Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዑለማ እና የጋዜጤኛ ልዩነት በሰሓባዎች ክብር ዙርያ

የዑለማ እና የጋዜጤኛ ልዩነት በሰሓባዎች ክብር ዙርያ
______________________________________________________

ኡስማን ኢብኑ ዓፋንን በመጥፎ የሚያነሳ ጃሂል ወይም የቢድዓ አራማጅ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። ሰለፎቻችን ግን ሰሓባዎችን በጥሩ እንጂ ስማቸውን አያነሱም ነበረ፣ ሰዉንም ሲያስተምሩ የነበረው ይሄው ነው። ቀደምት ያልደፈሩትን አጀንዳ ለምንድነው መጤ የሆኑ ሰዎች በተለይም ጋዜጤኞች የደፈሩት??? ልዩነቱ እዚሁ ላይ ማክሸፍ ይቻላል።
እሱም ዓሊሞች ልካቸውን ያውቃሉ። ትልቅ አእምሮ እና ምጥን ምላስ ነው ያላቸው/የነበራቸው። ጋዜጤኞች እና የመጤ ቡድን መሪዎች (ልክ እንደ ሺዓ እና ኢኽዋን) ልካቸውን አያውቁም፣ የሰሓባን ልክ አያውቁ፣ የዓሊም ልክ አያውቁ፣ የእስልምናን ልክ አያውቁም። ዝም ብሎ መንዳት።
ክርስትያኖች "የእየሱስ ወዳጆች ማን ናቸው?" ሲባሉ "12ቱ ሓዋርያቶች" ይላሉ። ሺዓ እና መሰሎቻቸው ደግሞ "የረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጠላት ማን ናቸው?" ሲባሉ "ሰሓባ" ይላሉ። ባጭሩ አሁን ያለንበት ዘመን ሲጠቃለል የሰሓባ ጠበቃ "ኡማ በታታኝ" ነው። የሰሓባ ተሳዳቢ ጠበቃ ደግሞ "የኡማው ብርቅዬ" ሆኗል። በዚህም ማንም መሸወድ የለበትም።
አኚህ ሰዎች እኮ ዞሮ ዞሮ እስልምናን ነው እየተሳደቡ ያሉት። "አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ለረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጓዳኛ አመራረጥ አልቻለበትም" እያሉ ነው እኮ ከአፋቸው ባይወጣም። ድፍረት

Post a Comment

0 Comments