Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እቤት ውስጥ ስራ በዝቶ ሰራተኛ የለሽምን?? የምርጧ አርዓያ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ ታሪክ!!


እቤት ውስጥ ስራ በዝቶ ሰራተኛ የለሽምን??

የምርጧ አርዓያ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ ታሪክ!!

ምርጥ አርዓያ ከሚሆኑ እጹብ ድንቅ እንስቶች ውስጥ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ (ﷺ) በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡

قال علي رضي الله عنه: «أن فاطمة عليها السلام شكت ما تلقى في يدها من الرحى فأتت النبي صلى الله عليه وسلم تسأله خادماً، فلم تجده فذكرت ذلك لـعائشة فلما جاء أخبرته قال: فجاءنا وقد أخذنا مضاجعنا فذهبت أقوم فقال: مكانك، فجلس بيننا حتى وجدت برد قدميه على صدري، فقال: ألا أدلكم على ما هو خير لكما من خادم؟ إذا أويتما إلى فراشكما أو أخذتما مضاجعكما فكبرا أربعاً وثلاثين، وسبحا ثلاثاً وثلاثين، واحمدا ثلاثاً وثلاثين فهذا خير لكما من خادم». رواه الإمام البخاري

አሊይ (ረድየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፤ « ፋጢማ ከስራ ብዛት በእጇ ላይ የሚደርሰውን ህመም አማረረችና፤ ሰራተኛ እንዲሰጣት ለመጠየቅ መልእክተኛው ﷺ ዘንድ ሄደች። ነገር ግን አላገኘቻቸውምና ለባለቤታቸው አዒሻ ተናግራ ተመለሰችና ሲመጡ ነገረቻቸው። የአላህ መልክተኛም ﷺ በሰሙ ጊዜ ወደኛ መጡና ተጋድመን አገኙን። ከመሀከላችን ሲቀመጡ የእግራቸው ቅዝቃዜ ተሰማኝ። እንዲህም አሉን፤ ፡- «ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለውን ነገር ላመላክታችሁን? ወደ ፍራሽ ስትጠጉ ወይም በመኝታችሁ ላይ ስትሆኑ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሀነላህ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አልሀምዱሊላህ፣ ሰላሳ አራት አላሁ አክበር ጊዜ በሉ! ይህ ለእናንተ ከአገልጋይ የበለጠ ነው::»

አዎን! አማኝ ሴት ከዚህ ታሪክ በርካታ ቁምነገሮችን ትማራለች፤

1) ደስታንም ሃዘንንም ከውድ ባሏ ጎን በመቆም ታሳልፋለች፤ የቤት ውስጥ ጣጣዎችን ለመሸፈን ትጥራለች።

2) በቤት ውስጥ ስራ ለሚገጥማት ድካም ታጋሽ ናት፤ እንኳን እሷ የመልእክተኛው ልጅ ታላቋ ፋጢማህ በትእግስት አሳልፋዋለች

3) ይህ ሀዲስ እውነተኛ መፍትሄ ነብያዊ ምክርም ነውና ትሰራበታለች። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑተይሚያህ ይህ ዚክር እውነትም ላመነበት አካላዊ ጥንካሬን ይለግሳል ብለዋል።

4) ኑሮ ሲከብደባት ከቅርብ ቤተሰቦች እርዳታን ከመጠየቅ
ኩራት አያግዳትም! ለመሆኑ ከነሱ በላይ ለማን ችግሯን ልታካፍል ነው?

ባለቤትሽን በመኻደምና በማስደሰት ፋጢማን አርአያ ለማድረግ ዝግጁ ነሽ?

#ሊንኩን_በመጫን_ፔጁን_ላይክ(like) _ያድርጉ =====>
--------------------------------
www.facebook.com/tenbihat
--------------------------------
ኢንሻ አላህ ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ይገበዩበታል!!!

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!