Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጠያቂ፡- በመስጂዶች ውስጥ የሳንቲም መሰብሰቢያ ሳጥኖችን ማስቀመጥ ብይኑ ምንድን ነው? ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ ሐፊዞሁላህ

Ibnu Munewor's photo.
ጠያቂ፡- በመስጂዶች ውስጥ የሳንቲም መሰብሰቢያ ሳጥኖችን ማስቀመጥ ብይኑ ምንድን ነው?
ሸይኽ፡- ሳጥኑ ሁሌ መስጂድ ውስጥ የሚቀመጥ ነው ወይስ ጁሙዐህ ብቻ ነው? ወይ መቼ ነው?
ጠያቂ፡- ሁሌ ነው፡፡
ሸይኽ፡- ይቺ የሒዝቢዮች (የቡድንተኞች) አካሄድ ናት፡፡ እንጂ የአህሉስሱናህ አካሄድ አይደለም፡፡ ልመና ሐራም ነው፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ብቻ እንጂ አይፈቀድም ባረከላሁ ፊኩም፡፡ ልመና መሰረቱ ክልክል ነው፡፡ ልመና የሚያበዛ ሰው በቂያማ ቀን ፊቱ ላይ ቁራጭ ስጋ እንኳን ሳይኖረው ይመጣል፡፡ ገባችሁ? እናም ይቺ የሒዝቢዮች አካሄድ ናት ባረከላሁ ፊኩም፡፡ ለመስጂድ መለገስ የፈለገ ሰው ሳጥን አያስፈልግም እንዲሁ ይስጥ፡፡ እንጂ ልመና? በጭራሽ!!
ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ ሐፊዞሁላህ
ድምፃቸውን በዚህ አውርደው ማዳመጥ ይችላሉ፡፡
http://www.bayenahsalaf.com/vb/attachment.php