Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴት ልጅ ያለዎት እንደሆን ታድለዋል

'‎󾁅                               󾁅 
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ• 18 

ሴት  ልጅ ያለዎት እንደሆን ታድለዋል
             󾀽󾀽󾔐󾀽󾀽

  የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በጃሂሊያ ዘመን ሰዎች የነበረውን የሴት ልጆች ጭቆናና ንቀት ለማስወገድ ከጌታቸው በተላኩት መሰረት በርካታ የሴት ልጆችን ክብርና መብት የሚያስጠብቅ ትምህርቶችን ለሶሃባዎች አስተምረዋል። በተግባርም አሳይተዋል።

1ـ عَنْ أَبِي قَتَادَةَ : ( أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَرَجَ يُصَلِّي وَقَدْ حَمَلَ عَلَى عُنُقِهِ أَوْ عَاتِقِهِ أُمَامَةَ بِنْتَ زَيْنَبَ فَإِذَا رَكَعَ وَضَعَهَا وَإِذَا قَامَ حَمَلَهَا )

   አቢ ቀታዳህ ረዲየላሁ ዐንሁ የነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከልጆች በተለይም ከሴቷ ጋር ያላቸውን ሁኔታ ሲገልፅልን በሰላት ላይ እንኳን እያሉ እንደማያርቋቸው ያስረዳናል።

« የአላህ መልእክተኛ ለሰላት ወጥተው ሳለ በአንገታቸው ወይም በትከሻቸው ላይ የዘይነብን ልጅ ኡማማን ተሸክመዋት ነበርና፤ ሩኩዕ ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ አውርደው ያስቀምጧትና ቀና ብለው ሲቆሙ ደግሞ መልሰው ይሸከሟታል።» ብሏል።

   በጃሂሊያው ህብረተሰብ ዘንድ ሴት ልጅ ከምንም ቁምነገር የማትቆጠርና በመወለዷም የምትናቅ የሚታፈርባት ውዳቂ ተደርጋ ነበር የምትታየው።

   ይህ ሴትን ልጅ ዝቅ የማድረግና ወንድን ልጅ ያለ አግባብ ከፍ ከፍ የማድረግ ዝንባሌ አሁንም ይታያል።

   እገሊት ወለደች የሚል ዜና ሲደርሳቸው እንኳ መጀመርያ ከአንደበታቸው የሚወጣው አልሀምዱሊላህ እንኳን በሰላም ገላገላት ሳይሆን ምን ወለደች የሚሉ በርካቶች ናቸው።

   ወንድ ❗ ሲባሉም መዝለል እስኪቀራቸው ጮቤ የሚረግጡ፣ በፈገግታ የሚሞሉ፤ በእንኳን ደስ ያላችሁ ወሬውን የሚያደምቁ ስፍር ቁጥር የላቸውም።

ይህንንም አላህ አዝዘ ወጀልለ ሲገልፅልን

” وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِالْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ .“ 
[النحل:58]،

« አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡ »
አል ነህል (58) 

   እርግጥ አንዳንዶቹ በዚህ ዘመን ሴት ልጅ ማግኘት ፈተና ስለሆነ ነው የሚሉ የተለያዩ ቀጫጭን መከራከርያዎችን ያቀርቡ ይሆናል።

   ነገር ግን ሴቷን የወለደቿም ሴት ናት፣ እናንተንም የወለደቿም ሴት ናት።

    ችግሩ ሴትነቷ ላይ ብቻ ሳይሆን አስተዳደጋችሁና በትኩረት እንክብካቤ መስጠታችሁ ላይ ነው።

   እርግጥ ሙስሊሞች ዘንድ ሴት ልጅን እንደ ንግስት ማየቱና መንከባከቡ ገና ከመወለዷ ጀምሮ ነው።

   ሴትን ልጅ ተንከባክቦ ማሳደግ ክብደት ስላለው የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሴት ልጆችን ከባድ ደረጃ በመግለፅ  እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማበረታታት የሚቀጥለው ብለውናል።

قال النبي صلى الله عليه وسلم
 ”من ابتلي من هذه البنات بشيء فأحسن إليهم  كن له  ستر من النار “

« ከእናንተ መካከል  በእነዚህ ሴቶች  የተሞከረና፣ለእነርሱ መልካምን የዋለ ከእሳት ከለላ ይሆኑታል። »

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

  ማለትም እነሱን አፍርቶ አሳድጎ አስተምሮ ለወግ ማእረግ ለማድረስ ሲል የተቸገረ፣ 

   ክብሯና ማንነቷ እንዳይሸራረፍ የደከመ፣

    የሴት ልጅ ወላጅ መሆን እንደ መታፈርያ ሲቆጠር የማህበረሰቡን መጥፎ ባህል ችላ ብሎ ታግሶ እሷን በማግኘቱ የኮራ፤

    ነገ የቂያም ቀን እሳት የሚያስገባው ወንጀል ቢኖረው እንኳን ለነዚህ ሙእሚን ወላጆች ሸፋኣ ትሆንላቸዋለች እያሉን ነው።

 عن أنس رضي الله عنه قال:
 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
” من عال جاريتين حتى تبلغا، جاء يوم القيامة أنا وهو -وضم أصابعه-. “
رواه مسلم.

በኢማሙ ሙስሊም ዘገባም
« ሁለት ሴት ልጆቹ አድገው ለቁምነገር እስኪበቁ የተንከባከባቸው ሰው የውመል ቂያማ ይመጣል። ያኔ እኔና እሱ ጎን ለጎን እንሆናለን በማለት ሁለቱን ጣታቸውን አቆራኝተው አሳዩ።

وفي رواية الترمذي: 
 دخلت أنا وهو الجنة كهاتين. وأشار بأصبعيه. 

በቲርሚዚ ዘገባ
" እኔና እሱ ጀነት እንገባለን በማለት ጣታቸውን አቆራኝተው አሳዩ።"  ይላል

    " عالهما "
  የሚለውን ኢማሙ ነወዊ ሲያብራሩት እነሱን በመርዳት በማሳደግ ላይ የሆነ  በማለት ገልፀዋል።

    ሴት ልጅን ማስተማር 
 ማህበረሰብን  ማስተማር ነው። 
ሴት ልጅ እናት ነች። ሴት ልጅ የልጆቿ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነች።

   ሴትን መንከባከብ ሲባልም የወለዷትን ብቻ ሳይሆን እህትንም መንከባከብ እንደሚካተትበት ተወስቷል።

وقوله صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ :

 ( مَنْ كَانَ لَهُ ثَلَاثُ بَنَاتٍ أَوْ ثَلَاثُ أَخَوَاتٍ أَوْ ابْنَتَانِ أَوْ أُخْتَانِ فَأَحْسَنَ صُحْبَتَهُنَّ وَاتَّقَى اللَّهَ فِيهِنَّ فَلَهُ الْجَنَّةُ )
 رواه الترمذي 

« ሶስት ሴት ልጆች ያሉት ወይም ሶስት እህቶች ያሉት፣ ወይም ሁለት ሴት ልጆች ወይም ሁለት እህቶች ኖሮት ከነሱ ጋር ያለውን ጓደኝነት ያሳመረ ( በመልካም አያያዝ የተኗኗራቸው) በነሱም ጉዳይ አላህን የፈራ ለሆነ ሰው ጀነት አለለት። »

   ሴት ልጆችን የጓዳ ውስጥ ተላላኪ በማድረግ ወደ ወንዱ ብቻ ትኩረት መስጠቱም የብዙሃን ስህተት ሆኖ ይታያል። ይህንን ማድረጉንም ትተን ኢስላማዊም ይሁን የአካዳሚ  ትምህርትን ልናስተምራትና ከወንዱ እኩል ልንንከባከባት ይገባል።

10ـ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : (( مَنْ وُلِدَتْ لَهُ ابْنَةٌ فَلَمْ يَئِدْهَا وَلَمْ يُهِنْهَا وَلَمْ يُؤْثِرْ وَلَدَهُ عَلَيْهَا يَعْنِي الذَّكَرَ أَدْخَلَهُ اللَّهُ بِهَا الْجَنَّةَ ))

ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወሩን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

« ሴት ልጅ ተወልዳለት ዝቅ ያላደረጋትና ያላዋረዳት፣ እንዲሁም ወንድ ልጁን ከፍ ከፍ ያላደረገባት፣ በሷ ሰበብ አላህ ጀነትን አስገብቶታል።» ብለዋል። 

   ሃላፊነት የሚሰማው  ትውልድ ታበረክትልን  ዘንድም የዲኗን ትምህርት በማስቀደም የዘመናዊውን ትምህርትም ክብሯን ባስጠበቀ መልኩ ማስተማር አለብን።

   በመልካም ሴት ታንፀው የሚያድጉ ልጆች  ለወደፊቱ ማህበረሰብ  የጀርባ አጥንት  ናቸውና ።

    ሴት ልጅ ከተማረች መብትና ግዴታዋን ስለምትረዳ የባሏን፣ የወላጆቿን፣ የልጆቿን፣ የዘመዶቿንና፣ የጎረቤቶቿን ሃቅ አላህን በሚያስደስት መልኩ  ትጠብቃለች ።

   የራሷንም መብትና ግዴታ  ስለምታውቅ ታከብራለች ታስከብራለችም።

   ስለዚህ እርስዎም ለራስዎ፣ ለቤተሰብዎ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ሲሉ ከጎኗ በመሆን በማረም፣ በማበረታታት፣ በማስተማር እና በመርዳት  ልያግዟት ይገባል።

    ውድ ወላጅ ሆይ  !  በተለይ አባቶች ልጅዎትን ዲንን በማሳወቅ  የተጣለብዎትን ከባድ  ሃላፊነት  ለመወጣት  ከአላህ  ከባድ ምንዳ  ለማግኘት  አሁኑኑ ይንቀሳቀሱ ❗
_________
  አላህ ብርታቱን  ይስጣችሁ።
መንገዱንም ያግራላችሁ።
_________
#ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ ያድርጉ ጠቃሚ ትምህርት ያገኙበታል።

www.facebook.com/tenbihat
_____
ዝግጅት #ኡሙ_አብዱረህማን_ሩቀያህ_አብደላህ
ትንታኔ አቡፈውዛን

󾕈 13 March 15
22 Jumad al Awwal 1436‎'

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ• 18
ሴት ልጅ ያለዎት እንደሆን ታድለዋል

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በጃሂሊያ ዘመን ሰዎች የነበረውን የሴት ልጆች ጭቆናና ንቀት ለማስወገድ ከጌታቸው በተላኩት መሰረት በርካታ የሴት ልጆችን ክብርና መብት የሚያስጠብቅ ትምህርቶችን ለሶሃባዎች አስተምረዋል። በተግባርም አሳይተዋል።
1ـ عَنْ أَبِي قَتَادَةَ : ( أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَرَجَ يُصَلِّي وَقَدْ حَمَلَ عَلَى عُنُقِهِ أَوْ عَاتِقِهِ أُمَامَةَ بِنْتَ زَيْنَبَ فَإِذَا رَكَعَ وَضَعَهَا وَإِذَا قَامَ حَمَلَهَا )
አቢ ቀታዳህ ረዲየላሁ ዐንሁ የነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከልጆች በተለይም ከሴቷ ጋር ያላቸውን ሁኔታ ሲገልፅልን በሰላት ላይ እንኳን እያሉ እንደማያርቋቸው ያስረዳናል።
« የአላህ መልእክተኛ ለሰላት ወጥተው ሳለ በአንገታቸው ወይም በትከሻቸው ላይ የዘይነብን ልጅ ኡማማን ተሸክመዋት ነበርና፤ ሩኩዕ ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ አውርደው ያስቀምጧትና ቀና ብለው ሲቆሙ ደግሞ መልሰው ይሸከሟታል።» ብሏል።
በጃሂሊያው ህብረተሰብ ዘንድ ሴት ልጅ ከምንም ቁምነገር የማትቆጠርና በመወለዷም የምትናቅ የሚታፈርባት ውዳቂ ተደርጋ ነበር የምትታየው።
ይህ ሴትን ልጅ ዝቅ የማድረግና ወንድን ልጅ ያለ አግባብ ከፍ ከፍ የማድረግ ዝንባሌ አሁንም ይታያል።
እገሊት ወለደች የሚል ዜና ሲደርሳቸው እንኳ መጀመርያ ከአንደበታቸው የሚወጣው አልሀምዱሊላህ እንኳን በሰላም ገላገላት ሳይሆን ምን ወለደች የሚሉ በርካቶች ናቸው።
ወንድ ሲባሉም መዝለል እስኪቀራቸው ጮቤ የሚረግጡ፣ በፈገግታ የሚሞሉ፤ በእንኳን ደስ ያላችሁ ወሬውን የሚያደምቁ ስፍር ቁጥር የላቸውም።
ይህንንም አላህ አዝዘ ወጀልለ ሲገልፅልን
” وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِالْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ .“
[النحل:58]،
« አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡ »
አል ነህል (58)
እርግጥ አንዳንዶቹ በዚህ ዘመን ሴት ልጅ ማግኘት ፈተና ስለሆነ ነው የሚሉ የተለያዩ ቀጫጭን መከራከርያዎችን ያቀርቡ ይሆናል።
ነገር ግን ሴቷን የወለደቿም ሴት ናት፣ እናንተንም የወለደቿም ሴት ናት።
ችግሩ ሴትነቷ ላይ ብቻ ሳይሆን አስተዳደጋችሁና በትኩረት እንክብካቤ መስጠታችሁ ላይ ነው።
እርግጥ ሙስሊሞች ዘንድ ሴት ልጅን እንደ ንግስት ማየቱና መንከባከቡ ገና ከመወለዷ ጀምሮ ነው።
ሴትን ልጅ ተንከባክቦ ማሳደግ ክብደት ስላለው የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሴት ልጆችን ከባድ ደረጃ በመግለፅ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማበረታታት የሚቀጥለው ብለውናል።
قال النبي صلى الله عليه وسلم
”من ابتلي من هذه البنات بشيء فأحسن إليهم كن له ستر من النار “
« ከእናንተ መካከል በእነዚህ ሴቶች የተሞከረና፣ለእነርሱ መልካምን የዋለ ከእሳት ከለላ ይሆኑታል። »
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ማለትም እነሱን አፍርቶ አሳድጎ አስተምሮ ለወግ ማእረግ ለማድረስ ሲል የተቸገረ፣
ክብሯና ማንነቷ እንዳይሸራረፍ የደከመ፣
የሴት ልጅ ወላጅ መሆን እንደ መታፈርያ ሲቆጠር የማህበረሰቡን መጥፎ ባህል ችላ ብሎ ታግሶ እሷን በማግኘቱ የኮራ፤
ነገ የቂያም ቀን እሳት የሚያስገባው ወንጀል ቢኖረው እንኳን ለነዚህ ሙእሚን ወላጆች ሸፋኣ ትሆንላቸዋለች እያሉን ነው።
عن أنس رضي الله عنه قال:
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
” من عال جاريتين حتى تبلغا، جاء يوم القيامة أنا وهو -وضم أصابعه-. “
رواه مسلم.
በኢማሙ ሙስሊም ዘገባም
« ሁለት ሴት ልጆቹ አድገው ለቁምነገር እስኪበቁ የተንከባከባቸው ሰው የውመል ቂያማ ይመጣል። ያኔ እኔና እሱ ጎን ለጎን እንሆናለን በማለት ሁለቱን ጣታቸውን አቆራኝተው አሳዩ።
وفي رواية الترمذي:
دخلت أنا وهو الجنة كهاتين. وأشار بأصبعيه.
በቲርሚዚ ዘገባ
" እኔና እሱ ጀነት እንገባለን በማለት ጣታቸውን አቆራኝተው አሳዩ።" ይላል
" عالهما "
የሚለውን ኢማሙ ነወዊ ሲያብራሩት እነሱን በመርዳት በማሳደግ ላይ የሆነ በማለት ገልፀዋል።
ሴት ልጅን ማስተማር
ማህበረሰብን ማስተማር ነው።
ሴት ልጅ እናት ነች። ሴት ልጅ የልጆቿ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነች።
ሴትን መንከባከብ ሲባልም የወለዷትን ብቻ ሳይሆን እህትንም መንከባከብ እንደሚካተትበት ተወስቷል።
وقوله صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ :
( مَنْ كَانَ لَهُ ثَلَاثُ بَنَاتٍ أَوْ ثَلَاثُ أَخَوَاتٍ أَوْ ابْنَتَانِ أَوْ أُخْتَانِ فَأَحْسَنَ صُحْبَتَهُنَّ وَاتَّقَى اللَّهَ فِيهِنَّ فَلَهُ الْجَنَّةُ )
رواه الترمذي
« ሶስት ሴት ልጆች ያሉት ወይም ሶስት እህቶች ያሉት፣ ወይም ሁለት ሴት ልጆች ወይም ሁለት እህቶች ኖሮት ከነሱ ጋር ያለውን ጓደኝነት ያሳመረ ( በመልካም አያያዝ የተኗኗራቸው) በነሱም ጉዳይ አላህን የፈራ ለሆነ ሰው ጀነት አለለት። »
ሴት ልጆችን የጓዳ ውስጥ ተላላኪ በማድረግ ወደ ወንዱ ብቻ ትኩረት መስጠቱም የብዙሃን ስህተት ሆኖ ይታያል። ይህንን ማድረጉንም ትተን ኢስላማዊም ይሁን የአካዳሚ ትምህርትን ልናስተምራትና ከወንዱ እኩል ልንንከባከባት ይገባል።
10ـ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : (( مَنْ وُلِدَتْ لَهُ ابْنَةٌ فَلَمْ يَئِدْهَا وَلَمْ يُهِنْهَا وَلَمْ يُؤْثِرْ وَلَدَهُ عَلَيْهَا يَعْنِي الذَّكَرَ أَدْخَلَهُ اللَّهُ بِهَا الْجَنَّةَ ))
ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወሩን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
« ሴት ልጅ ተወልዳለት ዝቅ ያላደረጋትና ያላዋረዳት፣ እንዲሁም ወንድ ልጁን ከፍ ከፍ ያላደረገባት፣ በሷ ሰበብ አላህ ጀነትን አስገብቶታል።» ብለዋል።
ሃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ታበረክትልን ዘንድም የዲኗን ትምህርት በማስቀደም የዘመናዊውን ትምህርትም ክብሯን ባስጠበቀ መልኩ ማስተማር አለብን።
በመልካም ሴት ታንፀው የሚያድጉ ልጆች ለወደፊቱ ማህበረሰብ የጀርባ አጥንት ናቸውና ።
ሴት ልጅ ከተማረች መብትና ግዴታዋን ስለምትረዳ የባሏን፣ የወላጆቿን፣ የልጆቿን፣ የዘመዶቿንና፣ የጎረቤቶቿን ሃቅ አላህን በሚያስደስት መልኩ ትጠብቃለች ።
የራሷንም መብትና ግዴታ ስለምታውቅ ታከብራለች ታስከብራለችም።
ስለዚህ እርስዎም ለራስዎ፣ ለቤተሰብዎ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ሲሉ ከጎኗ በመሆን በማረም፣ በማበረታታት፣ በማስተማር እና በመርዳት ልያግዟት ይገባል።
ውድ ወላጅ ሆይ ! በተለይ አባቶች ልጅዎትን ዲንን በማሳወቅ የተጣለብዎትን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት ከአላህ ከባድ ምንዳ ለማግኘት አሁኑኑ ይንቀሳቀሱ
_________
አላህ ብርታቱን ይስጣችሁ።
መንገዱንም ያግራላችሁ።
_________
‪#‎ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ‬ ያድርጉ ጠቃሚ ትምህርት ያገኙበታል።
www.facebook.com/tenbihat
_____
ዝግጅት ‪#‎ኡሙ_አብዱረህማን_ሩቀያህ_አብደላህ‬
ትንታኔ አቡፈውዛን
📋 13 March 15
22 Jumad al Awwal 1436

Post a Comment

0 Comments