Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆምን ያጠፋሉ ወይሰ አያጠፉም? በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ፆምን ያጠፋሉ ወይሰ አያጠፉም? (በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች)
1— በፊንጢጣ የሚወሰድ መድሀኒት ኪኒን  (ፆምን አያበላሽም) ሸይኽ ዑሰይሚን
2— የዐይን ጠብታ  (ፆምን አያበላሽም) ኢብኑ ተይሚያህ፣ኢብኑ ባዝ ዑሰየሚን ረሂመሁሙላህ አጅመዒን
3— ኩል  (ፆምን አያበላሽም) ኢብኑ ተይሚያህ፣ ኢብኑ ባዝ ዑሰይሚን
4— የጆሮ ጠብታ (ፆምን አያበላሽም) ኢብኑ ተይሚያህ፣ኢብኑ ባዝ ዑሰይሚን
5— በአፍንጫ የሚወሰድ ጠብታ (ወደ ሆድ የሚደርስ ከሆነ ፆምን ያበላሻል።) ሸይኽ ዑሰይሚን
ኢብኑ ባዝ ደግሞ "በአፍንጫ የሚወሰድ ጠብታ ፆመኛ መጠቀም አይኖርበትም ተጠቅሞም ጉሮሮው ላይ ጣዕሙን ካጣጣመ በሌላ ጌዜ ቀዳ መክፈል ይኖርበታል።" ይላሉ።

6— ፆመኛ መታፈን ሊያስከትሉ የሚችሉ በሽታዎች (አንደ አስም)ባሉ በሽታዎች የተነሳ የሚከሰቱ የአየር እጥረት መከላከያ መውሰዱ ፆምን አያበላሽም።
7— የአየር እጥረት መከላከያ ኦክሲጅን ፆምን አያበላሽም። (ሸይኽ ሰዐድ ኸስላን)
8— ምግብን ሊተኩ የሚችሉ መርፌዎች(ጉሉኮስ) ፆምን ያበላሻል። በጡንቻ ወይም በውጫዊ አካል የሚወጋ መርፌ ፆምን አያበላሽም። (ኢበኑ ባዝ እና ዑሰይሚን)
9— ስኳር በሽተኞች የሚወጉት መርፌ (ኦነሶሊን መርፌ) ፆምን አያበላሽም። የለጅነት ዳኢማ ፈትዋ።(ይቀጥላል)

Post a Comment

0 Comments