Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የእናቶችን ቀን ሙስሊሞች እንዴት ያዩታል?

Salah Ahmed's photo.
የእናቶችን ቀን ሙስሊሞች እንዴት ያዩታል?
እኛ ሙስሊሞች፤ እናትን በመታዘዝ፣ ለእናት መልካም በመዋልና አሷን በማስደሰት ታዘናል። እናትን ከመበደልና በሷ ላይ ከማመፅ በእጅጉ ተከልክለናል። ለእናት ክብር እንሰጥ ዘንድ በእርግዝና ወቅት ምን ያክል ድካምና እንግልት እንደሚገጥማት ቁርአን ይነግረናል።
(ﻭَﻭَﺻَّﻴْﻨَﺎ اﻹِْﻧﺴَﺎﻥَ ﺑِﻮَاﻟِﺪَﻳْﻪِ ﺣَﻤَﻠَﺘْﻪُ ﺃُﻣُّﻪُ ﻭَﻫْﻨًﺎ ﻋَﻠَﻰٰ ﻭَﻫْﻦٍ ﻭَﻓِﺼَﺎﻟُﻪُ ﻓِﻲ ﻋَﺎﻣَﻴْﻦِ ﺃَﻥِ اﺷْﻜُﺮْ ﻟِﻲ ﻭَﻟِﻮَاﻟِﺪَﻳْﻚَ ﺇِﻟَﻲَّ اﻟْﻤَﺼِﻴﺮُ) لقمان 14
«ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡»፣ ሉቅማን [31:14]

እኛ ዘንድ እናትን ማገልገል በህይወት ዘመኗ ብቻ ሳይሆን ከሞተችም በኃላ ይቀጥላል። ለምሳሌ፤ የእናትን ኑዛዜ ተግባራዊ ማድረግ፣ ዱዓ ማድግ፣ ከአላህ ማርታን መጠየቅ፣ ቤተሰቧንና ጓደኞቿን ማክበር፤ አንድ ሙስሊም ለእናቱ ያለውን ክብር የሚገልፅባቸው ተግባራት ናቸው። በጥቅሉ እናትን ማስደሰት ለጀነት ከሚያበቁ ታላላቅ መልካም ስራዎች ይመደባል።
በኢስላማዊ ሸሪዓ ለእናት የተሰጠውን ክብር በየትኛውም ምድራዊ ህግ ወይም ሀይማኖት አናገኘውም። እናትን አስመለክቶ የተጣለብን ሀላፊነት ከአባት የበለጠ መሆኑም ተገልፆልናል።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ : [جَاءَ رَجُلٌ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، مَنْ أَحَقُّ النَّاسِ بِحُسْنِ صَحَابَتِي ؟ قَالَ : أُمُّكَ . قَالَ : ثُمَّ مَنْ ؟ قَالَ : ثُمَّ أُمُّكَ . قَالَ : ثُمَّ مَنْ ؟ قَالَ : ثُمَّ أُمُّكَ . قَالَ : ثُمَّ مَنْ ؟ قَالَ : ثُمَّ أَبُوكَ] رواه البخاري ومسلم
አቡ ሁረይራ እንዲህ ብለዋል፤
«አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ ﷺ ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው፤ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከማንም በላይ መልካም ልውልለት የሚገባ ሰው ማነው? በማለት ጠየቀ። "እናትህ" አሉት። ቀጥሎስ? አላቸው። "እናትህ" አሉት። ቀጥሎስ? አላቸው። "እናትህ" አሉት። ቀጥሎስ? አላቸው። "አባትህ" አሉት።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
☞ የእናቶች ቀንን ማክበር እንዴት ይታያል?
ኢስላም ለናት ታላቅ ክብርን አጎናፅፏል። ይሁንና "የእናቶች ቀን" በማለት በአመት አንድ ቀን ብቻ እንድትከበር አላዘዘም። ይህንን በዓል አድርጎ ማክበር በዲናችን ያልነበረ መጤ ፈጠራ ነው። መልእክተኛው፤ እንዲሁም ሰሀቦችም ይሁኑ የዚህ ኡማ ታላላቅ መሪዎች ሁሉ አልፈፀሙትም።
መልእክተኛው ﷺ ከቢድዓ ሲያስጠነቅቁ እንዲህ ብለዋል፤
(وشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا ، وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ) رواه مسلم والنسائي وزاد:(وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ).
«የነገሮች ሁሉ ክፉ፤ (በዲን ውስጥ) አዳዲስ ፈጠራዎች ናቸው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው!» ሙስሊም ዘግበውታል
ነሳኢ ደግሞ ተከታዩን ጨምረው ዘግበውታል፤
«ጥመት ሁሉ ደግሞ የእሳት ነው።»
ይህ ተግባር ቢድዓ ከመሆኑም በተጨማሪ ከካፊሮች ጋር መመሳሰል ነው። ሙስሊም በማንነቱ ሊኮራና ምርጥ የሙስሊም ትውልዶችን አርአያ ሊያደርግ እንጆ የሌሎች ጭራ ሊሆን አይገባም።
የሚገርመው ይህ በአል የመጣብን የወላጆች ክብር ከጠፋባቸውና በደል ከተንሰራፋባቸው ማህበረሰቦች መሆኑ ነው። ወላጆቻቸውን የአዛውንቶች መጦርያ ጥለው በአመት እንኳ ለመጠየቅ ፍቃደኛ የማይሆኑ ሰዎች ከበዙባቸው ሀገራት ነው። እነሱ ዘንድ ወላጆችን ማስከፋትና መበደል እጅጉን ተንሰራፍቷል። ይህም ስለሆነ እናታቸውን የሚያስታውሱበትን ቀን መመደባቸው አይገርምም። በእናቶች ቀን የሚፈፅሙት መልካም ስራ አመቱን ሙሉ የሳዩትን ጉድለት የሚያጣጣ ይመስላቸዋል።
እኛ ሙስሊሞች ዘንድ አመቱን ሙሉ እናትን ማገልገል ተገቢ ነው። ለመሆኑ፤ በአመት አንድ ቀን መርጦ እናት እናት ማለት እና ማሟሟቅ ምን ትርጉም አለው?።
ሸይኽ ኡሰይሚን እንዲህ ብለዋል፤
«እናት፤ በአመት አንድ ቀን ብቻ ትኩረትን ከመቸሯ የበለጠ ሀቅ አላት። እንደውም ልጆች እናታቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው። እንደዚሁ፤ ከአላህ ትእዛዝ ጋር እስካልተጋጨ ድረስ እናትን በማንኛውም ጊዜና ቦታ መታዘዝ ግዴታ ነው። » መጅሙዑል ፈታዋ 2/301
እዝነትና መልካምነትን ያቀፈ ነውና ይህንን ታላቅ ዲን ጠንክረን እንያዝ! በርሱም እንብቃቃ፤ ስርአትና ድንጋጌዎቹንም እንተግብር።
ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው!
ወንድማቸሁ አቡጁነይድ