Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የልብ በሽታዎች እና መድሀኒታቸው!!


የልብ በሽታዎች እና መድሀኒታቸው!!

በሽታ ሁለት አይነት ነው!!!

አንደኛው በሽታ አካላዊ በሽታ ሲሆን ይህ የበሽታ አይነት አካልን ከማሣመም ያለፈ ምንም አይነት ችግር ተከትሎት የማይመጣ ቀላል የበሽታ አይነት ነው ሆኖም ይህ በሽታ እንደ ሚከሠትበት ሠውዬ ሁኔታ የአመጣጡ መንስኤ ከሶስት አንዱ ሊሆን ይችላል 
1 ፈተና ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ምርጥ የሆኑ ባርያዎቹን የተወኩል እና የእምነታቸውን ደረጃ ለሠዎች ግልፅ በሚሆን መልኩ በተለያዩ የፈተና አይነቶች ይፈትናል በፈተናው የመረጣቸው ባሮቹ ተበጥረው ከላይ ሲቀሩ የተቀሩት ደግሞ አግድም ይሽቆለቆላሉ በዚህ አጥፊው ከአሣማሪው ይለያል ። ከነዛ ፈተናዎቹ መካከል አንዱ በሽታ ነው ። ይህን ፈተና ላለፋት ብስራት ሲኖራቸው ለወደደቁና ለተሽመደመዱ ደግሞ ከባድ የሆነ ቅጣትን አዘጋጅቷል

2 አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ለሚወደው ባርያው ጥፋቱን ሊያብስለት ሲፈልግ በተለያዩ ችግሮች ይነካዋል ከነዛ ውስጥ አንዱ በሽታ ነው ።

3 እንደ ቅጣት እና ለሌሎችም እንደ መቀጣጫ ሆኖ ይመጣል አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እሡን ለሚያምፁ ሠዎች መቀጣጫዎችን አዘጋጅቷል ከነዛ ውስጥ አንዱ በሽታ ነው ።

ከሦስቱ በአንዱ ምክንያት ሊከሠት ይችላል ሆኖም ግን ይህ የበሽታ አይነት አካል ከመጉዳት ያለፈ ምንም አይነት ችግሮች ተከትለውት አይመጡም ይህን ስል በአካላዊ በሽታ ምክንያት እምነት ሊነጠቅ አይችልም ብዬ ሙሉ ለሙሉ መቁረጤ አለመሆኑን እንድትረዱልኝ እሻለው ምክንያቱም በአካላዊ በሽታ #ምክንያት እምነቱን የሚያጣበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል እሙን ነው ግን በሽታው በራሡ አካል ከመጉዳት ያለፈ እምነት ላይ የሚፈጥረው ምንም አይነት ችግር የለም! በተጨማሪም ይህ የበሽታ አይነት ከአላህ ፍቃድ ቡሀላ በዘርፉ ባልተቤቶች ምክንያትነት በቀላሉ ሊታከም እና ሊድን የሚችል የበሽታ አይነት ነው ። ላወራ ያሰብኩት ስለዚህኛው የበሽታ አይነት አይደለም ሆኖም ስለዚህኛው የበሽታ አይነት በራሱ ርዕስ በአላህ ፍቃድ ይዤ እመጣለሁ አሁን ወዳሠብኩት ልግባ

ሁለተኛው የበሽታ አይነት እንማንኛውም በሽታ ላብ ተገብቶ የማይመረመረው የቀልብ በሽታ ነው ይህ የበሽታ አይነት ለማከም እጅጉኑ የሚጠና የበሽታ አይነት ነው ለማከሙ ይክበድ እንጂ አይታከምም ማለት ግን አይደለም ቀልብ በሁለት ነገሮች ይታመማል በሹበሀ (ሸክ) እና በሸህዋ በሁለቱንም በተናጠል እንመልከት

☞ሹብሀ (ሸክ) ፦ ይህ የቀልብ በሽታ ከቀልብ በሽታዎች ከባዱና ለመታከምም እጅጉኑ አዳጋች የሆነው የቀልብ በሽታ አይነት ነው ። የዚህ በሽታ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ።

↪ ንፍቅና (ጥሩን ይፋ አድርጎ ሸሩን (መጥፎን) መደበቅ) ይህ ሁለት አይነት ነው
★ኒፋቁል አስገር (ትንሹ የንፍቅና አይነት) ይህ የንፍቅና አይነት ከተግባር ጋር ግኑኝነት ያለው ሢሆን ውሽታምነት ፣ ቀጠሮን ማፍረስ ፣አለታመን … እና መሠል አፍራሽ ስነ ምግባሮች መገለጫዎቹ ናቸው ።ባለቤቱን ከእስልም አያስወጣውም ግን በእምነቱ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ያሳድራል ።

★ ኒፋቁል አክበር (ትልቁ የንፍቅና አይነት ) ይህ የንፍቅና አይነት ከእምነት ጋር ግኑኝነት ያለው ሢሆን ክህደትን ደብቆ እምነትን በማወጅ በሙስሊሞች መሀከል ልዩነትን በመፍጠር ፣ የሙስሊሞችን ሚስጢር ለጠላት አሣልፎ በመስጠት… እና መሠል የተልካሻነት መገለጫዎች ሊገልፁት ይችላሉ ባልተቤቱ ከእስልምና ይወጣል


በሹብሀ ከተለከፋ ጀመአዎች መካከል ዋነኛዎቹ መናፍቃን ናቸው ማለት ነው

↪ ሸክ (ተጠራጣሪ) በልቡ ላይ ሹብሀ ያለበት ሠው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በቁርአን መልዕክተኛው በሀዲስ ያፀደቁትን ሀቅ እውነት ብሎ ከመቀበል ፈንታ እውነት በመሆኑ ላይ ይጠራጠራል ።

↪ ሡአ ዘን (መጥፎ ጥርጣሬ) አሁንም በሹበሀ ቫይረስ የተጠቃ ልብ ባለቤት በአላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ላይ ልቡ መጥፎን ከመጠርጠር አትወገድም ።

↪ ሪያእ (ታይታ) አሁንም በልቡ ላይ የሹብሀ ችግር ያለበት ግለሠብ ለአላህ ተብለው በሚሠሩ ስራቸው የሠዎችን አድናቆት እና ታይታ ይከጅላል ።

↪ ቀልቡ በሹበሀ የተጠቃ ሠው በሠዎች ላይ ድንበር ያልፋል ፣ በሚያስከፍረውም በማያስከፍረው ከእስልምና ያባርራል ፣ ከሠለፎች መንገድ የማያስወጡ ጥቃቅን ነጥቦችን በመያዝ ከመንሀጅ ያባራል ። እና ሌሎችም መገለጫዎች አሉት ።

♂ ከላይ የተጠቀሱት ነገራቶች በአጠቃላይ በሹበሀ በተጠቃ ሠው ላይ የሚከሠቱ ሢሆኑ ከነርሡ ስር ከሀዲ፣ ሙብተዲእ ፣ አሲ (ወንጀለኛ) የሚያሠኙ መኖራቸው የነገሩን ከባድነት ያመላክታሉ ።

☆መድሀኒቱ ፦ በዚህ በሽታ የተጠቁት ሠዎች የበሽታቸው ምልክት አይነት ስለሚለያይ እና በመሀከላቸው ያለው ልዩነት ሠፊ የሆነ በመሆኑ እና ከበሽተኞቹ ስር ከበሽታው መላቀቅ የማይፈልግ በመኖሩ ምክንያት በዚህ በሽታ የተጠቃን ሠው ማከም እጅጉኑ ከባድ ነው ። ሆኖም ይህን በሽታ ያክማሉ ያልኳቸውን ልጥቀስ

☞ ለበሽታው ዋነኛ መንስኤ የሆነው ነገር አለማወቅ ስለሆነ ሸሪአዊ እውቀትን መንገዱ ትክክለኛ ከሆነ ምሁር መማር

☞ ልባችን ውስጥ የተፈጠረውን ወይም በሠዎች አማካኝነት ወደ አእምሮአችን የገባውን አደናጋሪ (አምታች) ጥያቄ የሸሪአ እውቀት ወዳላቸው ሠዎች ሠዎች በማስጠጋት በማናውቀው ነገር ከመወጠር ነፃ መሆን

☞ የራስን አመለካከት ወደ ጎን በመተው ቁርአን እና ሀዲስን ሠለፎች በተረዱት መንገድ መረዳት እና ሌሎችም

✔ ሸህዋ ፦ ይሄኛ የበሽታ አይነት እንደመጀመርያው (ሹብሀ) ከባድ አይሁን እንጂ ቀላል የማይባል የበሽታ አይነት ነው ።ይህን ለማከም እንደ መጀመርያው ከባድ ላይሆን ይችላል ። የዚህ በሽታ መገለጫዎች እጅጉኑ በርካታ ናቸው ከነዛ ውስጥ
↪ልታይ ልታይ ባይነት
↪ በአጅ ነብ ሤት መፈተን
↪ በሀምር በቁማር መፈተን … በአጠቃላይ አላህ ለሙዕሚኖች እንዲርቁት ያዘዛቸው ወንጀሎች በአጠቃላይ እነሡን መዳፈር እዚህ ውስጥ ይካተታል ይህ የበሽታ አይነት ሙዕሚን (ሙወሒድ) በሆነ ሠው ላይ ሊከሠት ይችላል ። እንደሚታወቀው ነፍስያ ወደ መጥፎ ፀያፍ ነገር ነው የምታዘው እሦን የተከተላትን በአጠቃላይ ይዛ ወደ ገደል ትገባለች እኛም ለነፍስያችን ማሰሪያ ልጓም ካላበጀንላት ወደ ገደሉ ከመግባት ቅሮት የለንም ።

☆መድሀኒቱ ፦ ከላይ እንዳሣለፍ ነው ይህ የበሽታ አይነትን ለማከም እንደ መጀመርያው ከባድ አይደለም ሆኖም ግን ከራሱ አንፃር ግን ቀላል የሚባል ነገር አይደለም ። የተወሠኑ መድሀኒቶችን ልጥቀስ

☞ ዱአ ፦ በሸህዋ ማዕበል ተመታ በወንጀሎች ላይ በመዘውተር እና በሡና ላይ በመሠላቸት የተጠቃች ልብን ይዞ የሚዞር የአካል ባለቤት አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን አጥብቆ ሊማፀነው ግድ ይለዋል ።
☞ ትግል ማድረግ ፦ በመጥፎና እራሷን ወደ መከተል የምትጎትተውን ነፍስያ ሊታገላት ይገባል ። ይህ ከትግሎች ሁሉ ከባድና ተወዳጁ የትግል አይነት ነው ።

☞ መጥፎ ጓደኛን መራቅ ፦ ነፍስያ እኛን ለማሸነፍ በምታደርገው ጥረት ላይ የተለያዩ መሣሪያዎችን ትጠቀማለች ከነዛ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛ መሣርያዋ ከመጥፎ ጓደኛ ጋር ማስተዋወቅ ነው ። ነፍስያውን ድል ማድረግ የሚሻ ሠው ከመጥፎ ጓደኛ ሊርቅ ይገባዋል ።

☞ ሞትን ማስታወስ ፦ ነፍስያ ወደ ወደ ወንጀል እንድትነሣሣ ከምታወርግባቸው መንገዶች መካከል ዘላለም እንደምትኖር እየነገረች "በህልም ክትፎ " እያሞኘች ነው ስለዚህ እሦን ለመጨፍለቅና እሦን ከመከተል መቆጠብ የፈለገ ሠው ሞትን በቀን በርካታ ግዜ ሊያስታውስ ይገባል

☞ አኼራ ላይ የሚከሠቱ ነገራቶችን አንድ በአንድ ማስታወስ ሒሣብ ፣ ሢራጥ ጀነት ፣ጀሀነም… እና ሌሎችም አኼራ ላይ የሚከሠቱ እጅጉኑ አስፈሪ የሆኑ ክስተቶችን ማስታወስ የነፍስያን ክፋት ሊያኮላሸው ይችላል ።

☞ ጥሩ አቀማማጭን መቀማመጥ እና ሌሎችም ከዚህ ችግር የሚያወጡ ፍቱን የሆኑ መድሀኒቶችን ተጠቅመን ቀልባችንን ልናክም ይገባናል !!!

አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ከሸህዋም ከሹበሀም እንዲጠብቀን እማፀነዋለሁ!!!

Post a Comment

0 Comments