Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለአህባሾች እና ለሱፍዬች? ለምንድን ነው ኡመር ኢብነል ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ወደ አላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀብር ሄዶ አላህን ዝናብ ያልጠየቀው?

ለአህባሾች እና ለሱፍዬች?
==============
ለምንድን ነው ኡመር ኢብነል ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ወደ አላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀብር ሄዶ አላህን ዝናብ ያልጠየቀው?
ለምንድን ነው ወደ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አጎት አባስ (ረድየላሁ አንሁ) የሄደው?
ከአነስ በተዘገበ
ድርቅ ሲያስፈራቸው (ሲያሰጋቸው) ኡመር ኢብነል ኸጣብ አባስ ኢብን አብድል ሙጠሊብን አላህን ዝናብ እንዲያዘንብ እንዲጠይቅ ይጠይቀው ነበር፡፡ (ኡመር) እንዲህም ይል ነበር ‹‹ያ አላህ! ነብያችንን ዝናብ እንድታዘንብልን እንዲጠይቁህ እንጠይቅ ነበር አንተም ዝናብ ትለግሰን (ታዘንብልን፣ ትባርከንም) ነበር አሁን ደግሞ አንተ ዝናብ እንድትሰጠን እንዲጠይቅህ አጎታቸውን እንጠይቀዋለን፡፡ አላህ ሆይ! ዝናብ አውርድልን (አዝንብልን)›› እናም ይዘንብ ነበር፡፡ ሰሂህ አል ቡኻሪ

ቀብር ላይ ሄዶ አላህን መለመን፣ በረካን በፈለግ (ተወሱል) የሚቻል ቢሆን ኖሮ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ታላቁ ሰሃባ፣ አሚረል ሙዕሚኒን) ምርጥ ወደሆነው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀብር አይሄድም ነበርን
አህባሾች፣ ሱፍዬች ከኡመር ኢብኑል ኸጣብ ረድየላሁ አንሁ በላይ ያውቃሉን?
ከኡመር የበለጡ የተመሩ፣ የተቀኑ፣ የገባቸው ናቸውን?
ይህ ነው እውነታው፡፡
የአደም ልጅ ከሞተ በኋላ ስራው ይቋረጣል ይሉናል ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡ በህይወት ያለ ሰው ልክ በሰሃባዎች ምሳሌ የረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አጎት አባስ ወይንም አላህን ፈሪዎች በየዘመኑ ያሉ ዝናብ ሲጠፋ ዱዓ አድርገው አላህን እንዲለምኑት ይጠየቃሉ፡፡
ከዚህ ውጭ ቀብር ላይ ተሂዶ የቀብር ባለቤቶች አይለመኑም፡፡ ተውሂድ ማለት አላህን በብቸኝነት ማምለክ እና ከእርሱ ውጭ ያሉትን በጠቅላላ መራቅ ነው፡፡