‹‹የጀሀነም ውሾች››
ይህ አባባል የታላቁ አዛኙ ነብይ አባባል ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይ ወሰለም) ይህን ያሉት ለኸዋሪጆች ነው፡፡ ኸዋሪጆች ማለት ጣኦታዊያንን ትተው ሙስሊሞችን የሚገድሉ ናቸው፡፡ በዘመናችን ላኢላሃኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ ብለው ከሽርክና ቢድዓ የራቁ ሙስሊሞችን በመግደል፣ ለመግደል በመዛት ላይ ያሉ ናቸው እነዚህ ኸዋሪጆች፡፡ ካፊሮችን ‹‹ወንድሞቻችን›› እያሉ የሚጠሩም አልጠፉም፡፡ የሙስሊሞችን ደም ለማፍሰስ ሙስሊሞችን ‹‹ካፊር፣ ሙናፊቅና የመሳሰለውን›› ስም በማስጠት የሙስሊሞችን ደም ሲያፈሱ ብሎም ለማፍሰስ ሲዝቱ አለም ላይ ይታያሉ፡፡
አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! የሚከተለውን ልብ ብለህ አንብብ
ኡሳማ ረድየላሁ አንህ ጦርነት ላይ አንድን ሙሽሪክ ሊገድለው ሲል ሙሽሪኩ ‹‹ላኢላሃኢለላህ›› አለ፡፡ ኡሳማም ይህን እያለ ገደለው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ይህ ነገር ደረሰ፣
ከዛም እሳቸው እንዲህ አሉት ላኢላሃኢለላህ እያለ ትገድለዋለህን?
እሱም (ኡሳማ) እንዲህ አላቸው ‹‹እንዳልገድለው ሰይፍ ፈርቶ ነው››
የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ልቡን ከፍተህ አይተሃልን››? አሉት፡፡
ኡሳማ ‹‹ምነው ከዛ ቀን በፊት ባልሰለምኩ ኖሮ›› ብሎ እስኪፀፀት ድረስ፡፡
ዛሬ የሚሰሩትን ቢድዓ ያልተከተላቸውን ሙስሊም ለመግደል ‹‹ሙናፊቅ›› እያሉ በየስርቻው ሙስሊሞች ላይ የሚዝቱ፣ ብሎም እድሉን ሲያገኙ ሙስሊሞችን የሚገድሉ ሞልተዋል፡፡
ሙናፊቅ ማን እንደሆነ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን አላህ ካሳወቃቸው ሙናፊቆች ውጭ የማያውቁበት ሁኔታ ነበር፡፡ አላህም ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹አንተ አታውቃቸውም፣ እኛ እናውቃቸዋለን›› ብሎ የነገራቸው ሁኔታም አለ፡፡ ሙስሊሞች ሆይ ከእንደዚህ አይነት ሰዎች እራሳችሁን ጠብቁ፡፡
ረሱል ሰለላሁ አለይ ወሰለም እነዚህ ኸዋሪጆች በየዘመኑ እንደሚከሰቱ ብሎም ከሰማይ በታች መጥፎ የሚባሉት ሰዎች እነሱ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
የአላህ መልክተኛ እነዚህን ሰዎች የጀሐነም ውሾች ብለው ነው የጠሯቸው፡፡ አላህ ከሸራቸው ይጠብቀን፡፡ አላህ ሆይ! ብልሐትም ሐይልም የለንምና አንተው ከሸራቸው ጠብቀን፡፡