Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማን ነው ጿ ሚ ው ኢብኑል-ቀይ'ዪም አልጀውዚ [አላህ ይዘንላቸውና]

ተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ

ማን ነው ጿ ሚ ው
` ﻣــﻦ ﻫـــﻮ ﺍﻟﺼَّﺎﺋـــﻢ ؟؟

ኢብኑል-ቀይ'ዪም አልጀውዚ [አላህ ይዘንላቸውና] ፆመኛ ማን እንደሆነ በቀጣዩ መልክ ያብራሩልናል።☞
[{« ፆመኛ ማለት☞
⇝ ያ… አካላቱ ከኃጢኣት የፆመች
⇝ አንደበቱ ከሐሰት፣ ከአስፀያፊ ነገርና ከቅጥፈት መስካሪነት የታቀበች
⇝ ሆዱም ከመብልና ከመጠጥ እንዲሁም ብልቱ ከስሜታዊ እርካታ የተቆጠበ ሲሆን፤
💥ካወራ እንኳን ፆሙን የሚያቆስል ነገር አይናገርም። የሆነ ነገር ሲያደርግም ፆሙን የሚያበላሽበትን ነግር አይፈፅምም።
💥ከአንደበቱ የሚወጣው ንግግሩ ሁሉ ጠቃሚና መልካም ሲሆን ተግባራቱም እንደዚያው ያማሩ ናቸው።
🍇ምሳሌውም ልክ ሚስክ (መልካም መዓዛ ያለው ነገር) የያዘ ሰው ዘንድ ሲኮን ቆንጆ ሽታው እንደሚደርስ ሁሉ ከፆመኛው የተቀመጠም የንግግሩና የተግባሩ መልካምነት ይደርሰዋልና ይጠቀምበታል።
⇝ ከሱ ጋር የሆነ ከሀሰት ምስክር፣ ከቅጥፈትና ከወንጀሎች ብሎም ከበደል ሰላም ያገኛል።
📗የተደነገገልን የፆም አይነት ይህ ነው እንጂ ከምግብና ከመጠጥ መታቀብ ብቻ አይደለም።
⇝ ፆምኮ በውጫዊው አካል ከወንጀሎች መፆምና በሆድ ደግሞ ከሚጠጡና ከሚበሉ ነገሮች መታቀብ ነው።
⇝ ምክንያቱም ምግብና መጠጥ የፆምን ምንዳ ቆርጠው እንደሚያበላሹ ሁሉ ኃጢኣትም የፆምን ምንዳ ታቋርጣለች። ፍሬውንም ታበላሻለች። ከዚያም ምንም ወዳልፆመ ሰው ደረጃ ትወስደዋለች።»}]
ﻗـﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴِّﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
🌸« ﻭﺍﻟﺼَّﺎﺋﻢ ﻫﻮ ﺍﻟَّﺬﻱ ﺻﺎﻣﺖ ﺟﻮﺍﺭﺣﻪ ﻋﻦ ﺍﻵﺛﺎﻡ, ﻭﻟﺴﺎﻧﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﻜﺬﺏ ﻭﺍﻟﻔﺤﺶ ﻭﻗﻮﻝ ﺍﻟﺰُّﻭﺭ, ﻭﺑﻄﻨﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ, ﻭﻓﺮﺟﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﺮَّﻓَﺚ؛ ﻓﺈﻥْ ﺗﻜﻠَّﻢ ﻟﻢ ﻳﺘﻜﻠَّﻢ ﺑﻤﺎ ﻳﺠﺮﺡ ﺻﻮﻣﻪ, ﻭﺇﻥ ﻓﻌﻞ ﻟﻢ ﻳﻔﻌﻞ ﻣﺎ ﻳﻔﺴﺪ ﺻﻮﻣﻪ, ﻓﻴﺨﺮﺝ ﻛﻼﻣﻪ ﻛﻠُّﻪ ﻧﺎﻓﻌًﺎ ﺻﺎﻟﺤًﺎ, ﻭﻛﺬﻟﻚ ﺃﻋﻤﺎﻟﻪ, ﻓﻬﻲ ﺑﻤﻨﺰﻟﺔ ﺍﻟﺮَّﺍﺋﺤﺔ ﺍﻟَّﺘﻲ ﻳﺸﻤُّﻬﺎ ﻣﻦ ﺟﺎﻟﺲ ﺣﺎﻣﻞ ﺍﻟﻤﺴﻚ. ﻛﺬﻟﻚ ﻣﻦ ﺟﺎﻟﺲ ﺍﻟﺼَّﺎﺋﻢ ﺍﻧﺘﻔﻊ ﺑﻤﺠﺎﻟﺴﺘﻪ, ﻭﺃَﻣِﻦ ﻓﻴﻬﺎ ﻣﻦ ﺍﻟﺰُّﻭﺭ ﻭﺍﻟﻜﺬﺏ ﻭﺍﻟﻔﺠﻮﺭ ﻭﺍﻟﻈُّﻠﻢ, ﻫﺬﺍ ﻫﻮ ﺍﻟﺼَّﻮﻡ ﺍﻟﻤﺸﺮﻭﻉ ﻻ ﻣﺠﺮَّﺩ ﺍﻹﻣﺴﺎﻙ ﻋﻦ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ ... ؛
ﻓﺎﻟﺼَّﻮﻡ ﻫﻮ ﺻﻮﻡ ﺍﻟﺠﻮﺍﺭﺡ ﻋﻦ ﺍﻵﺛﺎﻡ, ﻭﺻﻮﻡ ﺍﻟﺒﻄﻦ ﻋﻦ ﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ ﻭﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ؛ ﻓﻜﻤﺎ ﺃﻥَّ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ ﻳﻘﻄﻌﻪ ﻭﻳﻔﺴﺪﻩ,ﻓﻬﻜﺬﺍ ﺍﻵﺛﺎﻡ ﺗﻘﻄﻊ ﺛﻮﺍﺑَﻪ، ﻭﺗُﻔﺴﺪُ ﺛﻤﺮﺗَﻪ, ﻓﺘُﺼَﻴِّﺮﻩ ﺑﻤﻨﺰﻟﺔ ﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺼُﻢ ».
ኢብኑል ቀይ'ዪም አልጀውዚ [ረሂመሁላህ]
📕ﺍﻟﻮﺍﺑﻞ ﺍﻟﺼَّﻴِّﺐ :ص(٣١، ٣٢) ምንጭ
አልዋቢሊ-አስ'ሰዪብ ከገፅ 31-32
---------------------
www.fb.com/tenbihat
🎐ረ መ ዷ ን 14 /1436
ጁላይ 01/2015

Post a Comment

0 Comments