Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፈርድ ሶላት የሚሰግድ ሠው ትርፍ ሶላት የሚሰግድን ሠው ተከትሎ መስገድ ይቻላልን? ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁሏህ)

ፈርድ ሶላት የሚሰግድ ሰው ትርፍን ሶላት የሚሰግድን ሰው ተከትሎ ቢሰግድ
ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁሏህ) ቱህፈቱል አኽዋን በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ካሰፈሩት ፈታዋ መካከል
ጥያቄ 41፡- ፈርድ ሶላት የሚሰግድ ሠው ትርፍ ሶላት የሚሰግድን ሠው ተከትሎ መስገድ ይቻላልን?
መልስ41፡- ፈርድ የሚሰግድ ሠው ትርፍ ሶላትን በሚሰግድ ሠው ተከትሎ ቢሠግድ ችግር የለውም።ይህም ነብዩ (ሠ.ዐ.ወ) ሶላተል ኸውፍን ሲያሰግዱ በተገኘው መረጃ መሰረት ነው ፡፡
መጀመሪያ የተወሰኑትን ሶሃቦችን ሁለት ረክአህ አሠግደው አሰላመቱ ። ይህ ለነብዩም ሆነ አሁን ለሠገዱት ሶሀቦች ፈርድ ሶላት ነው። ከዛ በኋላ ደግሞ ሌሎችን ሶሀቦችን ሁለት ረክአህ አሰገዷቸውና አሰላመቱ። ይህ ደግሞ ለነብዩ ትርፍ ሶላት ሲሆን አሁን ለሰገዱት ሶሀቦች ደግሞ ፈርድ ሶላት ነው።
ቡኻሪይና ሙስሊም እንዳስተላለፉት ሙዓዝ ኢብኑል ጀበል የተባለው ሶሀባ ከነብዩ ጋር የዒሻእን ሶላት ይሰግድና ወደ ህዝቦቹ በመሄድ የዒሻእን ሶላት እንደገና ያሰግዳቸው ነበር። ለእርሱ ትርፍ ሶላት ሲሆን ለነርሱ ግን ፈርድ ሶላት ነው። ልክ እንደዚሁ አንድ የዒሻእ ሶላት ያልሰገደ ሰው ተራዊህ የሚሰግዱ ሰወችን ቢያገኝ ከነርሱ ጋር ተቀላቅሎ የዒሻእን ሶላት በመስገድ የጀማዓህን (የህብረት ሶላትን) አጅር ማግኘት ይችላል። ይህም እነርሱ ሁለት ረክዓህ ከሰገዱ በኋላ ሲያሰላምቱ ቆሞ አራት ረክዓህ በማሟላት ይሆናል ማለት ነው፡፡