Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን መስጂዶችና ዙርያዎቻቸው የሽርክ ጭፈራ፣ የፎቶግራፍ መነሻ ቦታዎች ሆኑን?

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
መስጂዶችና ዙርያዎቻቸው የሽርክ ጭፈራ፣ የፎቶግራፍ መነሻ ቦታዎች ሆኑን?
አንድ መስጂድ ላይ ዛሬ አንድ ሙሽራ ወይንም ሚዜ ዙሁር ሰላት እያሰገደን እያለ የፎቶ ፍላሽ መአት ብልጭ ብልጭ ይላል ሱብሀነላህ መስጂድ የአላህ ቤት እንጂ ስቱድዬ አይደለም።
ከዚህ የከፋው ሙሉ ሚኑባስ ውስጥ ሽርካቸውን እያቀነቀኑ ይጨፍራሉ
"ያ ሀቢበላህ አል መደድ፣ ያረሱለላህ አል መደድ"
(የአላህ ውድ ሆይ! እርዳታ እንጠይቆታለን፣ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርዳታ እንጠይቆታለን)
እያሉ ድቤ እየመቱ፣ እየተጨፈረ የመስጂዱን አካባቢ በሽርክ አጥለቀለቁት መስጂድ ከሽርክ የፀዳ መሆን ሲገባው።
እርዳታ የሚለመነው አላህ ብቻ ነው። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንኳን በህይወት እያሉ ህያው የማይሞተውን አላህ ብቻና ብቻ ነበር እርዳታን ሲለምኑ የነበረው። ታድያ የእኛ ተምሳሌት እሳቸው አይደሉምን?
በተገላቢጦሹ እነ አቡ ጀህልና አቡ ለሀብ ነበሩ አላህንም እየጠሩ፣ ከአላህ ጋር ያለን ሌላ አማልክት የሚጠሩ የነበሩት።
የማይደባለቁ ነገሮችን መደባለቅ አይቻልም። አላህን ብቻ እና ብቻ እንጂ ማምለክ ከእርሱ ውጭ ያሉትን በርሱ ላይ መደረብ ሽርክ ነው። ምክንያቱም አላህ ሸሪካ፣ ልጅ፣ ሚስት፣ ረዳት የለውምና።
የፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ የነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጭምር ነውና።
የሙስሊም እምነትና ቃል ኪዳን በያንዳንዱ ሰላት ላይ ይህን ይመስላል
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንገዛለን፣ አንተንም ብቻ እርዳታ እንነምናለን።
አንተን ብቻና አንተንም ብቻ የሚሉት በደንብ ይሰመርባቸው።
ከአላህ ውጭ ማንንም ይሁን ማን አላህ ብቻ በሚችለው ጉዳይ እርዳታ መለመን ሽርክ ነው። ኢሳም (አለይሂ ሰላም)፣ ጂብሪልም (አለይሂ ሰላም)፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም)፣ ሌላም ቢሆን ሽርክ ነው።
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "የአደም ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል———" ብለዋል። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአደም ልጅ ናቸው ሞተዋል።
"ያ ረሱለላህ አል መደድ" እያሉ መስጂድን በሽርክ ጭፈራ መበጥበጥ አደጋው ከባድ ነው።
አላህ እንፍራ የሰርግ ቀን አላህ የሚመሰገንበት እንጂ የሚታመፅበት አይደለም። አለማዊ ዘፈን ወንጀል ነው እየተባለ፣ የወንጀሎችን ሁሉ ታላቅ ወንጀል ሽርክ መስጂድ በር ድረስ ይዞ መምጣት የሸይጧን መጫወቻ መሆን ነው።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎች የሰርግ ቀን "ባረከላሁ ለክ፣ ወባረከ አለይክ፣ ወጀመአ በይነሁማ ፊ ቨይር" ብለው ነበር ዱአ ያደረጉት ለሙሽራው። ያውም በዚህ ዱአም አልጨፈሩም ተወው በሽርክ ሊጨፍሩ።
ታድያ ለሰሃባዎች የበቃቸው ሱና ለዚህ ኡመት አይበቃውምን?
አላህ ሆይ! ሀቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን።