Ibnu Munewor
ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለቱልቀድር ዙሪያ
በቅድሚያ “ለይለቱልቀድር” ማለት ምን ማለት ነው? ከዑለማዎች1. “ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው” ያሉ አሉ፡፡2. “ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው” ያሉም አሉ፡፡የለይለቱልቀድር ደረጃዎች1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡ ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተልቀድር አወረድነው፡፡” [አልቀድር፡ 1]2. የተባረከች ወር ናት፡፡ ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው፡፡” [አድዱኻን፡ 3]3. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡ ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡” [አድዱኻን፡ 4]4. በሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየ ምንዳው የበለጠ ነው፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ለይለተልቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት፡፡” [አልቀድር፡ 3]5. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡” [አልቀድር፡ 4]6. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው፡፡ [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]7. ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡ ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡” [አልቀድር፡ 3]8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡ አልኢማም ኢብኑልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ (ማለትም አመቱን ሙሉ በመፈለግ) የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡ በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!” []በዳኢዑልፈዋኢድ፡ 1/55ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፡፡ ከረመዳንም ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸው ነው፡- “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፡፡ ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፡፡ ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ ተባለኝ” ማለታቸው ነው፡፡ ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ (በረመዳን) ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፡፡ የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል፡፡” [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]መቼ እንፈልጋት?ባይሆን እጅግ የምትገመተዋ ለሊት 27ኛዋ ለሊት ናት፡፡ ለዚህም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸው ማስረጃ መሆን ይችላል፡- “ለይለተልቀድርን በሃያ ሰባተኛው ለሊት ውስጥ ፈልጓት፡፡” [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ይሁን እንጂ “ለይለተልቀድርን በሃያሶስተኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተልቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት፡፡ ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ ሰባት ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተልቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል፡፡ በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው፡፡ ይህን አስመልክተው መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተልቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት፡፡” [ቡኻሪናሙስሊም] ይህ ማለት ግን ከናካቴው በሸፍዕ ለሊቶችም ማለትም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ለማለት አይደለም፡፡ ይህንንም ከሚያስረዱን ማስረጃዎች አንዱ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ለይለተልቀድርን በረመዳን የመጨረሻዋ ለሊት ላይ ፈልጓት” ማለታቸው ነው፡፡ [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ወሩ 30 ቀናት ከሆነ የመጨረሻው ለሊት ዊትር ቁጥር እንዳልሆነች ይስተዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የሚፈልጋት ሰው በመጨረሻዎቹ አስር ይፈልጋት” በሌላ ዘገባ ደግሞ “የሚፈልጋት ሰው በመጨረሻዎቹ ሰባት ለሊቶች ይፈልጋት” ማለታቸው ይህን ያስረዳል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ይህ አነጋገራቸው ዊትር ያልሆኑት ለሊቶች ተገንጥለው እንደማይወጡ ያሳያል፡፡ በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ዘገባ ላይ እንደመጣው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተልቀድር ከረመዳን በመጨረሻው አስር ፈልጓት፡፡ ዘጠኝ ሲቀር፤ ሰባት ሲቀር፤ አምስት ሲቀር፡፡” [ቡኻሪ] ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው፡፡ ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት፡፡ ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል፡፡ ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ይበልጥ የሚተኮረው በዊትሩ ሊሆን ይገባል፡፡በለይለተልቀድር ጊዜ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?ዒባዳህ ማብዛት፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው፡፡ምልክቶቿ1. “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች፡፡” [ሙስሊም]2. በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል፡፡ ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች፡፡ [ሶሒሑልጃሚዕ]ሸይኹልአልባኒ ረሒመሁላህ እንደሚሉት እነዚህ ምልክቶች አንፃራዊ ናቸው፡፡ በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስለሆነም በትክክል ለይለተልቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል፡፡ለይለተልቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!!የወር አበባ ደም ላይ ያሉ፣ የወሊድ ደም ላይ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም፡፡ ማስረጃው ጠቅላይ ነውና፡፡ ባይሆን በዚክርና መሰልዒባዳዎች ሊበራቱ ይገባል፡፡ ይህን የሚጠቁም ሀሳብም ከመልካም ሰለፎቻችን ተገኝቷል፡፡ በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው፡፡ እንዳውም ሱፍያኑ አሥሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ፡፡ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው፣ ወሬያቸውን እየፈጩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ፡፡ የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው፡፡ እሱን ሲያልፍ ሲመለከቱ “አኑረን አክብረን” ብለው በህብረት ይንጫጫሉ፡፡ ይሄ እዚህ ግባ የማይባል ባዶ እምነት ነው፡፡ ለይለተልቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ሊጠመዱ የሚገባቸውም በዒባዳ፣ በዚክር፣ በሶላት፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን እንጂ በወሬ መሆን የለበትም፡፡ ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተልቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም፡፡ለይለተልቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተልቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አልሏሁመ ኢንነከ ዐፉውዉን ቱሒቡልዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ፡፡ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፡፡ ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው፡፡ [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]ስለዚህ ዋናው ልናተኩርበት የሚገባን በዱንያም በአኺራም ከአላህ ይቅርታን እንድናገኝ መጣጣር ነው፡፡ግን ለምን አላህ ለይለተልቀድርን ስውር አደረጋት?ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳህ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት፡፡ እናም ለይለተልቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ይበልጥ በዒባዳህ ላይ ይቆያሉ፣ ይነቃቃሉም፡፡ በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ፡፡ ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹን ለሊቶች ሊዘናጉ ይችሉ ነበር፡፡ እናም መሰወሯ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው፡፡ [ቡኻሪ]አላህ ይቺን ታላቅ ለሊት ያድለን፡፡ የምንጠቀምባትም ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡ መልካም ሆኖ ካገኙት ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያድርጉ፡፡