Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፡- የፆም ኒያ ከእያንዳንዱ የረመዳን ሌሊት ከፈጅር በፊት መሆኑ ሸርጥ (መስፈርት) ነው ወይስ ለወሩ ባጠቃላይ አንድ ኒያ ይበቃል? በእያንዳንዱ የረመዳን ሌሊት በቃል መነየቱስ ብይኑ ምንድን ነው? ከሸይኽ ፈውዛን

ጥያቄ፡- የፆም ኒያ ከእያንዳንዱ የረመዳን ሌሊት ከፈጅር በፊት መሆኑ ሸርጥ (መስፈርት) ነው ወይስ ለወሩ ባጠቃላይ አንድ ኒያ ይበቃል? በእያንዳንዱ የረመዳን ሌሊት በቃል መነየቱስ ብይኑ ምንድን ነው?
መልስ፡- ፆምን ይሁን ሌላ ዒባዳ ትክክለኛ ይሆን ዘንድ ኒያ ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች አንዱ መስፈርት ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ስራዎች (የሚታሰቡት) በኒያዎች ብቻ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ደግሞ ያሰበው ብቻ ነው ያለው” ብለዋልና፡፡ ሁሉም ዒባዳ ያለ ኒያ ዋጋ የለውም፡፡ ፆምም ከነዚሁ ነው ያለ ኒያ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ኒያውን ከሌሊቱ ያላሳደረ ፆም የለውም” ብለዋልና፡፡” ስለዚህ ኒያ የፆም መስፈርት ነው፡፡ ግዴታ የሆነ ፆም የግድ ፈጅር ከመውጣቱ በፊት በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ መነየት (መታሰብ) አለበት፡፡ ለእያንዳንዱ ቀን አዲስ ኒያ ሊነይት የግድ ይላል፡፡ ምክኒያቱም የእያንዳንዱ ቀን ፆም ቀናት በተተካኩ ቁጥር አዲስ ኒያ የሚሻ እራሱን የቻለ ዒባዳ ነውና፡፡ ምክኒያቱም “ስራዎች (የሚታሰቡት) በኒያዎች ብቻ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ደግሞ ያሰበው ብቻ ነው ያልለው” የሚለው የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ጠቅላይ ነውና፡፡
ከእንቅልፉ ተነስቶ ስሑር ከበላ ይሄ በራሱ ኒያ ነው፡፡ ከመተኛቱ በፊት ነይቶ ከሆነ ፈጅር ከወጣ በኋላ ቢነቃም ኒያው ስለተገኘ ከአስፈጣሪ ነገር መታቀብ አለበት፡፡ ፆሙ ትክክል ነውና፡፡
ኒያን በቃል መናገርን በተመለከተ ጠያቂው ያነሳው ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም? ኒያን በቃል መናገሩ አይፈቀድም፡፡ ቢድዐ ነው፡፡ ምክኒያቱም ኒያ ከልብ ስራዎች ውስጥ ነውና፡፡ እሳቤዎችን የጠራውና ከፍ ያለው አላህ እንጂ ማንም አያውቃቸውም፡፡ እሱ ደግሞ መናገር ሳያስፈልግ ያውቃቸዋል፡፡ ነብዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቃል ይነይቱ እንደነበር የሚጠቁም ማስረጃ አልመጣም፡፡ … )) ከሸይኽ ፈውዛን (ፈታዋ ሸህሪ ረመዳን) የተወሰደ ነው፡፡

Post a Comment

0 Comments