Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ለረመዳን ወር ከሚዘጋጁት የቀን መቁጠሪያዎች (የሰላት ጊዜያት ማሳያዎች)መካከል ባንዳንዶቹ ላይ ..... ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ


ጥያቄ፦ ለረመዳን ወር ከሚዘጋጁት የቀን መቁጠሪያዎች (የሰላት ጊዜያት ማሳያዎች)መካከል ባንዳንዶቹ ላይ የ <<አል ኢምሳክ>> የጊዜ ሰሌዳ ይጨመርባቸዋል። ይህም ከፈጅር ሰላት በአስር ወይም በአስራ አምስት ደቂቃ ቀደም ብል ነው የሚቀመጠው። ይህ ከሱና መሠረት ያለው ነገር ነው ወይስ ቢድዐ ነው? አላህ ምንዳዎን ይክፈልዎትና ያብራራሉን።
መልስ፦ ይህ ቢድዓ ነው። ከሱና መሠረት የለውም። ሱናው የዚህ ተቃራኒ ነው። አላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) በቁርአን ውስጥ እንዲህ ይላል፦
ۚ وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ ٱلْخَيْطُ ٱلْأَبْيَضُ مِنَ ٱلْخَيْطِ ٱلْأَسْوَدِ مِنَ ٱلْفَجْرِ ۖ َ
<<...ከፈጅር (ከጎህ)የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ) ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም፡፡...>> (አል-በቀራ 2፥187)
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) <<ቢላል አዛን የሚያደርገው በሌሊት ስለሆነ የኢብኑ ኡም መክቱምን አዛን እስከምትሰሙ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም፤ እርሱ ፈጅር እስከሚወጣ ድረስ አዛን አያደርግምና>> ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም)። አላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ከወሰነው ውጭ ሰዎች የኢምሳክ (የፆም መያዣ) ጊዜ ብለው የሚያስቀምጡት ነገር ውድቅ ነው። በአላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ሃይማኖት ውስጥ ከልክ ማለፍ (ተነጥጡዕ) ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << ከልክ አላፊዎች (ሙተነጥጢዑን) ጠፉ፤ ከልክ አላፊዎች ጠፉ። >> ብለዋል (ሙስሊም)
ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ

Taju Nasir