Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለፈገግታ! ሙጊራህ .....

ለፈገግታ!
ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ ረዲየላሁ እንዲህ ይላሉ:
"አንድ ሰው ሸውዶኝ አያውቅም ከአንድ ወጣት በስተቀር። የሆነ ጊዜ አንዲት ሴት ላገባ አሰብኩኝና ሳማክረው:
"አሚራችን ሆይ! እኔ ባታገባት ይሻላል እላለሁ" አለኝ። "ለምን?" ስለው "የሆነ ሰው ሲስማት አይቻለሁ" አለኝ።
ከዚያ እሱ እራሱ እንዳገባት ሰማሁ።
"የሆነ ሰው ሲስማት አይቻለሁ አላልክም ነበር" ስለው
.
.
.
..
.
.
.
"አዎ ልጅ እያለች አባቷ ሲስማት አይቻለሁ" አለኝ።
【አልቢዳያ ወንኒሀያህ: 8/53】