Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ አንዱን ሰው እንዲህ ሲል ጠየቀው “እድሜህ ስንት ነው”

ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ አንዱን ሰው እንዲህ ሲል ጠየቀው “እድሜህ ስንት ነው”
ሰውየው፡ 60 አመት
ፉዶይል፡ 60 አመት ሙሉ ወደ ጌታህ እየተጓዝክ ነው፡፡ መድረሻህ ሳይቃረብ አይቀርም
ሰውየው፡ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ( እኛ ለአላህ ነን፡፡ ወደሱም ተመላሾች ነን)
ፉዶይል፡ “ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን” የሚለውን ተፍሲሩን ታውቃለህ ለአላህ ባሪያ እንደሆነ ወደሱም ተመላሽ እንደሆነ የሚያውቅ እንደሚቆም ይወቅ፡፡ እንደሚቆም ያወቀ እንደሚጠየቅ ይወቅ፡፡ እንደሚጠየቅ ያወቀ መልስ ያዘጋጅ፡፡
ሰውየው፡ ምንድን ነው ብልሃቱ
ፉዶይል፡ ቀላል ነው
ሰውየው፡ ምንድን ነው እሱ
ፉዶይል፡ በቀረህ እድሜ መልካም ስራ፡፡ ያለፈው ይማርልሃል፡፡ ቀሪው እድሜህን ካጠፋህ ግን ባለፈውም በቀሪውም ትያዛለህ፡፡