ሙስሊሟ ሴት እና ትዳር
ሚስት በ “መደረብ” በኩል በሴቶችና በወንዶች ላይ የሚስተዋሉ መስመር ዘለል ጠርዘኛ አመለካከቶች
በሴቶች በኩል ፡-
በእርግጥ ይህንን ህግ (መደረብ) ኢስላም እንዳስቀመጠው ተቀባዮች እንደሁኑ የሚለፍፉ ብዙዎች ናቸው:: ዳሩ ግን እውነታው ሲረጋገጥ ይህንን ድንጋጌ በቅናት ሽፋን ከመጻረራቸው የተነሳ ወደ ክህደት (ኩፍር)እያመሩ ያሉ ቀላል የሚባሉ አይደሉም::
እንዴት???
እንደሚታወቀው ከኢስላም ከሚያስወጡ ነገሮች አንዱ ነብዩ (ﷺ) ይዘውት የመጡትን ህግጋት እየሰሩትም ቢሆን መጥላት ነው፡፡
እንደሚታወቀው ከኢስላም ከሚያስወጡ ነገሮች አንዱ ነብዩ (ﷺ) ይዘውት የመጡትን ህግጋት እየሰሩትም ቢሆን መጥላት ነው፡፡
ታዲያ “መደረብ” የሚለውን ነገር ከመጥላታቸው የተነሳ የሚያንገሸግሻቸው ስንቶች ናቸው:: በተደረበባቸው ማግስት የጠንቆይ ቤትን ደጅ የሚጠኑ ቤታቸው ይቁጥረቻው:: ተሽለዋል የተባሉት ደግሞ የእህታቸውን ህይወት ቁም ስቅሉን በማሳጣት ባለ በሌለ ሃይል ባል ላይ ተጽኖ በማሳደር እንድትፋታ በማድረግ ትዳር ልጆቸን የሚበትኑት ለቁጥር ታክተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ የመደርብ ጥያቄ ሲቀርብላቸው የእምነትና ባህሪን ምንነት በማጣራት ፋንታ ቀዳሚ መስፈርትና ጥያቂያቸው ያለውን ሚስት እንዲፈታ ነው::”አዑዙቢላህ” ወላሂ እነዚህ ነገሮች ሃራም ብቻ ሳይሆኑ አረመኔያዊ አንባገነናዊ እርምጃዎች ናቸው::
በእርግጥ አንዲት ሴት ያገባ ወንድ አላገባም አልያም በኔ ላይ እንዳይደርብ ብላ መስፈርት ማድረግ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ያለችውን ህይወት ማወክና ማስፈታት ግን ኢስላም በአጽኖ ኮንኖታል፡፡
አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) ነብዩ (ﷺ) እርም ያደረጓቸው ነገር ብለው በጠቀሱበት ሃዲስ ላይ ይህ ይገኝበታል:-
አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) ነብዩ (ﷺ) እርም ያደረጓቸው ነገር ብለው በጠቀሱበት ሃዲስ ላይ ይህ ይገኝበታል:-
"...ولا تسأل المرأة طلاق أختها لتكفىء ما في إنائها" “
«አንድ ሴት እህቷ እንድትፈታ ፈፅሞ መጠየቅ የለባትም። (በዚህም) የእርሷን ድርሻዎች ልትቆጣጠር»
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ግን ደግሞ ለየትኛው ዘውታሪ ህይወት ነው ይህን ያህል የግር እሳት የሆነብን? አንቺ ዛሬ ስትንሰፈሰፊና በእህትሽ ላይ ስታሴሪ ቅጥፍ ልትይ ትችያለሽ:: እንበል አልጋ የሚያጎዳኝ በሽታ መጣብሽ ምን ታደርጊያለሽ አይንሽ እያየ ያሴርሽባት እህትሽ ሊያውም ያለ ተቀናቃኝ ተጠቃሚ ትሆናለች አላህ(ሱብሀነሁ.ወተአላ) እንዳለው:-
“وَلَا يَحِيقُ الْمَكْرُ السَّيِّئُ إِلَّا بِأَهْلِهِ ”
“وَلَا يَحِيقُ الْمَكْرُ السَّيِّئُ إِلَّا بِأَهْلِهِ ”
«ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም፡፡»
(ፋጢር : 43)
(ፋጢር : 43)
ምክንያቱም ምንም ማድረግ አትችይም እራስሽን እንኴ ማዳመጥ የማትችይበት ነገር ተጋርጦብሻልና:: ታዲያ እህቴ ይህንን ነገር እንኴ አስበን አላህን አንፈራም???
ነግ በኔ ማለት ይበጃል:: ሌላው እራሳችንን በዚህ ቦታ አድርገን እንመልከተው አንቺ አላገባሽም እድሜም ነጎደ፣ውበትም ፈሰሰ፣ወልዶ መሳምም ህልም እየሆነ መጣ ታዲያ በዚህ ግዜ መጥቶ አይዞሽ የሚልሽ እቅፍ ድግፍ የሚያደርግሽ ባል አራተኛም ቢሆን አትመኚም? እንዴታ እንጂ ትመኛለሽ ለማግኘትም ትጥሪያለሽ::
በቃ ሌላዋም እህትሽ እንዲሁ ነች::ትላንታ ባሎቻቸው “መደረብ” አይደለም ጥያቄውን ሲያነሱባቸው የነብር አራስ ይሆኑ የነበሩት ዛሬ ዛሬ ያ ገጠመኝ በእነርሱም ሲደርስ በሙሉ ደስታና ተቀባይነት ዘው ብለው ገብተውበታል፡፡
ይህ ሁሉ ሲባል ግን ቅናት የለም ምንም ነገር አይሰማን ማለት ፈጽሞ አይደለም። ለምን ትቀኚያለሽ የሚል ካለ ይወቀሳል ይወገዛል:: ቅናት የሴቶች ቁንጮ የአማኞች እናት በነበሩት ምርጦች ሰሃብያት ላይም ተንጸባርቌል:: ይህ የታወቀ ነው ማንኛውም ሰው ያፈቀረውን አካል ያለተቀናቃኝ የግሉ ማድረግ ነው የሚፈልገው:: ዳሩ ግን እነዚ እጹብ ድንቅ እንስቶች ላይ ቅናት ከመኖሩ ጋር በዘመናችን የምናየው ወንጀልና አረመኒያዊነት ፈጽሞ አልታየም::
ምክንያቱም …
በቅናትና ይህንን ህግ ባለመቀበል መካከል ልዩነት ስላለ ነው:: ሌላው ከምንምና ከማንም በላይ ተፈቃሪው አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ነው። እርሱ ከተፈቀረ ደግሞ ድንጋጌውን ለመቀበል ምንም አያዳግትም።
⌚ ሸዋል 23/10/1436
፝
ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!
፝
ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!
0 Comments