Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከአቂዳ አንዱ መሆኑን እናውቅ ይሆን ?



ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ተውሂድ ማስተማርና አቂዳን ማስተካከል እንዲሁም ከሽርክ ማስጠንቀቅ የነቢያቶች ዋና የዳዕዋ ተልኮ ነው ። አላህ በቁርዓኑ እንዳለው ፡
(وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ )
( ወደ ሁሉም ህዝቦች መልዕከትኛውን ልክናል ፤ ሰዎች አላህን በብቸኝነት እንዲገዙና እንዲሁም ከአላህ ውጭ ከሚገዙትን እንዲርቁ ዘንድ ) ።
ለዚህም ትልቅ አላማ በሁሉም ዘመን ሙሉና በትክከልኛውና መሰረት ባለው ሁኔታ የሚያስተምሩትና የሚያሰራጩት ትክክለኞች አህሉ ሱና ብቻ ናቸው ። ሌሎች የቢዳ አራማጆች ፤ በአቂዳና በተውሂድ ዙሪያ በከፊሉ በማመን ከፊሉን በማስተባበልና ችላ በማለት ይታወቃሉ ። ለምሳሌ ታላላቅ አኢማዎች በአቂዳ ኪታባቸው ከሚጠቅሱትና ከሚያካትቱ ከአቂዳ ነጥቦች ፤
አንደኛ ፡ (በሙስሊም መሪ ላይ አለማመፅን )፤ የሚል እናገኛለን ፤ ልክ ኢማሙ ጠሃዊ በአቂዳቱ ጣሃዊያ በሚል ኪታባቸው ፤ እንዲሁም ሼኽ ኢስላም ኢብኑ ቴይሚያ በአቂዳቱ ዋሲጢያና በሌሎች ኪታቦቻቸው ፤ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ኡለማዎች በአቂዳ ኪታባቸው አካተው እናገኛለን ። ነገር ግን ከቀድምት ኽዋሪጆች ጀምሮ አሁን ባለንበት ዘመን ፤ ሙስሉም በሆነ መሪ ላይ ማፅን አደትልቅ ጀብዱ ቆጥረው ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ ።
ሁለተኛው ምሳሌ በአቂዳ ኪታባቸው የሚያካትቱት ፤ ሶሃቦችን መውደድና የነሱን ክብር መጠበቅና እነሱን ከሚያቶናኮሉ ሰዎች ራሳችን ማራቅ እንዳለብን ያስቀምጣሉ ። ስለዚህ አንድ ሰው አህሉ ሱና ነኝ የሚል በነዚህንም ነጥቦች ዙሪያ አቂዳው ማስተካከል አለብት ፤ አንድ ሰው ሰለተውሂድና ሽርኽ ስለተነገርና ስለፃፈ ብቻ አይተን መታለል የለብንም ። ስንት በኽዋሪጅ አቂዳ የተባላሸ ሰለተውሂድና ሸሪዓ ሲለፈልፍ እናያለን ፤ ስንት ሶሃቦችን ከሚሳደቡ ሰዎች የሚከላልከሉ ሰዎች ሰለተውሂድና ስለ ሽርክ ያወራሉ፤ ይዕፋሉ ።
ኢኽዋኖች አንድ አቂዳ ያላቸው ሰዎች ጥርቅም አይደለም የተለያዩ አቂዳ ያላቸው ሰዎች ናቸው አንድላይ መተው ለኢስላም እንታገላለን የሚሉት ፤ አሻዒራዎች ፤ ሱፊዮች ፤ሙርጂዓዎች ፤ በአንዳድ ቦታ ላይም የአህሉ ሱና አቂዳ ያላቸውም ሰዎች በውስጣቸው አሉ ፤ ስለዚህ መጠንቀቅ አለብን ። ወሰላሙ አሌኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ።