Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንዲት ሴት ውዱእ ላይ ሆና የልጇን ሽንትና ሰጋራ ብታጥብ ውዱዋ ይፈርሳልን? ሸይኽ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ)

ሸይኽ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ይህ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
አንዲት ሴት ውዱእ ላይ ሆና የልጇን ሽንትና ሰጋራ ብታጥብ ውዱዋ ይፈርሳልን?
መልስ፦
"አንዲት ሴት የሴት ልጇን ወይም የወንድ ልጇን ስታጥብ ብልቱን/ቷን ብትነካ ውዱእን እነደገና አድርጊ ተብላ አትገደድም።
እጇን ብቻ ማጠብ ነው የሚጠበቅባት፣
ብልትን ያለ ስሜት መንካት ውዱእን አያስወጅብም(ግዴታ አያስደርግም)፣
እንደሚታወቀው አንድ ሴት ልጇን ሲታጥብ ስሜት ውል ይልባታል ተብሎ አይታሰብም፣
ነጃሳ ስለነካች እጇን ብቻ ነው እርሷ ላይ የሚጠበቀው፣ውዱእን መድግም በርሷ ላይ ግዴታ አይደለም፣
አበቃ!።"
【መጅሙዑል ፈታዋ 11/203】