📝 ኢስላማዊ የልጆች አስተዳደግ ስርዓት!
🔮ሙስሊም ሴት ከልጆቿ ጋር 🔮
ልጆች ማለት የአይን ማረፊያዎች፣ የአብራክ ክፋዮች የቅርቢቱ አለም ጌጦች ናቸው:: እነርሱን በትክክለኛ እምነትና ሰናይ ስነ ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ የወላጆች ግዴታና ሃላፊነት ነው:: ይሁንና ይህ ግዴታና ሃላፊነት እንዳለ ሆኖ እናት ግን በልጆችዋ ህይወት ውስጥ ከአባት በበለጠ ሁኔታ ትልቅ ሚና ትጫወታለች:: አባትን ስንወስድ የልጆችን አስፈልጎት ለማሟላት ደፋ ቀና እያለ በውጪ ያሳልፋል:: በተቃራኒው እናት ግን ይህን ስታጠባ፣ ያንን ስታበላ ባጭሩ ከልጆችዋ ጋር ረጅም ግዜን ታሳልፋልች::
እንግዲህ ይህንና መሰል ሁኔታዎችን ተንተርሶ ሙስሊሟ ሴት ከወንዱ በተለየ መልኩ በልጆች አስተዳደግ ላይ ያላትን ሃላፊነት ማወቅ አያዳግትም:: እርሷ የትክክለኛ እምነትና ስነምግባር ባለቤት መሆኗ ልጆቿ የርሷ ኮፒ ሆነው እንዲወጡ ያደርጋቸዋል:: በተቃራኒው ከሆነ ውጤቱም እንደዛው ይሆናል፡፡
ልጆች በተፈጥሯቸው የሚነገራቸውን ነገሮች ከመያዝ ጋር በእይታ የሚቀስሙት ነገር ላይ ግን የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ:: እናም ሙስሊም ሴት እንደናትነቷ ከእነርሱ ጋር በሚኖራት የዕለት ተዕለት ቆይታ ትክክለኛ እምነትና ሰናይ ስነም ምግባርን ልታንጸባርቅላቸው ይገባል:: እያንዳንዱን እንቅስቃሴዋን ከአላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ጋር ያስተሳሰረች ሆና ሊያይዋት ይገባል:: ሁሌም አላህን ተገዢና አመስጋኝ፣ ሰላተን አስተካክላ ሰጋጅ፣ሂጃቧ ዝንፍ የማይልና ወዘተ ከሆነች ልጆቿም በዚህ እየተቀረጹ ይሄዳሉ:: ከዐቂዳ ጀምራ “ተውሂድን”፣ “ፊቂህን”፣ “ቁርዓንን” “ሃዲስን” እና ከመሳሰሉት አጠርና ቀለል ያሉ ጥያቄና መልሶችንም ከሽልማት ጋር በማዘጋጀት በእርሱ ቀላል የማይባል ምልመላ ልትሰጣቸው ትችላለች::
አንዳንድ ወላጆች የሚያጠፉት ትልቅ ጥፋት አለ። እርሱም ገና ልጆች ናቸው ምንም አያውቁም እያሉ ሌሉትንም ቀኑንም በመጫወት ብቻ ሲያሳልፉ ዝም ይሏቸዋል:: ታዲያ አጋጣሚ ሆኖ ወጣ ብለው ሲመለሱ የማይሆን ነገር ሲናገሩና ሲሰሩ ሲያይዋቸው ለቁጣና ለዱላ ይጋበዛሉ:: መሆን የነበረበት ግን እነርሱ በሚገባቸው ቌንቌ መጥፎና ደጉን ማብራራት ነው::
❗ስንት ልጆች አሉ አስር አመት ሞልቷቸው ሰላት የማይሰግዱ አንዳንዶቹ ልጆች እንዲያውም ሲጠየቁ እናቴም አባቴም ስገድ አይሉኝም:: አሊያ ሲሰግዱ አላየውም በማለት ይመልሳሉ::
ዓምሩ ቢን ሹዓይብ ከአባቱና አያቱ እንዳወራው። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ይህንን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል ፡-
📜«ልጆቻችሁ ሰባት ዓመት ሲሆናቸው በሰላት እዘዟቸው:: አስር ዓመት ከሞላቸው ደግሞ ምቷቸው::»
📚(አቡ ዳውድ ሃሰን በሆነ ሰነድ ዘግበውታል)
📚(አቡ ዳውድ ሃሰን በሆነ ሰነድ ዘግበውታል)
አዎ! አስፈላጊ ሲሆን ልጆችን በመምታት ማደብ ያስፈልጋል::
🔜 በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል…
⌚ ሸዋል 29/10/1436
፝
🔚ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!
፝
🔚ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!
0 Comments