Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹እንግሊዝ ውስጥ የሚፆመው ረመዳን ማጠር አለበት›› ይላል ጠሞ አጥማሚው ኡሳማ ሀሰን (አላህ ይምራው)፡፡

አላህ ከእንደዚህ አይነት ጠሞ አጥማሚዎች በረመዳንም ይሁን ከረመዳን ውጭ ይጠብቀን፡፡
‹‹እንግሊዝ ውስጥ የሚፆመው ረመዳን ማጠር አለበት›› ይላል ጠሞ አጥማሚው ኡሳማ ሀሰን (አላህ ይምራው)፡፡
ይህ ግለሰብ ‹‹የሰው ልጅ ከጦጣ ነው የመጣው›› የሚለውን የዳርዊን ኩፍር ፍልስፍና ኢስላም ውስጥ ለማስገባት አፉን ሞልቶ የተጣራ ነው፡፡
እንደዚህ ሰው ፍልስፍና ከሆነ አጭር ሰዓት የሚፆሙትን ሙስሊሞች ሰዓት ይጨመርባቸው ሊል ነውን?
አላህ ጥበበኛ አዛኝ ነው፣ በየአመቱ ቀናት ስለሚቀያየሩ የተወሰነ ግዜ ረዥም ፆም የፆሙት በሌላ ግዜ ደግሞ ወቅቱ ያንስላቸዋል፡፡ አላህም ረዥም ፆም የሚፆሙ ወንድም እና እህቶቻችንን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላቸው፣ የእኛንም ፆም ይቀበለን፡፡
የፆም ወቅቱ ጎህ ከቀደደ አንስቶ ፀሃይ እስከጠለቀችበት ነው፡፡
ሸይጧን አዛኝ መስሎ ነው አደምና ሃዋን፣ የኑህን ህዝቦችም ይሁኑ ሌሎችን የሚያጠመው፡፡
እንግዲህ እንደዚህ አይነቶቹ ሲጋለጡ ነው ኡለማ ተነካ የሚሉት አንዳንዶች፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጠኞችም ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉለት ‹‹ኡለማ፣ አዋቂ›› ብለው ነው የጠሩት፡፡
ሸይጧን ሁለት አይነት ነው የጂን እና የሰው፡፡ አላህ ከ2ቱም ተንኮል ይጠብቀን፡፡

Post a Comment

0 Comments