሦችን በማጣቀስ መልካም ነገሮችን እንዲተገብሩ በማነሣሻ ቃላቶች እያሸበረቅን እንመክራለን እንገስፃለን እንደዛውም ደግሞ በቁርአን እና በሀዲስ የተነገሩትን የመጥፎ ተግባር ቅጣቶች እያጣቀስን ከመጥፎ እንከለክላለን ሆኖም እኛ ግን ካዘዝነው እና ከከለከልነው ነገር ተቃራኒ ሆነን የምንገኝ ስለበዛን ነው!

☞ ይህ ተግባር ድብን ያለ ውሸት ነው! የሚከሠተውም በኢማኑ ላይ ችግር ካለበት ሠው ላይ ነው! ወደ ኒፋቅ ከሚወስዱ መንገዶች አንዱና ዋነኛው መንገድ ነው !!

✔ አንድ ሠው የሚናገረውን የማይተገብር ከሆነ ወይ…
★ በሚያስተላልፈው መልዕክት እርግጠኛ አይደለም! እርግጠኛ ቢሆን ኖሮ ከመልካም ተግባሩ ጀርባ ያለውን ሽልማት ለማግኘት ሲል ይተገብረው ነበር
★ የሠዎችን ፊት ወደ ራሡ ለማዞር ሲል ነው በመልካም የሚያዛቸው ከመጥፎም የሚጠለክላቸው
★ ሠዎች ዘንድ ሷሊህ መስሎ ለመታየት ሲል ነው በመልካም አዞ የማይተገብረውና ከመጥፎ ከልክሎ የማይከለከለው
★ ወይ ደግሞ የእውቀት ደረጃው እንዲታይለት!

✔ አንድ ሠው የተናገረውን አለመስራቱ እላይ ከተጠቀሡት ምክንያቶች ውጪ ምን አይነት ምክንያት ሊኖር ይችላል? አንድ ሠው ምንን አስቦ የማይተገብረውን ሊናገር ይችላል?
☞ ይህን ተግባር በተመለከተ እየወቀሡት የመጡት የቁርአን እና የሀዲስ መረጃዎችን በአይነት ከፋፍለን እንመልከት

☞ ቁርዐን የቀደምት ነብያቶችን እንደ ምሣሌ በመውሠድ ይህን ተግባር ይወቅሣል ። እንደሚታወቀው ሠዎች በመምከር ደረጃ የመጀመርያውን ስፍራ የሚይዙት መልዕክተኞች ናቸው ሆኖም ግን አንድም ቀን የተናገሩትን ባለ መተግበራቸው ወይም የከለከሉትን በመተግበራቸው በህዝቦቻቸው ተወቀሱ የሚል ታሪክ ሠምተን አናውቅም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላም ነብዩላህ ሹአይብን (አለይሒ ሠላት ወሠላም) አስመልክቶ እንዲህ ይላል
" ከእርሱ ወደ ከለከሎኳችሁ ነገር ልለያችሁ አልሻም "(ሁድ 88)

☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በኒ እስራኤሎችን የተናገሩትን አለመተግበራቸውን ለኛ ተግሣፅ ይሆን ዘንዳ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ሲል አስፍሮታል "እናንተ መፀሀፍት የምታነቡ ሆናችሁ ሠዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁ ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁ (የሠራችሁትን መጥፎ) አታውቁምን"(በቀራ 44)

☞ ዛቻን ያዘሉ ማስፈራሪያዎችን በመጠቀም ይህን አይነት ተግባር ይወቅሳል ከነዛ ውስጥ
✔ የአላህን ጥላቻ እንደሚያከናንብ በመግለፅ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ የማትሠሩትን ለምን ትናገራላችሁ ()የማትሠሩትን መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ "(ሠፍ 2 –3)
✔ የዚህን አይነት ተግባር ቅጣቱን በመናገር
የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ ዐለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ "የቂያማ ቀን አንድ ሠውዬ በመላይኮች ተጠፍሮ ይመጣል ወደ እሣትም ይወረወራል የሆድ እቃው በአጠቃላይ ይወጣ እና በእሣት ይዘረገፍና አህያ በወፍጮ ላይ እንደሚዞረው ሠውዬውን ይዞሩታል ከዛም የሣት ባልተቤቶች በሡ ላይ ይሠባሠቡና "አይ አንተ ሠው ምን ሆነህ ነው እሣት የገባህ? በመልካም ታዘን ከመጥፎ ትከለክለን አልነበርን? አዎን በመልካም አዛችሁ ነበር እኔ ግን አልተገብረውም ነበር ከመጥፎም እከለክላችሁ ነበር እኔ ግን እሠራው ነበር "በማለት ይመልሣል

✔ የአላህ ባርያ ሆይ! አስተውል! ከላይ ያለፋት የቁርአን አንቀፅ እና ሀዲስ በአጠቃላይ የነገሩን ግዝፈት ያሣያሉ ተግባሩ ልክ እንደነ ዝሙት ፣ ሪባ እና መሠል ከባባድ ወንጀሎች ተርታ መሠለፋ ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው! ስለዚህ የማንተገብረውን ከመናገር ልንቆጠብ ይገባል

አላህ ሁላችንንም በተናገርነው የምንገኝ ያድርገን!!!

Post a Comment

0 Comments