ጥያቄ፡-
የኢዕቲካፍ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው? ፆም ከመስፈርቶቹ ይካተታልን? አንድ ሰው በኢዕቲካፍ ላይ እያለ በሽተኛን
መጠየቅ፣ በግብዣ ቦታ ላይ መገኘት፣ የቤተሰቦቹን ጉዳይ ማስፈፀም፣ አስክሬን መሸኘት ወይም ወደ ስራው መሄድ
ይችላልን? መልስ፡- ሰላተል ጀመዓ በሚሰገድባቸው መስጂዶች ውስጥ
ኢዕቲካፍ ማድረግ የተደነገገ ነው፡፡ ነገር ግን ኢዕቲካፍ የሚያደርገው ግለሰብ ሰላተል ጁምዓ ግዴታ ከሚሆንባቸው
ሰዎች መካከል ከሆነና ከኢዕቲካፍ ቀናት መካከል የጁምዓ ቀን ካለ ሰላተልጁምዓ በሚሰገድበት መስጅድ ውስጥ ኢዕቲካፍን
ማድረጉ የተሻለ (በላጭ) ነው፡፡ ፆም የኢዕቲካፍ መስፈርት አይደለም፡፡ እንዲሁም በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በዚያ
ወቅት በሽተኛን አለመጠየቁ፣ ጥሪ ቢቀርብለት በጥሪ ቦታ ላይ አለመገኘቱ፣ የቤተሰቦቹን ጉዳዬች አለማስፈፀሙ፣
አስክሬን አለመሸኘቱ፣ ከመስጂድ ውጪ ወደ ስራው አለመሄዱ ሱና ነው፡፡ ይህም እናታች ዓኢሻ በትክክለኛ ሰነድ እንዲህ
ማለታቸው የተረጋገጠ በሆኑ ነው፡፡ ‹‹በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በሽተኛን አለመጠየቁ፣ የአስክሬን አሸኛኘት ላይ
አለመገኘቱ፣ ግንኙነትን አለመፈፀሙም፣ በስሜት ከተቃራኒ ፆታ ጋር አለመተሻሸቱ፣ አስገዳጅ ለሆነ ጉዳይ ቢሆን እንጂ
ከኢዕቲካፍ አለመውጣቱ ሱና ነው፡፡›› አቡዳውድ እና ዳረቁጥኒ ዘግበውታል
ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ አብዱላህ ቢን ቁዑድ አብዱረዛቅ ዓፊፊ አብዱል ዓዚዝ ኢብን ባዝ
ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ አብዱላህ ቢን ቁዑድ አብዱረዛቅ ዓፊፊ አብዱል ዓዚዝ ኢብን ባዝ