Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ምክር ለሙስሊም እህቶቼ!!! በግጥም መልክ!! ተደፈርኩኝ አትበይ

ርዕስ :- ተደፈርኩኝ አትበይ

ያጠለቅሽው ቀሚስ
ቁልቁል ሲንሸራተት:
ገላሽ ተገላልጦ
ደረትሽ ሲከፈት:
ሂጃብሽ ተነስቶ
ፀጉርሽ ፍሪዝ ሆኖ:
ባርቴፊሻል ሜካፕ
ፊትሽ ተሽሞንሙኖ:
ተደፈርኩኝ አትበይ
ክብሬ ተረገጠ:
ድርጊትሽ ከዲንሽ እያፈነገጠ
ሰዉ እያሳሰተ ፊትና እየጎተተ:
ከእግርሽ እስከ ፀጉርሽ
ገላሽን ገላልበሽ:
ተደፈርኩኝ አትበይ
ራስሽን ደፍረሽ:
እኔስ ይገርመኛል
አንቺን ሳስተውልሽ:
ሂጃብሽን ክብርሽን አውልቀሽ
ክብር መፈለግሽ:
ጌታሽ ያዘዘሽን
ትዕዛዝ ሳታደርጊ:
መዋብን ማማርን
ክብርን አትፈልጊ!
እህቴ አድምጭኝ
እውነት ሙስሊም ከሆንሽ:
ዱንያ አልኖርም
እሞታለሁኝ ካልሽ :
አደራ የምልሽ ሲስቱ
በእውነት አኼራን ከፈለግሽ :
በጅልባብ ሸፍኚው
ይህን ክቡር ገላሽ:
ኒቃብም ልበሽ
ባክሽን አደራሽ
ይህ ነው ላንቺ መንገድ
ከሳትመዳኛሽ:
አላህን ለመታዘዝ
ቁርአንን ተከተይ:
ምን ብዬ ልንገርሽ
ሲስቱ ከዚ በላይ:
ወሰላሙ አለይኩም
ሙስሊም እህቶቼ:
ወሰላሙ አለይኩም
የዲን ጏደኞቼ:
by ወንድም hamdu Muhammad!   Muselsel!