የ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ክፋት በጥቂቱ
በመጀመርያ…
በህይወትም ያሉ የሞቱትንም የሡና ኡለማዎቻችንን አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው ይህን ኡመት ከጠማማው ኢኽዋነል ሙፍሲዲን ከማስጠንቀቅ እና ከሡ እንዲርቁ ለማድረግ የከፈሉትን መስዋትነት በሠው ልጆች አቅም ለመመለስ የሚሞከር ስላልሆነ አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው ከማለት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም ።… ስቀጥል
በህይወትም ያሉ የሞቱትንም የሡና ኡለማዎቻችንን አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው ይህን ኡመት ከጠማማው ኢኽዋነል ሙፍሲዲን ከማስጠንቀቅ እና ከሡ እንዲርቁ ለማድረግ የከፈሉትን መስዋትነት በሠው ልጆች አቅም ለመመለስ የሚሞከር ስላልሆነ አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው ከማለት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም ።… ስቀጥል
✔ ከዚህ ጀመአ ክፋቶች መካከል የተወሠነውን
1 ዋናው እና የመጀመርያ ክፋታቸው ማህበረሠቡ ተውሒድን እንዳያውቅ እና እንዳይማር ማድረግ ነው ።
አስተውል!!
☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የሠው ልጆችን በአጠቃላይ የፈጠረው እሡን በብቸኝነት እንዲያመልኩት እንደሆነ በማያሻማ ቃል ነግሮን ሣለ "አጋንንትንም ሆነ የሠው ልጅ እኔን በብቸኝነት እንዲያመልኩኝ እንጂ አልፈጠርኳቸውም "
☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የሠው ልጆችን በአጠቃላይ የፈጠረው እሡን በብቸኝነት እንዲያመልኩት እንደሆነ በማያሻማ ቃል ነግሮን ሣለ "አጋንንትንም ሆነ የሠው ልጅ እኔን በብቸኝነት እንዲያመልኩኝ እንጂ አልፈጠርኳቸውም "
☞ እንዲሁም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ መልዕክተኞችን በአጠቃላይ እሡን በብቸኝነት ወደ ማምለክ እንዲሠብኩ ልኳቸው ሣለ "በእርግጥ ወደ ሁሉም ህዝቦች አላህን በብቸኝነት አምልኩ ጣኦትንም ራቁ የሚሉ መልዕክተኞችን ልከናል "
☞ እንዲሁም የሠው ልጆች ስራ ተቀባይነት እና ተመላሽነት የሚመሠረተው የተውሒድ መስተካከል እና መበላሸት ላይ ተመስርቶ ሣለ "(ከሀዲያን) ወደሚሠሩት ስራ ተመለከትን የተበተነ አብዋራም አደረግነው "
★ እነዚህ እና ሌሎች ወሣኝ ነጥቦች ተውሒድን ለመማር እየገፋፉን ሣለ እነሡ ግን አይማሩትም አያስተምሩትም!
2 ትላልቅ ሽርኮች ውስጥ የተዘፈቁ ፣ ቀብር ላይ የሚደፉ፣ ለቀብር የሚሣሉ … ሠዎች መሀል ተቀምጠው ይሸሹናል ፣ ጊዜው አይደለም ፣ አንድነት… ምናምን እያሉ ካሉበት ስህተት አይመልሷቸውም ነገር ግን…
☞ ሽርክ መልካም ስራን በአጠቃላይ ያበላሻል አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በሀዲሠል ቁድስ ላይ እንዲህ ይላል "እኔ ከሽርክም ከአጋሪውም የተብቃቂው ነኝ በስራው ላይ ከኔ ጋር አጋርቶ አንድን ስራ የሠራ ሠው ስራውንም ሽርኩንም እተወዋለሁ "
☞ ሽርክ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በፍፁም የማይምረው የወንጀል አይነት ነው "አላህ በርሡ ማጋራትን አይምርም "
☞ ሽርክ ባለቤቱን ጀሀነም ውስጥ እንዲዘወትር ያደርጋል
★ እነዚህ እና ሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ከመኖራቸው ጋር እነሡ ግን ሽርክ በሚሠራ ማህበረሰብ ስር ተቀምጠው ማህበረሰቡን በሌላ ነገር እየጠመዱ ያታልሉታል
3 ይህ ጀመአ በማህበረሠቡ ውስጥ እስከ ሽርክ የሚያደርሡ ቢድአዎችን በመርጨት ኡማው ሡናን ትቶ በቢድአ ላይ እንዲወድቅ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል "የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ወደራሡ ተመላሽ ነው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ይህን ብለው ሣለ መስራቾቻቸው ግን በነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ድንበር የሚያልፋ ቃላቶችን ገጣጥመው ያዜሙ ነበር ።
4 "በተስማማንበት እንስማማለን በተለያየንበት ኡዝር እንሠጣጣለን " በሚል አዲስ ፈሊጥ የሚከተሉትን የሸሪአው መሠረቶችን ይንዳሉ
☞ በመልካም ማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከል "(ለነብያቶች) ከተስወጡ ህዝቦች መካከል በላጭ ህዝቦች ሆናችሁ በመልካም ታዛላችሁ ከመጥፎ ትከለክላላችሁ "ይሆን በላጭ ያሰኘው ጉዳይ በመልካም ማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከል ሆኖ ሣለ እነሡ ግን ይህን ኡዝር በመሠጣጠት ይንዱታል
☞ ወላዕ እና በራዕ የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም "ቢድአ የሚሠራን ሠው ያስጠጋ አላህ ከራህመቱ ያባረው " እያሉ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላም "ህዝቦችን በአላህ እና በመረሻው ቀን የሚያምኑ ሆነው ከአላህና ከመልዕክተኛው ጠላት ጋር ሢወዳጁ አታገኛቸውም "እያለን እነሡ ግን በአላህ ዲን ላይ አዲስ ነገር ከሚፈጥሩ ሠዎች (ሙብተዲኦች) ጋር እንዲሁም ከከሀዲያን ጋር ሢተሻሹ ይኖራሉ ሌላው ከንደዚህ አይነት ሠዎች እንዳይርቅ እና ለይቶ እንዳያውቃቸው የበኩላቸውን ይወጣሉ ።
5 የሙስሊሙን ማህበረሠቡ ወደ ረብሻ እና አመፅ በመቀስቀስ የሙስሊሙን ደም ያለ ምንም ጥቅም ያስፈስሳሉ: ለዚህ ማሣያ ደግሞ በአረቡ ክፍል የተነሡት የመፈንቅለ መንግስት ትዕይንቶች በአጠቃላይ በኢህዋነል ሙስሊሚን ጠንሣሽነት የተቀነባበሩ እንደነበር ግልፅ ነው ። የሚገርመው ደግሞ ጨንስሰው እነሡ ይሸሻሉ ተራው ማህበረሰብ ሲገደል እና ሲቆስል እነሡ ከነ ቤተሠባቸው ሠላም የሆነች ሀገር ተቀምጠው" ተጋደል ሸሒድ ነህ" እያሉ ያበረታታሉ ።
6 ተውሒድ እና ሡና የሚያስተምሩ የሡና ኡለሞችን በማብጠልጠል የተካኑ ናቸው ።
7 በኡመራዎች ላይ ምላሣቸውን ያረዝማሉ የኡመራዎችን ነውር ይከታተላሉ የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ግን "ንብረትህንም ቢቀሙህ ቢደበድቡህም ስማቸው ታዘዛቸው "ብለው ነበር እነሡ የመልዕክተኛው ንግግር ምንም ሣያግዳቸው ከአዋቂ ተብዬዎች እስከ ሙቀሊዳቸው ድረስ ኡመራዎችን በመዝለፍ እና በመፈላፈል የተመረቁ ናቸው ። …
✔ ይሄ በማህበረ ሠቡ ስር ከሚጥሉት በጣም ጥቂቱ ጥፋት ነው ሌሎችም በርካታ ክስረቶችን ያስከትላሉ ከዚህ አይነት የጥፋት ስብስብ ልንርቅ እና ልንጠነቀቅ ይገባናል ።
0 Comments