Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ የቁኑት ዱአን በተመለከተ ሱናው እንዴት እንደሆነ ቢያብራሩልን። የተወሰነ ዱዓ አለውን? በዊትር ሰላት ላይ ማስረዘምስ ይቻላልን? ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሒመሁላህ



Taju Nasir
ጥያቄ፦ የቁኑት ዱአን በተመለከተ ሱናው እንዴት እንደሆነ ቢያብራሩልን። የተወሰነ ዱዓ አለውን? በዊትር ሰላት ላይ ማስረዘምስ ይቻላልን?
መልስ፦ ከቁኑት ዱዓ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሐሰን ኢብኑ ዓሊይ ያስተማሩት ይገኝበታል፦ « አላሁመዲኒ ፊመን ሀደይተ ወዓፊኒ ፊመን ዐፈይተ…» በማለት (ቲርሚዚ)። ዱአዑ የታወቀ ነው። ኢማሙ የሚለምነው ለራሱና ለተከታዮቹም ስለሀሆነ « አላሁመዲና» (አላህ ሆይ! ምራን) ማለት ነው ያለበት። ሌላ ተስማሚ ዱዐ ቢያክልበትም ችግር የለውም። ነገር ግን በማእሙሞች ላይ በሚከብድ መልኩ ማስረዘም የለበትም። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙዓዝን በሰዎች ላይ ሰላት በማስረዘሙ ምክንያት « አንተ ሙዓዝ ፈታኝ ነህ እንዴ?» በማለት ተቆጥተውታልና፥፥(ብኻሪ)።
ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሒመሁላህ

Post a Comment

0 Comments