Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢንተርኔት ጣጣ

'የኢንተርኔት ጣጣ ❗

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ• 16

󾔫ይድረስ  ለሙስሊም ወገኖቼ󾔫

   እነሆ በዘመናችን ስሩን ሰዶ ተንስራፍቶና ተሰፋፈቶ ብዙሃኑን የጠለፈው በተለይ ገና በለጋ እድሜ ያሉ ታዳጊዎችን  ከአእምሮአቸው በላይ እንዲያስቡና ያዩትንና የሰሙትን ሁሉ ያላቅማቸው ለመተግበር እንዲሞክሩ ገፋፍቷቸዋል።

  ሣይደርሱም የደረሱ እንዲሁም የሰለጠኑ አስመስሎባቸው ብዙውን ነውረኛ ተግባር በአደባባይ ሲዳፈሩት ይታያል።

  ሴቶችን ማንነታቸውን አስረሳቸው። ወንድን መምሰልና ከጎኑ እየተጋፉ መታየት እኩልነትና ነፃነት እስኪመስላቸው ለአደባባይ በቁ።

   ጥሩ ትውልድ የማፍራት ሃላፊነቷን ዘንግታ ከኢንተርኔት የምትጋበዘውን የቁሳውያን አለም ትውልድን ለማስመሰል ትሯሯጣለች።

  የባል ሀቅ ሁሉ ተሽቀንጥሮ በነፃነት ስም መብትና ግዴታ ሁሉ ተተወ።

  ብዙሃን ዘንድ የወላጅ ሃቅ ተረስቶ እኩል መመላለስ፣ የራስን ምቾትና ደስታ ማስቀደምና የመሳሰሉት የውርስ ባህሎች ተንሰራፉ።

  ጎረምሣው ወጣት ለራሱና ለዲኑ ብሎም ለሀገር ለወገኑ በሚበጅ ጉዳይ ላይ ጊዜውን ከማሳለፍ ይልቅ የጥፋት መስኮቶችን ሲከፋፍት በዩቲዩብ፣ በፌስ ቡክ፣ በኢኒስቲግራም፣በዎትስ እና  በመሣሰሉት የኢንተርኔት ቀጣናዎች ላይ በመዘፍዘፍ ለስሜታዊነቱና ለግለቱ ቤንዚን የሚያርከፈክፍበትን ሳይቶች እየተቀባበለ ገንዘቡን፣ ግዜውንና አቅሉን ሲያወድም ይውላል ያመሻል ያነጋል።

    ትውልዱ ውሸታም እስኪመስል ውሎው ሁሉ ባብዛኛው በማጭበርበር ላይ ሆኗል።

  የማይወዳትን ሴት አበድኩልሽ፣ የማያገባትን ቶሎ ወስኚ እኔ ተዘጋጀሁልሽ፣ የሌለውን ዝናና ብቃት እንዳለው በመለፈፍ ሲጀናጀን ይውላል።

  እሱ የአንዱን እህት ሲያጠምድ ሲውል፣ ሌላኛው የሱን እህት ሲያማልል ያድራል።

   እሷም አንዱን ስታነድ ትውላለች፣ ሌላኛዋ ደግሞ የሷን ወንድም ስታስዝረከርከው ታነጋለች። ይህ ሁሉ የርቀት የእብደት ሜዳ በኢንተርኔት ገፆች የሚፈፀም ነው።

   ትውልዱ ራሱን ረስቷል። መተዛዘን ቀርቷል። ከግሃዱ ወመኔዎች በባሰ ሁኔታ ባየር ላይ አእምሮዎች ተበላሽተዋል። 

   አንዱ አንዱን ያጠምዳል። አንዱ ሌላን ያከስራል። ውጤቱ ስልጣኔ ይባላል።

  ኢንተርኔትን ለኢስላም ውብ መንገዶችና ባህልን ማጥኛ ማድረግ ትተው፤ የጥመት መንገዶችን መሞከሪያ  ላብራቶሪ በማድረግ ለኪሳራ ተጠቀሙበት።

  እነዚህ ዘመን አመጣሸ የመገናኛ ብዙሃን ሃይላቸው እጅግ ብርቱ ነው። ወጣቱን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አይነት የህብረተሰብ ክፍል በመፈተንም ላይ ናቸው።

   ታዳጊውን ወጣቱንና ሴቷን መሳርያ በማድረግ ጉልማሳውንም አዛውንቶችንም እያመሰ ይገኛል።

  ወጣቱ ቤተሰቡንና ወላጆቹን ዝም ለማሰኘት በትንሽ በትንሹ እነሱን የሚስብ ነገር በማቅመስ የኢንተርኔት ሱስ ውስጥ በመዝፈቅ ጎጂ ገፁን በማሰስ መርዙን እየተረጩ ይገኛሉ።

  ጭራሽ ደህና የሚባሉቱ እንኳን ድሮ ድሮ ስላተል ጀማአን ሰፈል አወል በመጣድ ተክቢረቱል ኢህራም የማያመልጣቸው አባ ወራዎች ዛሬ ሌላ አዛን እስኪያስፈልጋቸው ድረስ ከኢንተርኔት ሜዳ አልወጣ እያሉ ነው።

  የብዙሃኑ የፌስቡክና መሰሎቹ ተጠቃሚዎች " ታይም ላይን " ሲታይ ከ" ፕሮፋይል ፒክቸር " ጀምሮ " ሼር እንዲሁም ላይክ " የሚያደርጉትና የሚሰጡት ኮሜንት አስደንጋጭ ሆኗል።

   እዚህ ላይ እንዲታወቅ የምሻው የዘመኑን አዳዲስ መገናኛዎችን ሙሉ በሙሉ እያወገዝኩ እንዳልሆነ ባልናገርም ይገባችኋል።

    ጥቅማቸውን ስናስተውል እስከዛሬ የት ነበርን የሚያሰኝ ቢሆንም፤ በጎጂው መስመር የሚጠቀሙበትን ስናስተውል ደግም ምነው በቀረብን እስከማለት ያደርሳል።

   ዋትስአፕ፣ፌስ ቡክ ፣ትዊተርና ሌሎችም ለመልካም መረጃ መቀባበያነት መገልገሉ እፎይ አሰኝቶናል።

   ለምሳሌ ለቁርአን፣ ለሀዲስ ፣ ለተጅዊድ፣ ለደርሶች፣ለሙሃደራዎች ለመሳሰሉት ብሎም ለጠቃሚ አለማዊ ትምህርቶችና ጉዳዮች መጠቀምያ ማድረግ የተቀደስ ተግባር እንደሆነ የቅርቡም የሩቁም ያውቀዋል።

   ይሁንና ትውልዱ ባብዛኛው እየተገለገለበት ያለው ሸይጣናዊው መንገድ ነገ አላህ ፊት አስጠያቂና ከወንጀሉ ማጥ ውስጥ ለመውጣትም በሸይጣን ማሳበብና ማላከክ ለፈጣሪያችን መልስ እንደማይሆን ሁላችንም ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል ።
   ወትሮውንም ይህች ዐለም የፈተና አገር መሆኗ አይረሣምና ፤ ራሳችንን ከተጋረጠብን የኢንፎርሜሽን ፈተና ማላቀቅ ግድ ይላል። ከየመደብሩ የምንገዛውን ብርጭቆ ወይም ኩባያ ለአስካሪ መጠጥ መጠጫነት ለመጠቀም እንደማንደፍር ሁሉ፤ ኢንተርኔትንም ለሀላል ኢንፎርሜሽን እንጠቀም።

   የዚህ ሁሉ ጣጣ መውጫው ወሳኙ መፍትሄ አላህን መፍራት ነው። እሱ ድብቅና የተዘነጉ ነገሮችን ሁሉ የሚያውቅ፣ የሚያይ፣ የሚሰማ፣ የሚቆጣጠር ነውና ራሳችንን ባንሸነግል መልካም ነው።

   በዚህ ጣጣ ሰበብ የሚመጣብን መቅሰፍትም እንደቀላል የሚታይና የሚመለስ አይሆንም። የችግር ግዜ እሪ ብለን ብንጮህበት ደግሞ « በገዛ እጃችሁ በሰራችሁት ነው»  ይለናልና እንንቃ❗

   ምን ላይ ተቀምጠንም ጌታችን ላይ እያመፅን እንደሆነ የዘነጋነው ይመስላል።

  የትም ተሸሽገን የኔት መስኮቶችን ብንጎለጉል፤ ሰዎች እንዳያዩብን በፓስዎር ድ ብንቆላልፍ … ከአምላካችን እንደሆን እያንዳንዷ ክስተት የምትደበቀው አይደለችም። እሱ ሰሚውና ተመልካቹ ነው። 

አላህ ንቁ እና አስተዋይ ባርያው ያድርገን።
በአቡሸረይህና & በአቡ ፈውዛን የተከተበ 1436/5/20
________
#ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ ያድርጉት ጠቃሚ ትምህርት ያገኙበታል።

www.facebook.com/tenbihat'
የኢንተርኔት ጣጣ
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ• 16
ይድረስ ለሙስሊም ወገኖቼ

በዚህ ጣጣ ሰበብ የሚመጣብን መቅሰፍትም እንደቀላል የሚታይና የሚመለስ አይሆንም። የችግር ግዜ እሪ ብለን ብንጮህበት ደግሞ « በገዛ እጃችሁ በሰራችሁት ነው» ይለናልና እንንቃ
ምን ላይ ተቀምጠንም ጌታችን ላይ እያመፅን እንደሆነ የዘነጋነው ይመስላል።
የትም ተሸሽገን የኔት መስኮቶችን ብንጎለጉል፤ ሰዎች እንዳያዩብን በፓስዎር ድ ብንቆላልፍ … ከአምላካችን እንደሆን እያንዳንዷ ክስተት የምትደበቀው አይደለችም። እሱ ሰሚውና ተመልካቹ ነው።
አላህ ንቁ እና አስተዋይ ባርያው ያድርገን።
በአቡሸረይህና & በአቡ ፈውዛን የተከተበ 1436/5/20
________
‪#‎ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ‬ ያድርጉት ጠቃሚ ትምህርት ያገኙበታል።
www.facebook.com/tenbihat