Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዒድ ጁምዓ(ዓርብ) ዕለት ከዋለ


ዒድ ጁምዓ(ዓርብ) ዕለት ከዋለ
የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ በቁጥር 21160 ካወጣው መግለጫ ተከታዮቹን ሀሳቦች ጠቅሷል።
· ኢማሙ ሰላተል ጁምዓ እንዲሰገድ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጁምዓ ለመስገድ በቂ ሰዉ ካልተገኘ ዙህርን ያሰግዳል።
· ሰላተል ዒድ የሰገደ ሰው የጁምዓ ሰላትን ባይገኝ ይፈቀድለታል። ዙህርን በወቅቱ ይሰግዳል። ሆኖም ግን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ጁምዓን ቢሰግድ የተሻለ ነው።
· የዒድን ሰላት ያልሰገደ ግን ይህ ፍቃድ አይመለከተዉም። ጁምዓን የመስገድ ግዴታ አለበት።
· በዚህ እለት ጁምዓ በሚሰገድባቸዉ መስጂዶች ሲቀር የዙህር አዛን አይደረግም።

Post a Comment

0 Comments