በሳዳት ከማል አቡ መርየም...✍
ረመዳን የአንድነት ወር
============
አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙትን በታዘዝነው መሰረት አቅም በቻለው መጠን መፈፀም፤ የከለከሉትን ደግሞ በቁርጥ መራቅ የአንድነት ምንጭ ነው፡፡
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ››፤ ‹‹የሃጅ አፈፃፀምን ከእኔ ውሰዱ›› ነበር ያሉት፤ ውዱእ አደራረጋቸውን ታላቁ ሰሃባ ኡስማን (ረድየላሁ አንሁ) ውዱእ አድርጎ ካሳየ በኋላ ‹‹ይህ ነበር የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ውዱእ አደራረግ›› አለ፡፡
ልክ እንደዚህ ሁሉ ማንኛውንም የአምልኮ ትእዛዝ ለአላህ ብቻ በመፈፀም እና ከሽርክ በመራቅ፤ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በመተግበር እና ቢድዐን በመራቅ፤ የሰሃባዎችን አረዳድ በመያዝ ወደ እውነተኛ አንድነት መምጣት ይቻላል፤ ልዩነቶችን ማጥበብ ይቻላል፡፡
ሱሁር መብላት ‹‹የቤተሰብን ፍቅር እና አንድነት ያጠናክራል››፤ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱሁር መብላት በረካ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
አላህ እና መልክተኛው ያዘዙትን በአቅማችን ልክ በመስራት፤ የከለከሉትን በቁርጥ በመራቅ የሰሃባዎችን አረዳድ በመያዝ አላህ ወደ እውነተኛ አንድነት መርቶን ሽርክ እና ቢድዐ ላይ ድልን ከሚጎናፀፉት ያድርገን፡፡

0 Comments