Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይድረስ ላንች በኢስላም ውስጥ ለምትኖሪው በሂጃብሽ ተጎናፅፈሽ ለኮራሽው የአንችነትሽ መለያሽን ላሳየሽው




🔮ለውዷ እህቴ🔮
✒ Ruqeyah Abdellah


ይድረስ ላንች በኢስላም ውስጥ ለምትኖሪው
በሂጃብሽ ተጎናፅፈሽ ለኮራሽው
የአንችነትሽ መለያሽን ላሳየሽው

አዎን እህቴ!
ብትኮሪም ይገባሻል 
ኢስላምሽ ነው ያወጀልሽ ነፃነትሸን፣
ሠማያዊ ህግ አውርዶልሽ አፅድቆልሽ ሰውነትሽን
ያ ኔ እህቴ ነፃ አወጣሽ
ያለ ወንጀል ከመቀበር፣
ከመወገር ከመገደል ከመወርወር
ከእንስሳ በታች ከሚያስብሽ ህ/ሰብ ያዳነሽን
ተቀበይው እስልምናን አውለብልበሽ ባንዲንራሽን
ወደሽ ፈቅደሽ ህግጋቱን ለመፈፀም እምነትሽን፣
እናም አንች ይህን ግፍ አይተሽ
በመነሳት ቆርጠሽ ታጥቀሽ
ለወላጆች ታላቅ ሆነሽ
ለባልሽም የደስታ ምንጭ ትሆኛለሽ
አክብረሽው ራስሽን አስከብረሽ
ፍቅር ሰጥተሽ ተቀብለሽ
ለእርሱ ብቻ ትዋብያለሽ አምረሽለት
ልጆችንም ወልደሽለት
ተንከባክበሽ በማሳደግ ለኢስላምም ለማበርከት
አስተምረሽ ተቆጣጥረሽ
ቃልን ገብተሽ ትሰሪያለሽ ፈጣሪሽን ለማስደሰት
ቤትሽንም በመጠበቅ ከፍቃዱ ሳትወጭ
ቆጣ ሲልሽ በመታገስ፣በማባበል ሲከፋብሽ
ይቅር ብለሽ ሁሉን ትተሽ
ሲያማክርሽ ቦታ ሰተሽ 
ጊዜ ወስደሽ እሱን ብቻ አስቀድመሽ
አይዞህ ብለሽ ምርኩዝ ከሆንሽ
መፍትሄና የእፎይታው ምንጭ ትሆኚያለሽ ።
አቅሙን አውቀሽ ላኗኗርሽው
የሰውን ቤት ላላየሸው
የጀርባ አጥንት ለቤተሰብ የሆንሻቸው
ዝርያሽን አሳምረሽ ኮትኩተሽም ላሳደግሽው
ሃቃቸውን አሳውቀሽ እንደ ኢስላም ላኖርሻቸው
ውድ ትውልድ አበርክተሽ ኢስላምንም ላኮራሽው፣
ከጌታሽ ዘንድ ብቻ ምንዳሽንም ለፈለግሽው
አላህ ይስጥሽ የፈራሽው፣ ያከበርሽው
በእጥፍ ድርብ ይመንዳሽም ያስደሰትሽው
ለምን ይሆን ይህ መሆኑ ግን ታውቂያለሽ?
ያ ኢስላም ነው ከዙፋኑ ያስቀመጠሽ
የሂጃብ ዘውድ አስለብሶ ከፍ ያረገሽ
እርሱ እኮ ነው ያስተማረሽ ያስደነቀሽ
መብትሽን አሳውቆ በቁርአኑ ስምሽን ጠርቶ ያስከበረሽ
እናም እቴ በሰው በኩል የሚሰጠሽ 
መብት ብለው የሚያዜሙት እንደማይጠቅምሽ 
አንችም ቢሆን አውቀሽ አምነሽ
ነፃ እውጭ ነን ለሚሉ አላዛኞች አትስሚያቸው
አይበጁሽም እርቃንሽን ለማስኬድ ነው ድካማቸው
ምቀኝት በሽታቸው የአውሬነት ስሜታቸው
አይሎና በርትቶባቸው
ተገዥ ሊያደርጉሽ ነው ሩጫቸው
ይህን አውቀሽ ራቂያቸው
ባሪያ መሆን አልፈልግም ብለሻቸው
አርአያሽን በተግባርሽ አሳያቸው
መብትሸ በኢስላም ከአርሽ ላይ በፈጣሪሽ 
ያለ አድልዎ መታወጁን ንገሪያቸው አስረግጠሽ።

⌚ ሸዋል 27/10/1436
🔚ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!