Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ከጎንደር፡፡

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ከጎንደር፡፡
ጎንደር ላይ ሰሞኑን ድንበር ከሚታለፍባቸው፣ ሽርክ እና ቢድዐ ከሚተገበርባቸው እና ከተተገበረባቸው ውስጥ
1) ሸህ አሊ ጎንደር ጁምዓ ሚያዝያ 2:: የሚያስገርመው ጁምዓ እለት እዛው ከ40 ሰው በላይ ነን ብለው ጁምዐ ሰገዱ፡፡ ሃጅ የሄዳችሁ ወንድም እና እህቶች ካስታወሳችሁ መስጂደል ኸይፍ ሚና ላይ እናኳን ጁምዐ አይሰገድበትም፡፡
እዚህ ግን የጥመት መጨረሻው እንዲህ በስሜት መዳት ሆኗል፡፡
2) ሸህ አባድር በትላንትናው እለት እሁድ ሚያዝያ 4፣
3) በዛሬው እለት ሁሌ ቀኑ ቢቀያየርም ‹‹በፋሲካ›› ማግስት ብለው የሚያከብሩት ሸህ አዘል የሚባል ባጢል አለ፡፡
ጎንደር እና አካባቢው በጣም ብዙ ሽርኮች ይፈፀሙበታል፡፡ ዱዓቶች ነብያት ያስቀደሙትን አርስት አስቀድመው ሊለፉ ግድ ይላቸዋል፡፡
አላህ በአካባቢው ያሉ የተውሂድ እና ሱና ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ወደ ተውሂድ በሚያደርጉት ጥሪ ላይ አላህ ይርዳቸው ፍሬን የሚያፈሩ ያድርጋቸው፡፡