Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እናንተ የአላህ ባሪያዎች ፅኑ!!ኢኽዋንን የማታውቁት ስለ ኢኽዋኖች ጠንቅቃችሁ ልታውቁ ይገባል።

እናንተ የአላህ ባሪያዎች ፅኑ!!
————————————
አአላሙ አአይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ግን ለምን??
____________________________________
ኢኽዋንን የማታውቁት ስለ ኢኽዋኖች ጠንቅቃችሁ ልታውቁ ይገባል።ያልገባችሁ ግን ለምን አህባሽን እንደምትቃወሙት ለምን ኢኽዋንንም አትቃወሙም?ለምንስ አህባሽ ማነው ብላችሁ እንደጠየቃችሁት ሁሉ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ማነው ብላችሁ ለምን አትጠይቁም?? እንደማስበውና እንደሚገባኝ ከሆነ አንዳንድ ወንድሞች አህባሽን ሳያውቁት ይጠሉትና ልክ አህባሽን እንዲጠሉት የነገራቸው ሰው እሱብቻ ሀቅን የያዘ ስለሚመስላቸው በዛ ሰው መሪና ፍሬን ይንቀሳቀሳሉ።ንቁ ሙስሊም ሁለት ጊዜ አይታለልም። እንጠይቅ እንቅራ እንወቅ ወላሂ ብዙ ሰወች ሳያዉቁት የኢኽዋንን ባንዲራ ያራግባሉ። ለዚህም ይህንን እንዲያደርጉ ከኢኽዋኖች የሚወጉት መርፌ አለ። እርሱም.
1) መድኸሊ የሚባል እምነት መንግስት ከየመን አስመጥቷል ይባላሉ። ታዳ እስኪ መድኸሊ የሚባል እምነት ባይኖርም ሳኡዲ ውስጥ ካሉት ምርጥ የሱና ኡለማወች ውስጥ ሸይኽ ረቢእ አልመድኸሊ ኢኽዋኖችን በመረጃ ስለሚያንኮታኩቱ ይህ ስም ተሰጥቷቸዋል ግን ይህ ሰው ምንድን ነው ስህተቱ ብለን ኪታቦቹንና ዳእዋወቹን ማየትና ሌሎች የሱና ኡለሞች ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ሸይኽ ኡሰይሚን፣ ሽይኽ ሷሊህ አልፈውዛን እንዲሁም ሸይኹል አልባኒ ሸይኽ ረስላን እንዲሁም ሌሎች ምን አሉ ብለን በእርሱ ላይ የተሰጡ ፈተዋወችን ማየት ነው
2) አንድነታችን እንዳይጠፋ የሚል መርፌ፣ሲጀመር አንድነት የት አለንና ማለትም የሱና ባለቤትና የቢድአእ ባለቤት አንድ ሁነው አያውቁም አንድነት ካላችሁ ለምን አህባሽ ይላላችሁ ለምንስ ከመስጅድ ወጣን ለምንስ ያሁሉ ሰው ታሰረ ለምን ተሰደደ ለምን ተገደለ ለተዉሂድ ከሆነ አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ ግን ለምን አህለል ሱናወችን መድኸልይ ትላላችሁ
3) ኢኽዋኖች በነሻጣ በስሜት ብቻ ለዲኑ የሚሞትን እውቀት አልባ ግን አካዳሚካል የተማረ ሰው በመፈለግ ፖለቲካቸውን በማጠጣት እነሱን እንዲከተል ምንም ጥያቄ እንዳያነሳ ማድረግ
4)ሁሉም ፊርቃ አንድ ሁነን ነስር ከመጣ ቡሀላ እንደፈለግን እንሆናለን በሚል ጅል ሀሳብ አላህ ደግሞ ይህንን ሲነቅፈው (አንድ ናቸው ብለህ ታስባለህ ግና ቀልቦቻቸው ተለያይቷል )
5) መንግስት ተቃውሞውን ማስቆም ስላልቻለ ሊከፋፍለን ነው። ታዳ እንዳንከፋፈልን ከፈለግን በቁርአንና በሀዲስ ለምን አንሰራም ለምን በተውሂድና በሱና ላይ አደራ አንባባልም ለምንስ በሽርክ ላይ እና በቢድአ ላይ አናስጠነቅቅም ለነገሩ ኢኽዋኖች ተውሂድና ሱናን የሚያስተምር ካዩ ከፋፋይ ሽርክንና ቢድአን የሚያስጠነቅቅ ካዩ ካድሬ ይላሉ ለመሆኑ ከመቸ ጀምሮ ካድሬወች ሽርክንና ቢድአን አስጠነቀቀቁ ከአህባሽ ጋርስ ምን አጣላንና
6)ሁሉም ባሉበት ሉኢስላም ከሰሩ ነስር ይመጣል ይላሉ።ታዳ ለኢስላም ሲሰራ እኮ ስርአትና ደንብ አለው ቁርአንና ሀዲስ በሚደግፈው መልኩ እንጅ ፍሬን የሌለው መኪና ይመስል ቀጥታ መሮጥ የለም
7)ኢትዮጲያ ውስጠ ኢኽዋን የለም ይላሉ። ታዳ ኢኽዋን ከሌለ ለምን የኢኽዋን አንጃወች ሲነሱ ለምን ታብዳላችሁ ለምሳሌ ሰይድ ቁጥብ ሀሰነልበና የአሁኑ ጤነኛነቱ የማያስታውቀው ምንም የዲን እውቀት የሌለው ዩሱፍ አልቀርዷዊ አኢደል ቀርኒ.... ስታነሳና ሰወች እነሱም የአቂዳ ችግር እንዳለባቸው ስታስተምር ታብዳላችሁ እውነት ሀቅን ፈላጊ ከሆናችሁ ለምን ለነሱ ጥብቅና ትቆማላችሁ ታዳ ለምን ለአብዱላህ ሀረሪ ለምን አትቆሙም ከእነሱም ሱሀባን የሚሳደብ አለ ሽርክና ቢድአን ይደግፋሉ
ግን ለምን
ግን እውነት ኢኽዋኖች ሀቅላይ ከሆናችሁ ለምን ሰውን ሳታውቁ ትፈርጃላችሁ ለምሳሌ በተውሂድ ላይ ክንዱን ወጥሮ የሚያስተምረንን ወንድም ሳዳትን ብዙ ብላችሁታል ከኳእሱም አካውንት ጋር የሚመሳሰል አካውንት ከፍታችሁ ሰዉ ሀቅን እንዳይቀበል ታምታታላችሁ ልክ እንደወያኔ ሰውን አስቀድማችሁ ብላችሁ ትፈርጃላችሁ ስትፈልጉ ካድሬ ስትፈልጉ ከፋፋይ ስትፈልጉ መድኸልይ ሰውን በኮሜንት ትሳደባላችሀ ለዛውም ከሙስሊም የማይጠበቅ ስድብ ታዳ አካውንታችሁ ነው ሙስሊሙ እናንተ? የአህባሽን የተብሊጉም የሱፍያዉም የሽአውም አያስቸግር ምክንያቱም በግልፅ በግልፅ ስለሚናገሩ ኢኽዋኖች ግን ለዲን የሚቆረቆሩ የ አህለል ሱናን ማሊያ ስለሚለብሱ ትንሽ ያስቸግራሉ ቢሆንም በሱና ኡለማወች ይታወቃሉና አትጨነቁ ።
ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎቻችን አረዳድ ከተረዳን ወላሂ በሀቅላይ የተሰባሰብን ምርጥ አንድነት ይማጣል ደሞም ቁርአንና ሀዲስ እያለ ጥሩው ቆሻሻው ጋር አንድ አይሆንምና አንድነት ትንሽም ቢሆን በሀቅ ላይ ነው
ግን ለምን????

Post a Comment

0 Comments