Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

«የአላህን 99 ስሞች የሸመደደ ጀነት ገባ» የመስፈርቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ማብራሪያ

«የአላህን 99 ስሞች የሸመደደ ጀነት ገባ»
የመስፈርቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ማብራሪያ
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) በተወራው ሃዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
📜«ለአላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት መቶ ለመሙላት አንድ የቀረው። የሸመደደው ጀነት ገባ።»
📚 ቡኻሪና ሙስሊም
በቅድሚያ ይህ ሃዲስ ከመብራራቱ በፊት ከእርሱ ጋር የሚያያዝን አንድ ታላቅ መሰረት መጥቀሱ ግድ ነው።
እርሱም፦
"የአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ስሞች ፈፅሞ በቁጥር የተገደቡ አለመሆናቸውን ነው። "
ለዚህም ማስረጃው ከዓብደላህ ቢን መስኡድ (ረዲየላሁ ዓንሁ) የተወራው ሃዲስ ነው። ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በአንድ ዱዐቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦
📜 «᎐᎐᎐በስሞችህ ሁሉ እማፀንሃለው። እራስህን በሰየምክበት። ወይም መፅሃፍህ ውስጥ ባሰፈርካቸው። ወይም ከፉጡራንህ ለአንዱ ባስተማርከው። ወይም ለማንም ባልገለፅከው አንተ ዘንድ ባሉት ስሞችህ ሁሉ።᎐᎐᎐»
እንግዲህ እዚህ ሃዲስ ላይ የመጨረሻው ሃረግ የአላህ ስሞች በቁጥር ያልተገደቡ እንደሆኑ በማያሻማ መልኩ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጧል።
ሌላው እዚሁ ሃዲስ ላይ ራሱ ከላይ ያለው ሃረግም ይህንን ያመለክታል።
ምክንያቱም የተባለው፦
«ለአላህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት።»
እንጂ "የአላህ ስሞች ዘጠና ዘጠኝ ናቸው" አልተባለም።
ምክንያቱም ይህኛው አባባል እነዚህ ብቻ ናቸው የሚለውን ያሲዛልና።
📝ሁለተኛው ግን ይህንን ፈፅሞ አያመላክትም። ለዚህም አንድ ወሳኝ ምሳሌ እንጥቀስ፦
እከሌ ለሰደቃ ያስቀመጠው መቶ ብር አላው። ቢባል ይህ ሰው ከዚህ ውጪ ብር የለውም ማለትን ፈፅሞ አያሲዝም። ይህ ከተብራራ ዘንድ ሌላው ወሳኝ ነገር ደግሞ እውን የአላህን ስሞች መሸምደድ ሲባል ብዙዎቻችን እንደሚገባን ቃሉን ብቻ ሚመለከት ነውን?????? በፍፁም።
መልሱን አላህ ይዘንለትና ታላቁ የኢስላም ሊቅኢብኑል ቀይም "በዳኢኡል ፈዋኢድ" በተሰኘው መፅሃፉ ላይ በሚገባ አብራርቶታል።
የሚከተላው ነው፦[የአላህን የተዋቡ ስሞች ለመሸምደድ ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነርሱንም
በማሟላትና በማረጋገጥ ነው የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሃዲስ ላይ የተገለፀውን ታላቁን የአላህን ምንዳ መጎናፀፍ የሚቻለው።
☞ ደረጃ አንድ፦
ቃሉን መሸምደድ።
ምሳሌ፦አረህማን፣አረሂም እና ወዘተ እያሉ መሃፈዝ።
☞ ደረጃ ሁለት፦
ትርጉሙንና ያመላከተውን መልእክት መገንዘብ።
ምሳሌ፦ ከአላህ ስሞች ውስጥ "አሰሚዕ" ይገኝበታል። ትርጉሙ "ሰሚ"
ማለት ሲሆን የሚያመለክተው ደግሞ አላህ የመስማት በሃሪ እንዳለው ነው። አዎ የቅርቡንም የሩቁንም ፡ግልፁ ንም ስውሩንም፡ ቋንቋዎች ሳይደባለቁበት ፡ድምፆች ሳይቀላቀሉበት የሚሰማ መሆኑን የሚያመለክት ውብ ስሙ ነው። (ሱብሃነሁ ወተዓላ)።
☞ ደረጃ ሶስት፦
በእርሱ አላህን መጣራት (ዱዓ) ማድረግ።
እዚህ ጋር ሁለቱንም የዱዓ አይነቶች ያካትታል።
እነርሱም
1) ዱዓዑል መስአላ።
ይህ ማለት፦ በስሞቹ አላህን መለመን ነው።
ምሳሌ፦ አዛኙ ሆይ እዘንልኝ። ለጋሹ ሆይ ለግሰኝ። እና በመሳሰሉት።
2) ዱዐኡል ዒባዳ።
ይህ ማለት ደግሞ
ምሳሌ፦ አንድ ሰው አላህ እንደሚያየው አውቆ ቅጣቱን በመፍራት ወንጀልን ሲርቅ እንዲሁም እንደሚያየው አውቆ ምንዳውን በመከጀል መልካም ነገርን ሲፈፅም ነው።
እዚህ ጋር አንድን ነገር ላክልልላችሁ።
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ሲል ተናገረ።
«አንድ ሰውዬ አንዲት ሴትን በውድቅት ሌሊት ላይ ላልሆነ ነገር ይገፋፋት ጀመር። እርሷም በእጅ አልል አለችው። ታዲያ እንዲህ አላት ። ከዋክብት እንጂ ማንም አያየንም። እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት። "ፈአይነ ሙከውኪቡሃ?" የከዋክብቱ ባለቤትስ??። »
ሱብሃነ ረቢ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ተመልካች መሆኑን በወጉ ስለተገነዘበች ከዚህ መአት ለመትረፍ ቻለች።
አዎ ልክ እንደዚህ ነው በእያንዳንዱ የአማኝ ህይወት ላይ የአላህ ስሞቹና በሃሪዎቹ ትርጉም ሊኖራቸው የሚገባው። አበቃሁ።
📚 "ፊቅሁል አስማኡ ል ሁስና" ከተሰኘው የሸይኽ ዓብዱረዛቅ አል በድር ኪታብና ሸይኽ ኢሊያስ አህመድ "ዓቂደቱል ዋሲጥያ" ን ሲያስተምር ከጠቃቀሳቸው ማብራሪያዎች ኮርጄ ነው።
 አላህ ሁላችንንም ባማሩትና በተዋቡት ስምና በሃሪዎቹ እንድናመልከው ያድለን። አሚን
✒By Ummu Abdellah Muhammed
፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠
የተንቢሀት የዋትሳፕ ግሩፕ ⌚ ዙል ቃዕዳ 12/11/1436 መልእክት

🔚ተንቢሃት » ፝ »፝ » አማኝ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት!

Post a Comment

0 Comments