Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የነገዋ የኢድ ዋዜማ የዐረፋ እለት ትሩፋቶች


የነገዋ የኢድ ዋዜማ የዐረፋ እለት ትሩፋቶች

☞ ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ

♻ የዐረፋ ቀንን መፆም የሁለት ዐመታት ኃጢኣትን ያስምራልና ካሁኑ ኒያችንን እናስተካክል።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
🔸 قال الرسول ﷺ :
" صيامُ يومِ عرفةَ ، أَحتسبُ على اللهِ أن يُكفِّرَ السنةَ التي قبلَه، والسنةَ التي بعده "
«የዐረፋ እለት ፆም… ከዚህ አመት ቀድሞ ያለውንና የቀጣዩን ኣመት እንደሚያስምርልን ከአላህ ኣስባለሁ።» ብለዋል። 【ሰሂሁ-ሙስሊም: 1162】

ይህንን በማስመልከት ሸይኽ ሷሊህ አልዑሰይሚን [ረሂመሁላህ] “የዐረፋ እለት ፆም ያለፈው አመትንና የቀጣዩ አመትን ያስምራል። ሲባል ጥቃቅን ሀጢኣቶችን ብቻ የሚመለከት ነው። ከባባዶቹ ወንጀሎችን በተመለከተ የግድ ንስሃ መግባት ተውበት ማድረግ ይገባል።” ብለዋል።
【ፈታዋ ኑ…ሩን አለ-ድ'ደርብ: የካሴት ቁጥር ☞328】

በመሆኑም በዚሁ አጋጣሚ ከሐጢኣቶቻችን በመፀፀት ወደ ጌታችን በመመለስ ተውበት ከማድረግ ጋር የነገዋን የአረፋ እለት በፆም እናሳልፍ። የሰው ልጆች ነንና ከወንጀል ስለማንፀዳ ወንጀሎቻችንን እናራግፍ።

♻ የዐረፋ እለት ዱዓእ ከሌላው ቀን የተሻለ የሆነ ዱዓእ ነውና እጆቻችንን እናንሳ።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
🔸قال الرسول ﷺ :
" خيرُ الدعاءِ دعاءُ يومِ عرفَةَ وخيرُ ما قلْتُ أنا والنبيونَ من قبلي لا إلهَ إلَّا اللهُ وحدَه لا شريكَ له له الملكُ وله الحمدُ وهو على كلِّ شيءٍ قديرٌ "

«ከዱዓኦች በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው። እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩት ነቢያት ከተናገሩት መካከል በላጩ ቃል "ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም… እሱም ብቸኛና አጋር የሌለው ነው … ንግስናም ምስጋናም ለሱ የተገባ ነው … እሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ የሆነ ነውና።" የሚለው ቃል ነው።» ብለዋል።
【ሰሂሁ-ቲርሚዚይ: 3585, አል-አልባኒም ሀሰን ብለውታል】

ሸይኽ ዶክተር ሷሊህ ፈውዛን አል-ፈውዛን [ሀፊዘሁላህ] ስለዚህ ዱዓእ ሲያስረዱን☞
«የዐረፋ እለት ዱዓእ ሐጃጆችንም ሀጅ የማያደርጉትንም የሚያጠቃልል ነው። የሀጃጆች ግን ለየት ይላል። ምክንያቱም እነሱ ብልጫ ባለው ስፍራ ኢህራም ለብሰው በዐረፋ ምድር ቆመዋልና።» ብለዋል።
ከድምፃቸው በቀጣዩ ሊንክ ያድምጡ⇣
http://www.alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/240.mp3

♻ የዐረፋ እለት ከእሳት ነፃ የሚኮንበት ቀን ነው። በእለቱም በዐረፋ ምድር ለተገኙት ሀጃጆች ብቻ ሳይሆን ለመላው ሙስሊም ከእሳት ነፃ መውጫ ነውና ከወዲሁ በተውበትና በዒባዳ ነቃ እንበል።

ነቢዩ ﷺ
🔸قال النبي ﷺ :
" ما من يوم أكثر من أن يعتق الله فيه عبدًا من النار من يوم عرفة، وإنه ليدنو ثم يباهي بهم الملائكة فيقول: ما أراد هؤلاء"

«አላህ ከባሮቹ መካከል በብዛት ከእሳት ነፃ ከሚያደርግባቸው እለታት ከዐረፋ እለት የበለጠ የለም። አላህም በእለቱ ወደነሱ ይቀርባል። መላኢኮቹንም እነዚያ ሰዎች ምን ፈለጉ ይላቸዋል።» ብለዋል
【ሰሂሁ-ሙስሊም: 1348】

ልእለ ሀያሉ ጌታችን የያንዳንዳችንን ፍላጎትና አላማ እያወቀ ለመላእክት ጥያቄ ማቅረቡም በእለቱ የሚለምኑትን ባሮቹን ለመላእክቶች ለማሳወቅና ለማስመስከር ነው።

አል ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር [ረሂመሁላህ]
«የዐረፋ ቀን ከእሳት ነፃ የሚወጣበት ቀን ነው። አላህ (በሀጅ ተግባር) በዐረፋ ምድር የቆመን ሰው ከእሳት ነፃ ይለዋል። በዐረፋ ምድር ያልተገኘን በተለያዩ ሀገራት የሚገኙትንም ሙስሊሞች በእለቱ ከእሳት ነፃ ያደርጋቸዋል። ለዚህም ሲባል ነው ከዐረፋ እለት ቀጥሎ ያለውን ቀን በሀጅ ላይ ለተሳተፉትም ላልተሳተፉትም በያሉበት ሀገሮቻቸው ለመላው ሙስሊሞች የዒድ ቀን ያደረገው። ይህም ከእሳት ነፃ በመውጣቱና ከአላህ ምህረትን በማግኘቱ ረገድ ሁሉም ስለሚጋሩ ነው።» ብለዋል።【ለጧኢፉል-መዓሪፍ… ሊኢብኒ-ረጀብ አል-ሀንበሊይ】

---------
ዚልሂጅ'ጃ ምሽት 09/12/1436
September 23/09/2015
www.fb.com/tenbihat

Post a Comment

0 Comments