Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ህዝባዊ ተሳትፎነት ሸሪዓዊ ልጋም ካልተደረገለት ወደ ጥፋት ይመራል


 ህዝባዊ ተሳትፎነት ፤ለድምፅ ብልጫ ፤ለህዝባዊ ምርጫና ዲሞክራሲ ለሚባሉት ኢስልምና የማያቃቸው ከኩፋሮች ወደኛ የፈለሰውን የአመራር ስልት ወደ ሙስሊሞች ለማምጣት እንደማስረጃ መጠቀም የማያስችለን ነጥቦችን አንድ ላይ እንመልከት ።
1። ነቢያችን ( ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ) ሶሃቦቻችን ለዚህ የሶላት ጥሪ ስልት ሃሳባቸውን አንዲለግሱ ስጠይቃቸው ሁሉም ሙስሊሞችህ ፤ ወዱንም ሴቱንም አንድላይ ሰብስቦ ህዝባዊ መብታቹሁን ተጠቅማቹህ ሃሳባቹህ ለግሱን አላላቸውም ፤ በሳቸው ዙሪያ ያሉትን የተወሰኑ ሶሃቦችን ብቻ ያሳተፈ ሃሳብ የመሰበሰብ እርምጃ ነበር ።
2። ሀሳባቸው ከለገሱት ሶሃቦች ሃሳባቸውን ውድቅ ያደረጉበት መንገድ ፤ በድምፅ ብልጫ ሳይሆን ሸሪዓዊ መንገድን ሊፃረሩና ከኩፋሮች ጋር ሊያመሳስላቸው የሚችሉትን ፤ ሃሳቦችን መሆኑን በመስረጃውን በመጥቀስ ነበር ውድቅ ያደረጉት ለምሳሌ ፤ ወደ ሶላት ሰውን ለመጥራት እሳትን በማቀጣጠል ቢሆንስ ተብሎ የቀረበውን ሃሳብ ፤ እሳት የሚገዙት ሰዎች ጋር መመሳሰልን ያማጣል በሚል ነቢያችን ( ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ) ሃሳቡን ውድቅ አደረጉት ። ደውልን በመደወል ወደ ሶላት ሰውን ብንጠራስ የሚለው የቀረበውን ሃሳብ ፤ ይህ ከነሳራዎች ጋር ያመሳስለናል በማለት ነቢያችን ( ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ) ሃሳቡን ውድቅ አደረጉት ።
በዚህ መልኩ ነው ሊሰነዘሩ የሚችሉት ሃሳቦች ከሸሪዓ ጋር አያይዘው ውድቅ ማደረግ ያለብን እንጂ የብዙሃኑ ህዝቡ ሃሳብ ስለሆነ ሃሳባቸውን ማክበር አለብን በማለት ፤ ለብዙሃኑ ህዝብ ሜዳ ማስፈት የለብንም።
3። አዛን ማድረጉ የተሻለ ሃሳብ ተብሎ የተወሰደው የአብዛኛው ሃሳብ ተብሎ በድምፅ ብልጫ ሳይሆን ። ነቢያችን ጥሩ መሆኑና በድርጊቱ ከኩፋሮች ጋር የማይመሳስልና አዛን በሚደረግበት ግዜ ያሉት ቃላቶቹ ፤ የአላህን ማወደስና ወደ ሰላት ሰው እንዲመጣ በጥሩ መልኩ የሚያበረታታ ስለሆነ ነበር ።
በመጨረሻም ፤ በኢስልምና ብዙሃኑ ህዝብ ሊኖራቸው የሚችል ተሳትፎ በሸሪዓዊ ልጓም መሎገም አለበት እንጂ ልቅ የሆነ መብት ተሰቷቸው የፈለጉትን መደንገግ ፤ ሃሳብ መስጠት ፤መምረጥ ፤ ማስመረጥ ፤ በጣም አሳሳቢና ወሳኝ የሙስሊሞች ጉዳይ ላይ ሁሉም ህዝብ እጃቸውን ማስገባት ፤ አይገባቸውም ። ለምን ብዙሃኑ ሙስሊም ሁሉም በተለያየ የዲን እውቀት ደረጃና ብስለትና ከዛም አልፎ በተለይ በዚህ ባለንበት
ዘመን በሙስሊሙ መሃል የተሳሳተ አቂዳ ያለውና በተለያዩ ብልሹ በሆኑ የጥመት አስተሳሰብ ውስጥ ያለ ሰው በሙስሊሙ ማሃል ይገኛል ።
ሰለዚህ ሃሳብ የሚሰጥና መመሪያ የሚያስተላልፈው አካል ፤ በየቦታው የተደራጁት ብዙሃኑ ህዝበ ሙስሊም ሳይሆን በትክክለኛ ሸሪዓው እውቀት የተካኑ ኡለማዎች ናቸው ፤ መጥፎ ሃሳብና ጥሩ ሃሳብን ለይተው የሚያቁት ፤ የሙስሉሙ በደልን ለመታገል ትክክለኛ ሃሳብ የሚነድፉት ፤ ትክክለኛ እርምጃን የሚደነግጉት ።
ስለዚህ ውድ የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ፤ ሁላችንም ደረጃችና አቅማችን እንወቅ ለኢስላምና ለሙስሊሞች መስራት አለብን ብለን የምንወሳደቸውን እርምጃዎችን እንመረምረው ፤ እኔ ማነኝ ?ከማን ጋር ነኝ መስራት ያለብኝ ?
፤ ለሙስሊሙ በደል አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ የሚል አጉል የዋህነታችን ከአላህ ጋር አጣልቶን ሌላ ስህተት ውስጥ ከመግባት ራሳችን እንጠብቅ ።
የዚህ ዓይነት መልዕክት በቀጣይነት አንድላይ የምናይበት አጋጣሚዎች ብዙ ስለሆነ ተጠባበቁን ። ጥሩን በጡርነቱ አውቀው የሚከተሉ
መጥፎውን በመጥፎነቱ አውቀው የሚርቁ አላህ ያድርገን ።