Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ገደሉት አላህም ይግደላቸውና


عن جابر قال خرجنا في سفر فأصاب رجلا منا حجر فشجه في رأسه ثم احتلم فسأل أصحابه هل تجدون لي رخصة في التيمم فقالوا ما نجد لك رخصة وأنت تقدر على الماء فاغتسل فمات فلما قدمنا على رسول الله صلى الله عليه وسلم أخبر بذلك فقال قتلوه قتلهم الله ألا سألوا إذ لم يعلموا فإنما شفاء العي السؤال إنما كان يكفيه أن يتيمم ويعصر أو يعصب على جرحه ثم يمسح عليه ويغسل سائر جسده
አቢ ዳውድና ዳሩልቁጥን በዘገቡትና ፤ ጃቢር ባወሩት ሃዲስ ወስጥ ፡ ጃቢር እንዲህ በማለት ይተርካል ፤( ግዞ ላይ እያለን ፤ ከእኛ አንድ ሰው ጭንቅላቱ በድንጋይ ቆስሎ እያለ ኢህቲላም ( በእንቅልፉ ልቡ መንይ ወጣ ) ሆነና ለመታጠብ ሲፈልግ ፤ ከእኛ የተወሰኑት ሰዎችን እንዴት ነው ውሃ ትቼ በአፈር ተየሙም ማድረግ ብቻ እችላለው ብሎ ሲጠይቃቸው ፤ አይ በጭራሽ ጌዴታ በውሃ መታጠብ አለብህ አሉት ። እሱም ገላውን በውሃ ሲታጠብ ፤ ቁስሉ ብሶበት ሞተ ። ወደ ነቢያችን ሰለላሁ አሌሂ ወሰለም መተን ነገሩ ስንነግራቸው ( ገደሉት አላህም ይግደላቸው ፤ ካላወቁ ለምን አይጠይቁም ፤የአለማወቅ መዳኒት እኮ መጠየቅ ነው ። በአፈር ብቻ ተየሙም ማድረግና በቁስሉ ላይ ጨርቅ ነገር ጠቅልሎ በሱ ላይ በመዳበስ የቀረውን ሰውነቱን በውሃ ማጠብ ይችል ነበር ) አሉ ።
ከዚህ ሀዲስ የምንረዳው አንድን ሙስሊም መገድል ማለት ቀጥታ በግዱያው ላይ መሳተው ብቻ ሳይሆን ፤ ለሞቱ ምክንያት በሆኑት ነገር ላይ ፈትዋ መስጠት ፤ አመራርና ትብብር ማድረግ ልክ እሱን እንደመግደል ይቆጠራል ። ስለዚህ በማንኛም ሙስሉም ላይ ግዴታ የሚሆነው በተለይ የሙስሊሙ ደም በተመለከተ የሚሰጠው ፈትዋና አመራር ፤ ከቁርዓንና ከትክክለኛ ሀዲስ ማስረጃ መሆን
አለበት እንጂ ፤ ስሜታችን በመከተል ፤ ከዛም አልፎ የኩፋሮችን ስልት በመጠቀም ፤ ኩፋሮች ያሳለፉትን ትግል እንደ ምሳሌ በመጥቀስ እና የመሳሰሉትን አመራር መስጠት ፤ ማሰራጨት ፤ በዛ ምክንያት የሙስሊሙ ደም በከንቱ የሚፈስ ከሆነ ሁላችንም ከተጠያቂነት መዳን እንደማንችል አውቀን ከወዲህው ጥንቃቄ እናድርግ