Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፊታዋ ለሙስሊም ሴቶች ሒናን በራስ ላይ መቀባት ውዱእን አያጠፍም ሽይኽ አብዱልአዚዝ ኢብን ባዝ

1.4 ሒናን በራስ ላይ መቀባት ውዱእን አያጠፍም።
ጥያቄ፦
_____
አንድ ሴት ውዱእ ካደረገች በኋላ ጸጉሯን ሒና ተቀባች። ሒናው በጸሯ ላይ እያለ ሶላት ሰገደች ። የዚህች ሴት ሶላት ተቀባይነት የለውምን ? ያደረገችው ውዱእ ከጠፍ (ከተበላሽ ) እንደ አዲስ ወዱእ ስታደርግ ጸጉሯን በውሃ በምታብስበት ጊዜ በሒናው ላይ ነው የምታብስው ወይስ ሂናውን በሙሉ በመታጠብ አስወግዳ መደበኛ የሆነውን ወዱእ ነው ማድረግ ያለባት?
መልስ ፦
_____
ይህች ሴት ውዱእ ስታደርግ ጸጉሯን በውሃ እንደምታብሰው ሁሉ በሂናው ላይ ማበስና በመጫረሻ ላይ እግሮቿን ማጠብ ነው ያለባት። ሆኖም ግን ጁንብ ከሆነች (ከባለቤቷ ጋር ግንኙነት ከፈጸመች ) በሂናዋ ላይ ብቻ ማበስ በቂ ባልመሆኑ በጸጉሯ ላይ ለሶስት ጊዜያት ያክል ውሃ ማፍሰስ ይኖርበታ። ለዚህ አባባላችን እንደ ማስረጃ የምንይዘው በኡሙ ሰላም رضى الله عنه የተወራውንና ሙስሊም በዘገቡት ሶሂህ {ጠንካራ }ሀዲስ ላይ የተጠቀሰውን ክስተት ነው። በዚህ ሐዲስ መሠረት ኡሙ ሰላማ
رضى الله عنه
ነቢዩን ﷺ እንዲህ በማለት ጠይቃቸዋለች ።<<የአላህ መልዕክተኛ ሆይ !እኔ ጸጉሬን በቀጭኑ( ጥቅጥቅ አድርጌ) የምጒነጒን ሴት ነኝ ። ጅኑብ በምሆንበት ጊዜና ከወር አባባየ ስጠራ የጸጉሬን ሹሩባ ፈትቼ መታጠብ ይኖርብኛልን?>>ለዚህ ጥያቄ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሚከተለውን መልስ ሰጡ፦<< አይደለም!ጸጉርሽና የራስ ቅልሽ እስኪርስ ድርስ ሶስት ጊዜ በእፍኝህ ውሃ እየዘገንሽ ራስሽ ላይ ማፍስሰ ይበቃሻል። >>ከዚያ በኋላ ሌላውን የሰውነትሽን ክፍል በማጠብ መንፃት ትችያለሽ ።
ይሁን እንጂ አንድ ሴት ከወር አበባዋ ስትነፃ ጉንጉኗን ብትፈታና በውሃ ጸጉሯንና .የራስ ቅሏን ብታዳርስ መልካም ነው የሚል ሌላ የሒዳስ ዘገባም እንዳለ መግለጽ እፈልጋለሁ ።[ሽይኽ አብዱልአዚዝ ኢብን ባዝ]

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
➊ ሆኖም ግን ከሂናውን ጋር የሚደባለቁ ነገሮች ኖረው የቅባትንት ጠባይ ካላቸው በሙሉ መታጠብ ግድ ይሆንበታል የሚል አቋም ያላቸው ምሁራን እንዳሉ መታወቅ አለበት ።
2 ሰሂህ ሀዲስ የሚባለው በሀዲስ ጥናት [እስጢላህ ] መሰረት ታማኝነታቸውና እውነተኛ ነታቸው በሁሉም ሰዎች ዘንድ በተመሰከረላቸው ሰዎች አማካኝነት ሰንስለቱ ሳይቋረጥ ወደ ነብዩ ﷺየደረስ ዘገባ ሲሆን ከአፊንጋጭነትና ከተለያዩ የሐዲስ በሽታዎች የጠራ መሆን ይኖርበታል።
\\_________________________________\\

Post a Comment

0 Comments