ለሴቶች፤ ፀጉርን ለውበት ማሳጠር የተፈቀደ ነው
ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት
www.fb.com/tenbihat
www.fb.com/tenbihat
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه أما بعد:
⇨ ሙስሊሟ ለባልዋ ለመዋብ ከፈለገች ወይም ፀጉርዋ ረዝሞ ለእንክብካቤ ካስቸገራት፤ ወይም ለሌላ በሸሪዓ ለተፈቀደ አላማ ፀጉሯን ማሳጠርዋ በትክክለኛው የኡለማዎች አቋም መሰረት የተፈቀደ ነው።
ምክኒያቱም፤ የሰዎች ተለምዷዊ ወጎችና ልማዶች በሸሪዓዊ መረጃ ክልክልነታቸው ካልተገለፀ ሀራም አይሆኑም።
⇨ ሴቶች ፀጉራቸውን ማሳጠራቸውን ሀራም የሚያደርግ ሸሪዓዊ መረጃ ደግሞ የለንም። እንደውም እንደሚፈቀድ የሚያሳዩ መረጃዎች ተላልፈውልናል።
☞ ይህም ተከታዩ ሀዲስ ነው፤
عن أبي سلمة بن عبد الرحمن رحمه الله قال: ( كَانَ أَزْوَاجُ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَأْخُذْنَ مِنْ رُءُوسِهِنَّ حَتَّى تَكُونَ كَالْوَفْرَةِ)
رواه مسلم (320)
رواه مسلم (320)
والوفرة : قيل : الشعر الذي يزيد على المنكبين قليلا . وقيل : يصل إلى شحمة الأذنين.
▲ አላህ ይዘንላቸውና አቡ ሰለማህ ቢን አብዲረህማን እንዲህ ብለዋል፤
«የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ፀጉራቸውን ለትኬሻቸው እስኪቀርብ ወይም እስከ ጆሯቸው ጫፍ አሰኪደርስ ያሳጥሩት ነበር» መስሊም ዘግበውታል
«የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ፀጉራቸውን ለትኬሻቸው እስኪቀርብ ወይም እስከ ጆሯቸው ጫፍ አሰኪደርስ ያሳጥሩት ነበር» መስሊም ዘግበውታል
☞ አል ኢማሙ ነወዊ ሀዲሱን ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፤ «ሴቶች ፀጉራቸውን ማሳጠራቸው የተፈቀደ መሆኑን ያሳያል» የሙስሊም ማብራሪያ 4/5
ለሴቶች ፀጉርን ማሳጠር ሀራም የሚሆነው በተከታዮቹ ሁኔታዎች ነው፤
① ከካፊሮች እና የአላህን ህግጋት ከሚጥሱ ፋሲቅ ሴቶች ጋር ለመመሳሰል ከሆነ ወይም ካመሳሰለ፤
② ባእድ ለሆኑ ወንዶች የሚዋቡና የሚጋለጡ ከሆነ
③ አቆራረጡ የወንዶች ስታይል ከሆነ
④ የሚያሳጥረው ባእድ ወንድ ከሆነ
⑤ ከባል ፍቃድ ዉጪ ከተፈፀመ
∴ በነዚህ ሁኔታዎች ሀራም መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም
⇒ ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፤ « ሴት የኃላውን የፀጉሯን ክፍል አሳጥራ የጎኑን መተው አይፈቀድላትም፤ ምክኒያቱም መልክ ማበላሸት በውበቷ መጫወት ነው። ከእንስሳት እና ከካፊር ሴቶች ጋር መመሳሰልም ነው። በእንስሳት ወይም በካፊር ሴቶች ስምና ሰታይል መቆረጥም አይቻልም። ለምሳሌ፤ ዲያና ቁርጥ፤ አንበሳ ቁርጥ፣ የአይጥ ቁርጥ፤ እራስን ከኩፋሮች እና ከእንስሳት ጋር ማመሳሰል ሀራም ነው። ውበት በሆነው የሴቶች ፀጉር መጫወትም እና ነው።» ፈታዋ አልመርአቲል ሙስሊማህ 2/516-517
☞ ኡለማዎች፤
ለሴቶች ፀጉርን ማሳጠር ክልክል ሊሆን የሚችልባቸውን ሁኔታዎች አስመልክቶ በጣም በማሳጠር ከወንዶች ጋር መመሳሰል ወይም ከካፊርና ከዱርዬ ሴቶች ጋር መመሳሰላቸው ሀራም እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
ለሴቶች ፀጉርን ማሳጠር ክልክል ሊሆን የሚችልባቸውን ሁኔታዎች አስመልክቶ በጣም በማሳጠር ከወንዶች ጋር መመሳሰል ወይም ከካፊርና ከዱርዬ ሴቶች ጋር መመሳሰላቸው ሀራም እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
✔ የቀድሞው ሙፍቲ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ኢብኑ ባዝ አላህ ይማራቸውና ተከታዩን በለዋል፤
«ሴቶች ፀጉራቸውን ማሳጠራቸውን አስመልክቶ ምንም አይነት ክልከላ አናውቅም! የተከለከለው መላጨቱ ነው። ፀጉርሽን መላጨት አይፈቀድልሽም፤ ነገር ግን እርዝመቱን ብዛቱን መቀነስ ምንም ችግር የለውም። ነገር ግን አንቺና ባልሽ በምትወዱት መልኩ ከእሱ ጋር ተስማምተሽ መሆን አለበት፤ እንደዚሁ ከካፊር ሴቶች ጋር መመሳስል አይኑርበት። ረጅም ሆኖ ከተተወ የመታጠብና የማበጠሩ ሀላፊነት ይጫንባታልና ከእርዝመቱ ወይም ከብዛቱ ብትቀንስ ምንም የለበትም የለውም። እንደዚሁ የተወሰነውን ማሳጠር አርሷ የምትወደውን ወይም ባሏ የሚወድላትን ዉበት የሚሰጣት ከሆነ ምንም የሚከለክል መረጃ አናውቅም። ከበሽታ ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር ፀጉርን በሙሉ መላጨት አይፈቀድም። ወቢላሂተውፊቅ!»
ፈታዋ አልመርአቲል ሙስሊማህ 2/515
✔ ታላቁ ሙሀዲስ ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩዲን አልአልባኒ፤
«ለሴቶች ፀጉርን ማሳጠርን አስመልክቶ፤ የምታሳጥርበት አላማ ይታያል፤ ከካፊር ወይም የአላህን ህግ ከሚጥሱ ፋሲቅ ሴቶች ጋር ለመመሳሰል ከሆነ በዚህ አላማ መቆረጧ አይፈቀድም። የባለቤቷን ፍላጎት ለማሟላት ወይም (ቀለል እንዲላት) ፀጉሯን ለመቀነስ ብታሳጥረው ምንም የሚከለክል ነገር አለ ብዬ አላምንም። በሙስሊም ዘገባ እንደተላለፈው የነብዩ ባለቤቶች ፀጉራቸውን ያሳጥሩ ነበር »
የሸይኽ አልባኒ 1413-1415 ዓ.ሂ አል አሳላህ መፅሔት ፈትዋዎች ጥንቅር ጥያቄ ቁ.2
✔ ታላቁ የፊቅህ ሊቅ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል ዑሰይሚን እንዲህ ብለዋል፤
«ሴት ፀጉሯን ማሳጠሯን አንዳንድ ኡለማዎች ጠልተውታል፤ አንዳንዶቹም ሀራም ነው ብለዋል፤ ሌሎች ደግሞ የተፈቀደ ነው ብለዋል፤ ይሁንና፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ውዝግብ እስካለ ድረስ ጉዳዩን ወደ ቁርአንና ወደ ሱና እንመልሰዋለን፤ በበኩሌ እሰከዚህ ሰአት ድረስ ሴት ልጅ ፀጉሯን ማሳጠሯን የሚከለክል መረጃ አላውቅም። ስለዚህ መሰረታዊ ፈርዱ የተፈቀደ መሆኑ ነው። የአካባቢውን ልማድም መሰረት ያደረገ ይሆናል፤ ድሮ ድሮ ሴቶች የፀጉራቸውን መርዘም ይፈልጉ ነበር፤ እንደውም በፀጉራቸው ይኮሩ ነበር። ለሸሪአዊና ተጨባጭ ለሆኑ ምክኒያቶች ካልሆነ በቀር አያሳጥሩም ነበር። ነገር ግን አሁን ሁኔታዎች ተቀያይረዋል፤ "ሀራም" ነው የሚለው አቋም ደካማና ተቀባይነት የሌለው ነው። የተጠላ "መክሩህ" ነው የሚለውም ቢሆን መረጃዎችን ማጤንና ይበልጥ ማጥናት ያስፈልገዋል። ለሸሪዐዊ መረጃዎችና መሰረታዊ ምርሆዎች የቀረበው የተፈቀደ "ሙባህ" ነው የሚለው አቋም ነው» ፈታዋ ኑሩን አለደርብ ካሴት ቁ.336

ሸይኽ ኡሰይሚን ይህንን ካሉ በኃላ አስከትለው ከላይ የተጠቀሰውን ሀዲስ አውስተዋል።
አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው!!
ሀሳቡ በከፊል የተወሰደው ከአል ኢስላም ሱአሉን ወጀዋብ ቁጥር
ምላሽ 139414 ነው።
ምላሽ 139414 ነው።
0 Comments